ኢዮብ 26:7-14
ኢዮብ 26:7-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሰማይን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም አንዳች አልባ ያንጠለጥላል። ውኃውን በደመና ውስጥ ይቋጥራል፥ ደመናውም ከታች አይቀደድም። የዙፋኑን ፊት ይከድናል፥ ደመናውንም ይዘረጋበታል። ብርሃን ከጨለማ እስከሚለይበት ዳርቻ ድረስ፥ የውኃውን ፊት በተወሰነ ትእዛዙ ከበበው። የሰማይ አዕማድ ይንቀጠቀጣሉ፥ ከተግሣጹም የተነሣ ይደነግጣሉ። በኀይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፥ በማስተዋሉም ዐንበሪውን ይገለብጠዋል። የሲኦል በረኞች ለእርሱ አደሉ። በትእዛዙም ዐመፀኛውን እባብ ገደለው። እነሆ ይህ የመንገዱ ክፍል ነው፤ የቀሩትንም ነገሮቹን እንሰማለን፤ በሚያደርግበትስ ጊዜ የነጐድጓዱን ኀይል የሚያውቅ ማን ነው?”
ኢዮብ 26:7-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የሰሜንን ሰማይ በሕዋው ላይ ዘረጋው፤ ምድርንም እንዲያው በባዶው ላይ አንጠለጠላት። ውሆችን በደመናዎቹ ይጠቀልላል፤ ክብደታቸውም ደመናዎቹን አይሸነቍርም። ደመናዎቹን በላዩ ዘርግቶ፣ የሙሉውን ጨረቃ ፊት ይጋርዳል። ለብርሃንና ለጨለማ ድንበር ይሆን ዘንድ፣ በውሆች ላይ የአድማስ ክበብ አበጀ። የሰማይ ምሰሶዎች ይንቀጠቀጣሉ፤ በተግሣጹም ይደነግጣሉ። በኀይሉ ባሕርን ያናውጣል፤ በጥበቡም ረዓብን ይቈራርጣል። በእስትንፋሱ ሰማያትን አጠራ፤ እጁም ተወርዋሪውን እባብ ወጋች። እነዚህ የሥራው ዳር ዳር ናቸው፤ ስለ እርሱ የሰማነው ምንኛ አነስተኛ ነው! የኀይሉንስ ነጐድጓድ ማን ሊያስተውል ይችላል?”
ኢዮብ 26:7-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም በታችዋ አንዳች አልባ ያንጠለጥላል። ውኆችን በደመናዎቹ ውስጥ ያስራል፥ ደመናይቱም ከታች አልተቀደደችም። የዙፋኑን ፊት ይከድናል፥ ደመናውንም ይዘረጋበታል። ብርሃንና ጨለማ እስከሚለያዩበት ዳርቻ ድረስ፥ በውኆች ፊት ላይ ድንበርን አደረገ። የሰማይ አዕማድ ይንቀጠቀጣሉ፥ ከተግሣጹም የተነሣ ይደነግጣሉ። በኃይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፥ በማስተዋሉም ረዓብን ይመታል። በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ፥ እጁም በራሪይቱን እባብ ወጋች። እነሆ፥ ይህ የመንገዱ ዳርቻ ብቻ ነው፥ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉንስ ነጐድጓድ ያስተውል ዘንድ ማን ይችላል?
ኢዮብ 26:7-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር የሰሜንን ሰማይ በሕዋው ላይ ዘረጋ፤ ምድርም በባዶ ቦታ እንድትንጠለጠል አደረገ። እግዚአብሔር፥ ደመናዎች ውሃን እንዲጠቀልሉ ያደርጋል፤ ከውሃውም የተነሣ ደመናዎቹ አይቀደዱም። የሙሉ ጨረቃውን ፊት ይጋርዳል፤ በደመና ይሸፍነዋል። ብርሃንና ጨለማን ለመለየት በውቅያኖስ ፊት አድማስን ድንበር አድርጎ ዘረጋ። እርሱ በሚገሥጻቸው ጊዜ፥ የሰማይ አዕማድ በድንጋጤ ይናወጣሉ። በኀይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፤ በጥበቡም ረዓብ የተባለውን ታላቅ አውሬ ያጠፋል። በእስትንፋሱ ሰማይን ያጠራል፤ በእጁም ተወርዋሪውን እባብ ይወጋል። እነዚህ ሁሉ እግዚአብሔር ከሚሠራቸው ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፤ የምንሰማውም ሹክሹክታውን ብቻ ነው፤ የኀይሉን ነጐድጓድማ ማን ሊያስተውል ይችላል?”
ኢዮብ 26:7-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ ምድሪቱንም ያለአንዳች ድጋፍ ያንጠለጥላል። ውኆችን በደመናዎቹ ውስጥ ያስራል፥ ደመናይቱም ከታች አልተቀደደችም። የዙፋኑን ፊት ይሸፍናል፥ ደመናውንም ይዘረጋበታል። ብርሃንና ጨለማ እስከሚለያዩበት ዳርቻ ድረስ፥ በውኆች ፊት ላይ ድንበርን አሰመረ። የሰማይ አዕማድ ይንቀጠቀጣሉ፥ ከተግሣጹም የተነሣ ይደነግጣሉ። በኃይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፥ በማስተዋሉም ረዓብን ይመታል። በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ፥ እጁም የሚሸሸውን እባብ ወጋች። እነሆ፥ እነኚህ የሥራዎቹ ጫፎች ብቻ ነው፥ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉንስ ነጐድጓድ ማን ማስተዋል ይችላል?”