የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 40:12-25

ኢሳይያስ 40:12-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ውኆ​ችን በእ​ፍኙ የሰ​ፈረ፥ ሰማ​ይ​ንም በስ​ን​ዝሩ የለካ፥ ምድ​ር​ንም ሁሉ ሰብ​ስቦ በእጁ የያዘ፥ ተራ​ሮ​ችን በሚ​ዛን፥ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም በሚ​ዛ​ኖች የመ​ዘነ ማን ነው? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕሊና ያወቀ ወይስ አማ​ካሪ ሆኖ ያማ​ከ​ረው ማን ነው? ወይስ ከማን ጋር ተመ​ካ​ከረ? ወይስ ማን መከ​ረው? ፍር​ድ​ንስ ማን አስ​ተ​ማ​ረው? የጥ​በ​ብ​ንስ መን​ገድ ማን አሳ​የው? እነሆ፥ አሕ​ዛብ በገ​ንቦ እን​ዳ​ለች ጠብታ ናቸው፤ እንደ ሚዛ​ንም ውል​ብ​ል​ቢት ተቈ​ጥ​ረ​ዋል፤ እንደ ኢም​ን​ትም ናቸው። ሊባ​ኖስ ለማ​ን​ደጃ እን​ስ​ሶ​ች​ዋም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አይ​በ​ቁም። አሕ​ዛብ ሁሉ በፊቱ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ናቸው፤ እንደ ከንቱ ነገ​ርም ይመ​ስ​ላሉ። እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በማን ትመ​ስ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስ​ተ​ያ​ዩ​ታ​ላ​ችሁ? እን​ጨት ጠራቢ በሠ​ራው ምስል፥ ወይስ አን​ጥ​ረኛ መትቶ በሠ​ራው ወርቅ፥ በወ​ር​ቅም ለብጦ በሠ​ራው ምስል ትመ​ስ​ሉ​ታ​ላ​ች​ሁን? ጠራ​ቢው የማ​ይ​ነ​ቅ​ዘ​ውን እን​ጨት ይመ​ር​ጣል፤ ምስ​ሉም እን​ዳ​ይ​ና​ወጥ ያቆ​መው ዘንድ ብልህ ሠራ​ተ​ኛን ይፈ​ል​ጋል። አላ​ወ​ቃ​ች​ሁ​ምን? ወይስ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምን? ከጥ​ን​ትስ አል​ተ​ወ​ራ​ላ​ች​ሁ​ምን? ወይስ ምድር ከተ​መ​ሠ​ረ​ተች ጀምሮ አላ​ስ​ተ​ዋ​ላ​ች​ሁ​ምን? እርሱ የም​ድ​ርን ክበብ ያጸ​ናል፤ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖ​ሩት እንደ አን​በጣ ናቸው፤ ሰማ​ያ​ትን እንደ መጋ​ረጃ የሚ​ዘ​ረ​ጋ​ቸው፥ እንደ ድን​ኳ​ንም ለመ​ኖ​ሪያ የሚ​ዘ​ረ​ጋ​ቸው፤ አለ​ቆ​ች​ንም የሚ​ገ​ዛ​ላ​ቸው እን​ዳ​ይ​ኖር የሚ​ያ​ደ​ርግ ምድ​ር​ንም እንደ ኢም​ንት የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት እርሱ ነው። በእ​ር​ሱም ላይ ዛፉ​ንና ሣሩን፥ የማ​ይ​ቈ​ጠር ሌላ​ው​ንም ብዙ ፍጥ​ረት የፈ​ጠረ እርሱ ነው። ነፋ​ስም በነ​ፈ​ሰ​ባ​ቸው ጊዜ ይደ​ር​ቃሉ፤ ዐውሎ ነፋ​ስም እንደ ገለባ ይጠ​ር​ጋ​ቸ​ዋል። እን​ግ​ዲህ እተ​ካ​ከ​ለው ዘንድ በማን መሰ​ላ​ች​ሁኝ? ይላል ቅዱሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ኢሳይያስ 40:12-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ውሆችን በዕፍኙ የሰፈረ፣ ሰማያትን በስንዝሩ የለካ፣ የምድርን ዐፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛን፣ ኰረብቶችንም በመድሎት የመዘነ ማነው? የእግዚአብሔርን መንፈስ የተረዳ፣ አማካሪውስ ሆኖ ያስተማረው ማነው? ዕውቀት ለማግኘት እግዚአብሔር ማንን አማከረ? ትክክለኛውንስ መንገድ ማን አስተማረው? ዕውቀትን ያስተማረው፣ የማስተዋልንም መንገድ ያሳየው ማን ነበር? እነሆ፤ አሕዛብ በገንቦ ውስጥ እንዳለች ጠብታ ናቸው፤ በሚዛን ላይ እንዳለ ትቢያ ይቈጠራሉ፤ ደሴቶችንም እንደ ደቃቅ ዐፈር ይመዝናቸዋል። ሊባኖስ ለመሠዊያ እሳት አትበቃም፤ የእንስሶቿም ቍጥር ለሚቃጠል መሥዋዕት ያንሳል። አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንደ ኢምንት ናቸው፤ ከምንም የማይቈጠሩ መና ናቸው። እንግዲህ፣ እግዚአብሔርን ከማን ጋር ታወዳድሩታላችሁ? ከየትኛውስ ምስል ጋር ታነጻጽሩታላችሁ? የተቀረጸውንማ ምስል ባለ እጅ ይቀርጸዋል፤ ወርቅ አንጥረኛም በወርቅ ይለብጠዋል፤ የብር ሰንሰለትም ያበጅለታል። እንዲህ ያለውን መባ ማቅረብ የማይችል ምስኪን ድኻ፣ የማይነቅዝ ዕንጨት ይመርጣል፤ የማይወድቅ ምስልን ለማቆምም፣ ታዋቂ ባለሙያ ይፈልጋል። አላወቃችሁምን? አልሰማችሁምን? ከጥንት አልተነገራችሁምን? ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን? እርሱ ከምድር ክበብ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ ሕዝቦቿም እንደ አንበጣ ናቸው። ሰማያትን እንደ ድባብ ይዘረጋቸዋል፤ እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይተክላቸዋል። አለቆችን ኢምንት፣ የዚህን ዓለም ገዦች እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል። ተተክለው ምንም ያህል ሳይቈዩ፣ ተዘርተው ምንም ያህል ሳይሰነብቱ፣ ገና ሥር መስደድ ሳይጀምሩ አነፈሰባቸው፤ እነርሱም ደረቁ፤ ዐውሎ ነፋስም እንደ ገለባ ጠራርጎ ወሰዳቸው። ቅዱሱ፣ “ከማን ጋር ታወዳድሩኛላችሁ? የሚስተካከለኝስ ማን አለ?” ይላል።

ኢሳይያስ 40:12-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው? የእግዚአብሔርም መንፈስ ያዘዘ፥ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያስተማረው ማን ነው? ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍርድንም መንገድ ማን አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው? እነሆ፥ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፥ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፥ እነሆ፥ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል። ሊባኖስ ለማንደጃ እንስሶችዋም ለሚቃጠል መሥዋዕት አይበቁም። አህዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፥ ከምናምን እንደሚያንሱ፥ እንደ ከንቱ ነገርም ይቈጥራቸዋል። እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ? የተቀረጸውንስ ምስል ሠራተኛ ሠርቶታል፥ አንጥረኛም በወርቅ ለብጦታል፥ የብሩንም ሰንሰለት አፍስሶለታል። ለዚህ መባዕ ገንዘቡ ያልበቃው ድሀ የማይነቅዘውን እንጨት ይመርጣል፥ ምስሉም እንዳይናወጥ ያቆመው ዘንድ ብልህ ሠራተኛን ይፈልጋል። አላወቃችሁምን? ወይስ አልሰማችሁምን? ከጥንትስ አልተወራላችሁምን? ወይስ ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን? እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፥ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥ አለቆችንም እንዳልነበሩ፥ የምድርንም ፈራጆች እንደ ከንቱ ነገር የሚያደርጋቸው እርሱ ነው። ገና እንደ ተተከሉና እንደ ተዘሩ፥ በምድርም ሥር ገና እንደ ሰደዱ ወዲያውኑ ነፈሰባቸው፥ እነርሱም ደረቁ፥ ዐውሎ ነፋስም እንደ እብቅ ጠረጋቸው። እንግዲህ እተካከላለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ።

ኢሳይያስ 40:12-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ውቅያኖስን በእፍኙ፥ ሰማይንም በስንዝሩ፥ የምድርን ዐፈር በቊና መለካት የሚችል ማን ነው? ተራራዎችንና ኰረብቶችንስ በሚዛን የሚመዝን ማን ነው? እግዚአብሔርን “እንዲህ አድርግ” ብሎ የሚያዘው ማን ነው? እርሱን ማስተማርና መምከር የሚችልስ ማን ነው? ያብራራለት ዘንድ እግዚአብሔር ማንን አማከረ? ትክክለኛውን ፍርድ ያስተማረው ማነው? ዕውቀትን ያስተማረው፥ ወይም ትክክለኛውን መንገድ እንዲያስተውል ያደረገው ማነው? በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቦች እንደ አንድ የውሃ ጠብታ ናቸው፤ በሚዛንም ላይ እንዳለ ዐቧራ ናቸው፤ ደሴቶችም በእርሱ ዘንድ እንደ ትቢያ የቀለሉ ናቸው። በሊባኖስ የሚገኙ እንስሳት ሁሉ ለአምላካችን የሚቃጠል መሥዋዕት ለመሆን፥ ከሚፈለገው ቊጥር ያነሱ ናቸው። ዛፎቹም ሁሉ የመሥዋዕቱን እሳት ለማቀጣጠል አይበቁም። በእግዚአብሔር ዘንድ ሕዝቦች ሁሉ እንዳሉ የሚቈጠሩ አይደሉም። እነርሱ በእርሱ ዘንድ እንደ ኢምንት የሚቈጠሩና ዋጋ የሌላቸው ናቸው። እግዚአብሔርን ከማን ጋር ታነጻጽሩታላችሁ? ከማንስ ጋር ታመሳስሉታላችሁ? እርሱ እኮ እንጨት ጠራቢ እንደሚቀርጸው፥ አንጥረኛም በወርቅ እንደሚለብጠው በብር ሠርቶ እንደሚያቆመው ጣዖት ዐይነት አይደለም። ሀብት የሌለው ድኻ ለመባው በማይነቅዝ ልዩ እንጨት ይመርጥና በግንባሩ እንዳይደፋ ብልኀተኛ አስተካክሎ እንዲሠራው ያደርጋል። ከቶ ይህን አታውቁምን? አልሰማችሁምን? ከመጀመሪያው ጀምሮ አልተነገራችሁምን? ምድር ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ አላስተዋላችሁምን? እግዚአብሔር ከምድር ክበብ በላይ ዙፋኑን ዘርግቶ መቀመጡን ሰማይን እንደ መጋረጃ መወጠሩንና፥ እንደ መኖሪያ ድንኳን መዘርጋቱን የምድርም ሕዝቦች እንደ ፌንጣ አነስተኞች መሆናቸውን። እርሱ ልዑላንን ያዋርዳል፤ የዚህ ዓለም ገዢዎችንም እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል። እነርሱ ገና እንደ በቀለና ሥር እንዳልሰደደ አዲስ ተክል ናቸው፤ እግዚአብሔር ነፋሱን ሲልክ ወዲያውኑ ይደርቃሉ፤ እንደ ገለባም በነው ይጠፋሉ። “ታዲያ፥ እኔን ከማን ጋር ታነጻጽሩኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታመሳስሉኛላችሁ?” ይላል ቅዱስ እግዚአብሔር።

ኢሳይያስ 40:12-25 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው? የጌታን መንፈስ ያዘዘ፥ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያስተማረው ማን ነው? ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍትህንም መንገድ ማን አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው? እነሆ፥ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፥ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ እነሆ፥ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል። ሊባኖስ ለማንደጃ እንስሶችዋም ለሚቃጠል መሥዋዕት አይበቁም። አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፤ ከምንም እንደሚያንሱ፥ እንደ ባዶ ነገር ይቈጠራሉ። እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ? የተቀረጸውንስ ምስል ሠራተኛ ሠርቶታል፥ አንጥረኛም በወርቅ ለብጦታል፥ የብሩንም ሰንሰለት ቅርጽ እንዲሰጥ አፍስሶለታል። ለዚህ መባዕ ገንዘቡ ያልበቃው ድሀ የማይነቅዘውን እንጨት ይመርጣል፤ ምስሉም እንዳይናወጥ ያቆመው ዘንድ ብልህ ሠራተኛን ይፈልጋል። አላወቃችሁም? ወይስ አልሰማችሁ ይሆን? ከጥንትስ አልተወራላችሁም? ወይስ ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁም? እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርሷም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥ መስፍኖችንም እንዳልነበሩ፥ የምድርንም ፈራጆች እንደ ከንቱ ነገር የሚያደርጋቸው እርሱ ነው። ገና እንደ ተተከሉና እንደ ተዘሩ፥ በምድርም ሥር ገና እንደ ሰደዱ ወዲያውኑ ነፈሰባቸው፥ እነርሱም ደረቁ፥ ዐውሎ ነፋስም እንደ እብቅ ጠረጋቸው። እንግዲህ የሚስተካከለኝ ማን አለ? ከማንስ ጋር አመሳሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ።