ኢዮብ 38:1-5
ኢዮብ 38:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኤልዩስ ንግግሩን ካቆመ በኋላ እግዚአብሔር በደመናና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮብን ጠየቀው፤ እንዲህም አለው፦ “ከእኔ ምክርን የሚሸሽግ፥ በልቡም ነገርን የሚደብቅ ማን ነው? ከእኔ ይሰውረዋልን? እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ፤ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም መልስልኝ። ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆነ ንገረኝ። ብታውቅ መስፈሪያዋን የወሰነ፥ በላይዋስ የመለኪያ ገመድን የዘረጋ ማን ነው?
ኢዮብ 38:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰለት፤ እንዲህም አለው፤ “ዕውቀት በጐደለው ቃል፣ ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማን ነው? እስኪ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤ እኔ ልጠይቅህ፣ አንተም መልስልኝ። “ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ? በርግጥ የምታስተውል ከሆንህ ንገረኝ። ካወቅህ፣ መጠኗን ለይቶ ማን ወሰነ? በላይዋስ መለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው?
ኢዮብ 38:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ፦ ያለ እውቀት በሚነገር ቃል ምክርን የሚያጨልም ይህ ማነው? እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ፥ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ተናገረኝ። ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር። ብታውቅስ መሠፈሪያዋን የወሰነ፥ በላይዋስ የመለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው?
ኢዮብ 38:1-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮብን እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር “ይህ፥ ያለ ዕውቀት በሚነገሩ ቃላት ምክሬን የሚያቃልል እርሱ ማነው? እስቲ በፊቴ እንደ ወንድ ታጠቅ፤ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም መልስልኝ። ለመሆኑ ዓለምን ስፈጥር አንተ በዚያ ነበርክን? የምታውቅና የምታስተውል ከሆነ እስቲ ንገረኝ። የምድርን መጠን የወሰነ ማን ነው? በእርሱዋ ላይስ የመለኪያ መስመሮችን የዘረጋ ማን እንደ ሆነ ታውቃለህን?