ኤርምያስ 42:1-12

ኤርምያስ 42:1-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ፥ የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የሐ​ና​ንያ ልጅ ኢዛ​ን​ያስ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ መጡ። እን​ዲ​ህም አሉት፥ “እባ​ክህ ልመ​ና​ችን በፊ​ትህ ትድ​ረስ፤ ስለ እኛ፥ ስለ እነ​ዚ​ህም ቅሬ​ታ​ዎች ሁሉ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን፤ ዐይ​ኖ​ችህ እንደ አዩን ከብዙ ጥቂት ቀር​ተ​ና​ልና። አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የም​ን​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገ​ድና የም​ና​ደ​ር​ገ​ውን ነገር ይን​ገ​ረን።” ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም አላ​ቸው፥ “ሰም​ታ​ች​ኋል፤ እነሆ እንደ ቃላ​ችሁ ወደ አም​ላ​ካ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​መ​ል​ስ​ል​ኝን ሁሉ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ን​ተም አን​ድም ቃል አል​ሸ​ሽ​ግም።” ኤር​ም​ያ​ስ​ንም፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ እኛ የላ​ከ​ህን ነገር ሁሉ ባና​ደ​ርግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን እው​ነ​ተ​ኛና ታማኝ ምስ​ክር ይሁን። የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ​ም​ን​ሰማ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልን፥ መል​ካም ወይም ክፉ ቢሆን፥ አን​ተን ወደ እርሱ የም​ን​ል​ክህ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እን​ሰ​ማ​ለን” አሉት። እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዐ​ሥር ቀን በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ መጣ። የቃ​ር​ሔ​ም​ንም ልጅ ዮሐ​ና​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን የጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ፥ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ ጠራ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ልመ​ና​ች​ሁን በፊቱ አቀ​ርብ ዘንድ ወደ እርሱ የላ​ካ​ች​ሁኝ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አደ​ር​ግ​ባ​ችሁ ዘንድ ከአ​ሰ​ብ​ሁት ክፉ ነገር ተመ​ል​ሻ​ለ​ሁና በዚች ምድር ብት​ቀ​መጡ እሠ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ አላ​ፈ​ር​ሳ​ች​ሁም፥ እተ​ክ​ላ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ አል​ነ​ቅ​ላ​ች​ሁም። ከም​ት​ፈ​ሩት ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ፊት አት​ፍሩ፤ አድ​ና​ችሁ ዘንድ፥ ከእ​ጁም አስ​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ እኔ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍሩ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ይቅ​ር​ታን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይቅ​ርም እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ ሀገ​ራ​ች​ሁም እመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ለሁ።

ኤርምያስ 42:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የቃሬያን ልጅ ዮሐናንና የሆሻያን ልጅ ያእዛንያን ጨምሮ፣ የጦር መኰንኖች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ቀርበው፣ ነቢዩ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “ቀድሞ ብዙዎች ነበርን አሁን እንደምታየን ግን የቀረነው ጥቂት ነን፤ ስለዚህ እባክህ ልመናችንን ስማ፤ ለዚህ ለተረፈው ሕዝብ ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ። አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት መሄድ እንዳለብንና ምን ማድረግ እንደሚገባን እንዲነግረን ጸልይልን።” ነቢዩ ኤርምያስም፣ “ሰምቻችኋለሁ፤ እንዳላችሁት ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር በርግጥ እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔር ያለኝን ሁሉ አንዳች ሳላስቀር እነግራችኋለሁ” አላቸው። እነርሱም ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “እግዚአብሔር አምላክህ በአንተ በኩል የሚለውን ነገር ሁሉ ባናደርግ፣ እግዚአብሔር ራሱ በእኛ ላይ እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁን። አምላካችንን እግዚአብሔርን በመታዘዝ መልካም ይሆንልን ዘንድ ነገሩ ቢስማማንም ባይስማማንም፣ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንታዘዛለን።” ከዐሥር ቀን በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። ስለዚህ የቃሬያን ልጅ ዮሐናንንና፣ ከርሱም ጋራ የነበሩትን የጦር መኰንኖች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡን ሁሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ ጠርቶ፤ እንዲህ አላቸው፤ “ልመናችሁን በፊቱ እንዳቀርብ ወደ እርሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ባመጣሁባችሁ ጥፋት ዐዝኛለሁና፣ በዚህች ምድር ብትቀመጡ እሠራችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፤ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም። አሁን የሚያስፈራችሁን የባቢሎንን ንጉሥ አትፍሩ፤ አድናችሁ ዘንድ ከእጁም አስጥላችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋራ ነኝና አትፍሩ ይላል እግዚአብሔር፤ እርሱ እንዲምራችሁና ወደ አገራችሁ እንዲመልሳችሁ እኔ እምራችኋለሁ።’

ኤርምያስ 42:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የጭፍራ አለቆችም ሁሉ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የሆሻያም ልጅ ያእዛንያ ሕዝብም ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ቀረቡ፥ ነብዩንም ኤርምያስን፦ ዓይኖችህ እንዳዩን ከብዙ ጥቂት ቀርተናልና ልመናችን፥ እባክህ፥ በፊትህ ትድረስ፥ አምላክህም እግዚአብሔር የምንሄድበትን መንገድና የምናደርገውን ነገር ያሳየን ዘንድ ስለ እኛ፥ ስለዚህ ቅሬታ ሁሉ፥ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት። ነቢዩም ኤርምያስ፦ ሰምቻችኋለሁ፥ እነሆ፥ እንደ ቃላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፥ እግዚአብሔርም የሚመልስላችሁን ሁሉ እነግራችኋለሁ፥ ከእናንተም ምንም አልሸሽግም አላቸው። ኤርምያስንም፦ አምላክህ እግዚአብሔር በአንተ እጅ ወደ እኛ የላከውን ነገር ሁሉ ባናደርግ፥ እግዚአብሔር በመካከላችን እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁን። የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል በመስማታችን መልካም እንዲሆንልን፥ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን፥ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል እንሰማለን አሉት። ከአሥር ቀን በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። የቃሬያንም ልጅ ዮሐናንን ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጭፍራ አለቆች ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝቡንም ሁሉ ጠራ፥ እንዲህም አላቸው፦ ጸሎታችሁን በፊቱ አቀርብ ዘንድ ወደ እርሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስላደረግሁባችሁ ክፉ ነገር ተጸጽቻለሁና በዚህች ምድር ብትቀመጡ እሠራችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፥ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም። ከምትፈሩት ከባቢሎን ንጉሥ አትፍሩ፥ አድናችሁ ዘንድ ከእጁም አስጥላችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ፥ ይላል እግዚአብሔር። እርሱ እንዲምራችሁ ወደ አገራችሁም እንዲመልሳችሁ እኔ እምራችኋለሁ።

ኤርምያስ 42:1-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የሠራዊት አለቆች፥ የቃሬሐ ልጅ ዮሐናንና የሆሻያ ልጅ ዐዛርያስ ሕዝቡም ሁሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ ወደ እኔ መጥተው እንዲህ አሉኝ፦ “እባክህ የምንጠይቅህን ነገር አድርግልን! ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን! ከስደት ለተረፍነው ሁሉ ጸልይልን! ቀድሞ ብዙዎች ነበርን፤ አሁን ግን አንተ ራስህ እንደምታየን ጥቂቶች ብቻ ቀርተናል፤ ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር በየት አቅጣጫ መሄድ እንዳለብንና ምን ማድረግ እንደሚገባን ይገልጥልን ዘንድ ጸልይልን።” እኔም “መልካም ነው፤ ልክ እናንተ በጠየቃችሁት መሠረት ወደ እግዚአብሔር አምላካችሁ እጸልይላችኋለሁ፤ የሚገልጥልኝንም ሁሉ ከእናንተ ምንም ነገር ሳልሰውር እነግራችኋለሁ” ብዬ መለስኩላቸው። ከዚህም በኋላ እነርሱ እንዲህ አሉኝ “አምላክህ እግዚአብሔር በአንተ አማካይነት የሚሰጠንን ትእዛዝ ሁሉ በመፈጸም ለቃሉ ታዛዦች ሆነን ባንገኝ፥ እርሱ ራሱ በእኛ ላይ እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁንብን! መልካም ቢሆንም ባይሆንም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ቃል እንታዘዛለን፤ ወደ እርሱ የምንልክህም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብናከብር ሁሉ ነገር የሚሳካልን በመሆኑ ነው።” ከዐሥር ቀን በኋላ እግዚአብሔር ተናገረኝ፤ ስለዚህም ዮሐናንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን የሠራዊት አለቆች ሕዝቡንም ሁሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ ወደ እኔ እንዲመጡ ጠራኋቸው፤ እንዲህም አልኳቸው፦ “ጥያቄአችሁን ወደ እርሱ እንዳቀርብ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በዚህች ምድር የምትኖሩ ቢሆን እኔ እንደገና አንጻችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፤ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም፤ በእናንተ ላይ ያመጣሁት ጥፋት ታላቅ ሐዘን ሆኖብኛል፤ አሁን እንደምትፈሩት የባቢሎንን ንጉሥ ከእንግዲህ ወዲያ አትፍሩት፤ እኔ ከእናንተ ጋር ስለ ሆንኩ ከእርሱ ኀይል እታደጋችኋለሁ፤ እኔ እራራላችኋለሁ፤ እርሱም እንዲራራላችሁና ወደ አገራችሁ እንዲመልሳችሁ አደርጋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’

ኤርምያስ 42:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የጭፍራ አለቆችም ሁሉ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የሆሻያም ልጅ ያእዛንያ ሕዝቡም ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ቀረቡ፥ ነቢዩንም ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “በዐይኖችህ እንደምታየን ከብዙ ጥቂት ተርፈናልና ልመናችን እባክህ፥ በፊትህ ትድረስ፥ ስለ እኛና ስለዚህ ትሩፍ ሁሉ ለጌታ ለአምላክህ ጸልይ፥ ጌታ አምላክህም የምንሄድበትን መንገድና ማድረግ የሚገባንን ነገር ያሳውቀን ይሆናል።” ነቢዩም ኤርምያስ እንዲህ አላቸው፦ “ሰምቻችኋለሁ፤ እነሆ፥ እንደ ቃላችሁ ወደ ጌታ ወደ አምላካችሁ እጸልያለሁ፤ ጌታም የሚመልስላችሁን ቃል ሁሉ እነግራችኋለሁ፥ ከእናንተም ምንም አልሸሽግም።” እነርሱም ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “ጌታ አምላክህ በአንተ አማካይነት ወደ እኛ የላከውን ቃል ሁሉ ባናደርግ፥ ጌታ በመካከላችን እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁንብን። የአምላካችንን የጌታን ድምፅ በመስማታችን መልካም እንዲሆንልን፥ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን፥ እኛ ወደ እርሱ የምንልክህን የአምላካችንን የጌታን ድምፅ እንሰማለን።” ከዐሥር ቀን በኋላ የጌታ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። ኤርምያስም የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጭፍራ አለቆች ሁሉ፥ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝቡንም ሁሉ ጠራ፥ እንዲህም አላቸው፦ ጸሎታችሁን በፊቱ እንዳቀርብ ወደ እርሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ስላደረግሁባችሁ ክፉ ነገር ተጸጽቻለሁና በዚህች ምድር ብትቀመጡ አንጻችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፥ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም። የምትፈሩትን የባቢሎንን ንጉሥ አትፍሩት፤ እናንተን ለማዳን ከእጁም ለመታደግ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና እርሱን አትፍሩ፥ ይላል ጌታ። እርሱ እንዲምራችሁ ወደ አገራችሁም እንዲመልሳችሁ እኔ እምራችኋለሁ።