ኤርምያስ 10:1-13

ኤርምያስ 10:1-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእስራኤል ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔር የሚላችሁን ስሙ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የአሕዛብን መንገድ አትከተሉ፤ እነርሱ በሰማይ ምልክቶች ይታወካሉ፣ እናንተ ግን በእነዚህ አትረበሹ። የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከጫካ ይቈርጣሉ፤ የእጅ ጥበብ ባለሙያ በመሣሪያው ቅርጽ ያበጅለታል። በብርና በወርቅ ይለብጡታል፤ እንዳይወድቅም፣ በመዶሻ መትተው በምስማር ያጣብቁታል። ጣዖቶቻቸው በኪያር ዕርሻ መካከል እንደ ቆመ ማስፈራርቾ ናቸው፤ የመናገር ችሎታ የላቸውም፤ መራመድም ስለማይችሉ፣ ተሸካሚ ያስፈልጋቸዋል፤ ጕዳት ማድረስም ሆነ፣ መልካምን ነገር ማድረግ ስለማይችሉ፣ አትፍሯቸው።” እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ፤ የስምህም ሥልጣን ታላቅ ነው። የሕዝቦች ሁሉ ንጉሥ ሆይ፤ አንተን የማይፈራ ማነው? ክብር ይገባሃልና። ከምድር ጠቢባን ሁሉ፣ ከመንግሥቶቻቸውም ሁሉ መካከል፣ እንደ አንተ ያለ የለም። ከከንቱ የዕንጨት ጣዖት ትምህርት የሚቀሥሙ ሁሉ፣ ጅሎችና ሞኞች ናቸው። የተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣ ወርቅም ከአፌዝ ይመጣል። የእጅ ጥበብ ባለሙያና አንጥረኛው የሠሯቸው፣ ብልኀተኞችም ያበጇቸው ሁሉ፣ ሰማያዊና ሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፈዋል። እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱ ሕያው አምላክ፣ ዘላለማዊም ንጉሥ ነው፤ በሚቈጣበት ጊዜ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ መንግሥታትም ቍጣውን ሊቋቋሙ አይችሉም። “እናንተም፣ ‘እነዚህ ሰማያትንና ምድርን ያልፈጠሩ አማልክት ከምድር ላይ፣ ከሰማያትም በታች ይጠፋሉ’ ትሏቸዋላችሁ።” እርሱ ግን ምድርን በኀይሉ ፈጠረ፤ ዓለምን በጥበቡ መሠረተ፤ ሰማያትንም በማስተዋሉ ዘረጋ። ድምፁን ባንጐደጐደ ጊዜ በሰማይ ውሆች ይናወጣሉ፤ ጉሙን ከምድር ዳርቻ ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርገዋል፤ መብረቅን ከዝናብ ጋራ ይልካል፤ ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።

ኤርምያስ 10:1-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ስሙ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የአ​ሕ​ዛ​ብን መን​ገድ አት​ማሩ፤ ከሰ​ማይ ምል​ክ​ትም አት​ፍሩ፤ አሕ​ዛብ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ ይፈ​ራ​ሉና። የአ​ሕ​ዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፥ ከዱር በመ​ጥ​ረ​ቢያ እን​ደ​ሚ​ቈ​ረጥ፥ በሠ​ራ​ተ​ኛም እጅ እን​ደ​ሚ​ሠራ እን​ጨት ነው። በብ​ርና በወ​ርቅ ይለ​ብ​ጡ​ታል፤ እን​ዳ​ይ​ና​ወ​ጥም በች​ን​ካ​ርና በመ​ዶሻ ይቸ​ነ​ክ​ሩ​ታል። እንደ ተቀ​ረጸ ብር ናቸው፤ እነ​ር​ሱም አይ​ና​ገ​ሩም፤ መራ​መ​ድም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል። ክፉ መሥ​ራ​ትም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፥ ደግ​ሞም መል​ካም ይሠሩ ዘንድ አይ​ች​ሉ​ምና አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው።” አቤቱ! እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስም​ህም በኀ​ይል ታላቅ ነው። የአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ሆይ! በአ​ሕ​ዛብ ጥበ​በ​ኞች ሁሉ መካ​ከል፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ​ሌለ፥ ለአ​ንተ ክብር ይገ​ባ​ልና አን​ተን የማ​ይ​ፈራ ማን ነው? በአ​ንድ ጊዜ ሰን​ፈ​ዋል፥ ደን​ቍ​ረ​ው​ማል፤ ጣዖ​ታት የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩት የእ​ን​ጨት ነገር ብቻ ነው። የሠ​ራ​ተ​ኛና የአ​ን​ጥ​ረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተ​ር​ሴስ ጥፍ​ጥፍ ብር፥ ከአ​ፌ​ዝም ወርቅ ይመ​ጣል፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም ሰማ​ያ​ዊና ቀይ ግምጃ ነው፤ ሁሉም የብ​ል​ሃ​ተ​ኞች ሥራ ናቸው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ ነው፤ እር​ሱም ሕያው አም​ላ​ክና የዘ​ለ​ዓ​ለም ንጉሥ ነው፤ ከቍ​ጣው የተ​ነሣ ምድር ትን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣ​ለች፤ አሕ​ዛ​ብም መዓ​ቱን አይ​ች​ሉም። እና​ን​ተም፦ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ያል​ፈ​ጠሩ እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ከም​ድር ላይ፥ ከሰ​ማ​ይም በታች ፈጽ​መው ይጥፉ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ። ምድ​ርን በኀ​ይሉ የፈ​ጠረ፥ ዓለ​ሙን በጥ​በቡ ያጸና፥ ሰማ​ያ​ት​ንም በማ​ስ​ተ​ዋሉ የዘ​ረጋ እርሱ ነው። በላይ በሰ​ማይ ውኆ​ችን ይሰ​በ​ስ​ባል፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ደመ​ና​ትን ከፍ ያደ​ር​ጋል፤ ለዝ​ና​ብም መብ​ረ​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ ነፋ​ስ​ንም ከቤተ መዛ​ግ​ብቱ ያወ​ጣል።

ኤርምያስ 10:1-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእስራኤል ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔር የሚላችሁን ስሙ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የአሕዛብን መንገድ አትከተሉ፤ እነርሱ በሰማይ ምልክቶች ይታወካሉ፣ እናንተ ግን በእነዚህ አትረበሹ። የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከጫካ ይቈርጣሉ፤ የእጅ ጥበብ ባለሙያ በመሣሪያው ቅርጽ ያበጅለታል። በብርና በወርቅ ይለብጡታል፤ እንዳይወድቅም፣ በመዶሻ መትተው በምስማር ያጣብቁታል። ጣዖቶቻቸው በኪያር ዕርሻ መካከል እንደ ቆመ ማስፈራርቾ ናቸው፤ የመናገር ችሎታ የላቸውም፤ መራመድም ስለማይችሉ፣ ተሸካሚ ያስፈልጋቸዋል፤ ጕዳት ማድረስም ሆነ፣ መልካምን ነገር ማድረግ ስለማይችሉ፣ አትፍሯቸው።” እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ፤ የስምህም ሥልጣን ታላቅ ነው። የሕዝቦች ሁሉ ንጉሥ ሆይ፤ አንተን የማይፈራ ማነው? ክብር ይገባሃልና። ከምድር ጠቢባን ሁሉ፣ ከመንግሥቶቻቸውም ሁሉ መካከል፣ እንደ አንተ ያለ የለም። ከከንቱ የዕንጨት ጣዖት ትምህርት የሚቀሥሙ ሁሉ፣ ጅሎችና ሞኞች ናቸው። የተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣ ወርቅም ከአፌዝ ይመጣል። የእጅ ጥበብ ባለሙያና አንጥረኛው የሠሯቸው፣ ብልኀተኞችም ያበጇቸው ሁሉ፣ ሰማያዊና ሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፈዋል። እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱ ሕያው አምላክ፣ ዘላለማዊም ንጉሥ ነው፤ በሚቈጣበት ጊዜ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ መንግሥታትም ቍጣውን ሊቋቋሙ አይችሉም። “እናንተም፣ ‘እነዚህ ሰማያትንና ምድርን ያልፈጠሩ አማልክት ከምድር ላይ፣ ከሰማያትም በታች ይጠፋሉ’ ትሏቸዋላችሁ።” እርሱ ግን ምድርን በኀይሉ ፈጠረ፤ ዓለምን በጥበቡ መሠረተ፤ ሰማያትንም በማስተዋሉ ዘረጋ። ድምፁን ባንጐደጐደ ጊዜ በሰማይ ውሆች ይናወጣሉ፤ ጉሙን ከምድር ዳርቻ ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርገዋል፤ መብረቅን ከዝናብ ጋራ ይልካል፤ ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።

ኤርምያስ 10:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የተናገረውን ቃል ስሙ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፥ አሕዛብ ይፈሩታልና። የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፥ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እንጅ በመጥረቢያ ይሠራል። በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል። እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም፥ መራመድም አይቻላቸውምና ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና፥ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው። አቤቱ፥ እንደ አንተ ያለ የለም፥ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው። የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፥ በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለሌለ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው? በአንድ ጊዜ ሰንፈዋል፥ ደንቍረውማል፥ ጣዖታት የሚያስተምሩት የእንጨት ነገር ብቻ ነው። የሠራተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፥ ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው፥ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው። እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፥ እርሱም ሕያው አምላክና የዘላለም ንጉሥ ነው፥ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፥ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም። እናንተም፦ ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ ትሉአቸዋላችሁ። ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው። ድምፁን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይሰበሰባሉ፥ ከምድርም ዳር ደመናትን ከፍ ያደርጋል፥ ለዝናቡም መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።

ኤርምያስ 10:1-13 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እነሆ እግዚአብሔር የሚነግራችሁን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የአሕዛብን አካሄድ አትከተሉ፤ መቼም አሕዛብ ያልተለመደ አዲስ ነገር በሰማይ ባዩ ጊዜ በፍርሃት መንቀጥቀጥ ልማዳቸው ነው፤ እናንተ ግን በዚህ አትሸበሩ። የአሕዛብ ልማዳዊ እምነት ከንቱ ነው፤ ዛፍ ከደን ይቈረጣል፤ አናጢ በመሮ ቅርጽ ያወጣለታል፤ በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፤ እንዳይወድቅም በምስማር ያጠብቁታል። እንደነዚህ ያሉት ምስሎች በዱባ ተክል ውስጥ ለወፍ ማስፈራሪያ እንደሚተከሉ ነገሮች ናቸው፤ መናገር አይችሉም፤ መራመድ ስለማይችሉ ሰዎች ይሸከሙአቸዋል፤ ጒዳት ማድረስም ሆነ ጥቅም ማስገኘት ስለማይችሉ፥ ፈጽሞ አትፍሩአቸው።” እግዚአብሔር ሆይ! አንተን የሚመስል ማንም የለም፤ አንተ ኀያል ነህ፤ ስምህም ታላቅና አስፈሪ ነው። የመንግሥታት ሁሉ ንጉሥ ስለ ሆንክ አንተን የማይፈራ ማን ነው? በአሕዛብ ጠቢባንም ሆነ በንጉሦቻቸው መካከል አንተን የሚመስል ስለሌለ ክብር ይገባሃል። ሁሉም ሞኞችና አላዋቂዎች ሆነው ነው እንጂ ከእንጨት ከተሠሩ ምስሎች ከቶ ምን ትምህርት ማግኘት ይችላሉ? ምስሎቻቸው ከተርሴስ በመጣ ጥሬ ብርና ከኡፋዝ በተገኘ ወርቅ ተለብጠዋል፤ በብልኀተኞችም ሥራ አጊጠዋል፤ ጥበበኞች ሸማኔዎች በሠሩአቸውም የወይን ጠጅና ሐምራዊ ልብስ ተሸፍነዋል። እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን እውነተኛ አምላክ ነህ፤ አንተ ሕያው አምላክ፥ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነህ፤ አንተ በምትቈጣበት ጊዜ ዓለም ይናወጣል፤ የአሕዛብ መንግሥታትም የአንተን ቊጣ ችለው አይቆሙም። “ጣዖቶች ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ መሆናቸውንና አንተ እግዚአብሔር ጣዖቶችን ሁሉ እንደምትደመስስ ንገራቸው” አልከኝ። እግዚአብሔር በኀይሉ ምድርን ሠራ፤ በጥበቡም ዓለምን ፈጠረ፤ በማስተዋሉም ሰማያትን ዘረጋ፤ በእርሱ ትእዛዝ ከሰማይ በላይ ያሉ ውሃዎች የመናወጥ ድምፅ ያሰማሉ፤ እርሱ ደመናዎችን ከምድር ዳርቻ ያመጣል፤ በዝናብ ጊዜም መብረቅ እንዲበርቅ ያደርጋል፤ ነፋስንም ከማከማቻው ይልካል።

ኤርምያስ 10:1-13 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ! ጌታ በእናንተ ላይ የተናገረውን ቃል ስሙ። ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የአሕዛብን መንገድ አትማሩ፥ ከሰማይ ምልክቶችም የተነሣ አትፍሩ፤ አሕዛብ ከእነርሱ የተነሣ ይፈራሉና። የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሞያተኛውም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል። በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል። በዱባ እርሻ (የአትክልት ስፍራ) ውስጥ እንዳለ እንደ ወፍ ማስፈራርያ ዓምድ ናቸው፥ እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም ስለማይችሉ ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራት አይችሉምና፥ ደግሞም መልካም መሥራት በእነርሱ ውስጥ የለምና አትፍሩአቸው።” ጌታ ሆይ! እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው። የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ ሌለ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው? በአንድ ጊዜ ቂላ ቂሎችና ሞኞች ሆነዋል፤ ጣዖታት የሚያስተምሩት ከግዑዝ እንጨት የማይሻልን ነገር ብቻ ነው። የሞያተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፤ ልብሳቸውም ሰማያዊና ሐምራዊ ነው፥ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው። ጌታ ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቁጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን መቋቋም አይችሉም። እናንተም፦ “ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ” ትሉአቸዋላችሁ። ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለምን በጥበቡ የመሠረተ፥ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው። ድምፁን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፥ ከምድርም ዳርቻ ደመናትን ከፍ ያደርጋል፤ ለዝናቡም መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።