መጽ​ሐፈ ኢዮብ 38:1-5

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 38:1-5 አማ2000

ኤል​ዩስ ንግ​ግ​ሩን ካቆመ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​መ​ናና በዐ​ውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮ​ብን ጠየ​ቀው፤ እን​ዲ​ህም አለው፦ “ከእኔ ምክ​ርን የሚ​ሸ​ሽግ፥ በል​ቡም ነገ​ርን የሚ​ደ​ብቅ ማን ነው? ከእኔ ይሰ​ው​ረ​ዋ​ልን? እን​ግ​ዲህ እንደ ሰው ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ እጠ​ይ​ቅ​ሃ​ለሁ፥ አን​ተም መል​ስ​ልኝ። ምድ​ርን በመ​ሠ​ረ​ትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበ​ርህ? ታስ​ተ​ውል እንደ ሆነ ንገ​ረኝ። ብታ​ውቅ መስ​ፈ​ሪ​ያ​ዋን የወ​ሰነ፥ በላ​ይ​ዋስ የመ​ለ​ኪያ ገመ​ድን የዘ​ረጋ ማን ነው?