ኢሳይያስ 49:15-17
ኢሳይያስ 49:15-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“በውኑ ሴት፥ ልጅዋን ትረሳለችን? ከማኅፀንዋ ለተወለደውስ አትራራምን? ሴት ይህን ብትረሳ፥ እኔ አንቺን አልረሳሽም። እነሆ፥ እኔ በእጄ ግንቦችሽን ሣልሁ፤ አንቺም ሁልጊዜ በፊቴ ነሽ። ከአፈረሱሽ በኋላ ፈጥነሽ ትታነጺያለሽ፤ ያፈረሱሽ ከአንቺ ይወጣሉ።
ኢሳይያስ 49:15-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን? ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን? ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም! እነሆ፤ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ፤ ቅጥሮችሽ ምን ጊዜም በፊቴ ናቸው። ወንዶች ልጆችሽ ፈጥነው ይመለሳሉ፤ ያፈራረሱሽም ከአንቺ ይሸሻሉ።
ኢሳይያስ 49:15-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። እነሆ፥ እኔ በእጄ መጻፍ ቀርጬሻለሁ፥ ቅጥሮችሽም ሁል ጊዜ በፊቴ አሉ። ልጆችሽ ይፈጥናሉ፥ ያፈረሱሽና ያወደሙሽ ከአንቺ ዘንድ ይወጣሉ።