ኢሳይያስ 50:4-8
ኢሳይያስ 50:4-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የምናገረውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የጥበብ ምላስን ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፤ ለመስማትም ጆሮን ሰጥቶኛል። የጌታ የእግዚአብሔር ተግሣጽም ጆሮዬን ከፍቶአል፤ እኔም ዐመፀኛ አልነበርሁም፤ አልተከራከርሁም። ጀርባዬን ለግርፋት፥ ጕንጬንም ለጽፍዐት ሰጠሁ፤ ፊቴንም ከምራቅ ኀፍረት አልመለስሁም። ጌታ እግዚአብሔር ረዳኝ፤ ስለዚህም አላፈርሁም፤ ፊቴንም እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፤ እንዳላፍርም አውቃለሁ። የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? እስቲ በእኔ ላይ ይነሣ፤ የሚከራከረኝስ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።
ኢሳይያስ 50:4-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ልዑል እግዚአብሔር የተባ አንደበት ሰጥቶኛል፤ ስለዚህ ደካሞችን ብርቱ ለማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ፤ በየማለዳው ያነቃኛል፤ በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል። ልዑል እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶታል፤ እኔም ዐመፀኛ አይደለሁም፤ ወደ ኋላም አላፈገፈግሁም። ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ ጢሜን ለሚነጩ ጕንጬን ሰጠሁ፤ ፊቴን ከውርደት፣ ከጥፋትም አልሰወርሁም። ጌታ እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ አልዋረድም፤ ስለዚህ ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌአለሁ፤ እንደማላፍርም ዐውቃለሁ። ንጹሕ መሆኔን የሚያረጋግጥልኝ በአጠገቤ አለ፤ ታዲያ ማን ሊከስሰኝ ይችላል? እስቲ ፊት ለፊት እንጋጠም! ተቃዋሚዬስ ማን ነው? እስቲ ይምጣ!
ኢሳይያስ 50:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፥ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል። ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶአል፥ እኔም ዓመፀኛ አልነበርሁም ወደ ኋላዬም አልተመለስሁም። ጀርባዬን ለገራፊዎች ጕንጬንም ለጠጕር ነጪዎች ሰጠሁ፥ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም። ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛልና ስለዚህ አልታወክሁም፥ ስለዚህም ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፥ እንዳላፍርም አውቃለሁ። የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፥ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? በአንድነት እንቁም፥ የሚከራከረኝ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።
ኢሳይያስ 50:4-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ደካሞችን በቃል ማጽናትን ዐውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የምሁርን አንደበት ሰጥቶኛል፤ በየማለዳው ከእንቅልፍ ያነቃኛል፤ እንደ ተማሪም አዳምጥ ዘንድ ጆሮዬን ይከፍታል። ጌታ እግዚአብሔር ማስተዋልን ሰጥቶኛል፤ እኔም ዐመፀኛ ሆኜ ከእርሱ አልራቅሁም። ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፥ ጢሜንም ለሚነጩ ጒንጬን ሰጠኋቸው፤ ከሚሰድቡኝና ከሚተፉብኝ ፊቴን አላዞርኩም። ጌታ እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ አልተዋረድኩም፤ ራሴን እንደ ጠንካራ ድንጋይ አበረታሁ፤ እንደማላፍርም ዐውቃለሁ። የሚፈርድልኝ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤ ታዲያ ማን ይከሰኛል? የሚከሰኝ ካለ ፊት ለፊት እንገናኝ፤ እስቲ ይቋቋመኝ።
ኢሳይያስ 50:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ እንዳውቅ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም እንድትሰማ ጆሮዬን ያነቃቃል። ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶአል፥ እኔም ዓመፀኛ አልነበርሁም ወደ ኋላዬም አልተመለስሁም። ጀርባዬን ለገራፊዎች፥ ጉንጬንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠሁ፤ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም። ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛልና አልታወክሁም፤ ስለዚህም ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፥ ኀፍረት ላይ እንደማልወድቅም አውቃለሁ። የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? በአንድነት እንቁም፤ የሚከራከረኝ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።