ኢሳይያስ 7:14-16
ኢሳይያስ 7:14-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙንም ለመምረጥ ሳያውቅ ቅቤና ማር ይበላል። ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት፥ መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ፥ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት ሀገር ባድማ ትሆናለች።
ኢሳይያስ 7:14-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ሲችል ቅቤና ማር ይበላል። ነገር ግን ሕፃኑ ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ከመቻሉ በፊት የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት ምድር ባድማ ይሆናል።
ኢሳይያስ 7:14-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፥ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ክፉን ለመጥላት መልካሙንም ለመምረጥ ሲያውቅ ቅቤና ማር ይበላል። ሕፃኑም ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች።
ኢሳይያስ 7:14-16 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እንግዲህ እግዚአብሔር ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ‘ዐማኑኤል’ ብላ ትጠራዋለች፤ እርሱም ክፉውን ነገር ትቶ መልካሙን ነገር ለመምረጥ የሚያስችል ዕውቀት በሚያገኝበት ጊዜ ማርና ወተት ይመገባል። ታዲያ፥ ይህ ሕፃን በጎውን ከክፉ ለይቶ ከማወቁ በፊት አንተ ትፈራቸው የነበሩ የእነዚህ የሁለት ነገሥታት ምድሮች ፈራርሰው ባድማ ይሆናሉ።