ኢዮብ 33:15-18
ኢዮብ 33:15-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ፥ በሰዎች ላይ ታላቅ ድንጋጤን ያመጣል። በዚያን ጊዜ የሰዎችን ማስተዋል ይከፍታል፥ ግርማ ባለው ራእይም ያስደነግጣቸዋል፤ ሰውን ከኀጢአቱ ይመልሰው ዘንድ፥ ሥጋውንም ከውድቀት ያድነው ዘንድ፥ ነፍሱን ከሞት ያድናታል፤ በሰይፍም እንዳይጠፋ ይጠብቀዋል።
Share
ኢዮብ 33 ያንብቡኢዮብ 33:15-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሰዎች ዐልጋቸው ላይ ተኝተው ሳሉ፣ ከባድ እንቅልፍ ሲወድቅባቸው፣ በሕልም፣ በሌሊትም ራእይ ይናገራል። በጆሯቸው ይናገራል፤ በማስጠንቀቂያም ያስደነግጣቸዋል፤ ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሳል፤ ከትዕቢት ይጠብቃል፤ ነፍሱን ከጕድጓድ፤ ሕይወቱንም ከሰይፍ ጥፋት ያድናል።
Share
ኢዮብ 33 ያንብቡኢዮብ 33:15-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በሕልም፥ በሌሊት ራእይ፥ አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ፥ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ፥ በዚያን ጊዜ የሰዎችን ጆሮ ይከፍታል፥ በተግሣጹም ያስደነግጣቸዋል፥ ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሰው ዘንድ፥ ከሰውም ትዕቢትን ይሰውር ዘንድ፥ ነፍሱን ከጕድጓድ፥ በሰይፍም እንዳይጠፋ ሕይወቱን ይጠብቃል።
Share
ኢዮብ 33 ያንብቡ