ዕብራውያን 10:26-39

ዕብራውያን 10:26-39 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእውነትን ዕውቀት ከተቀበልን በኋላ ሆነ ብለን በኀጢአት ጸንተን ብንመላለስ፣ ከእንግዲህ ለኀጢአት የሚሆን ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤ የሚቀረው ግን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚበላ ብርቱ እሳት መጠበቅ ብቻ ነው። የሙሴን ሕግ የናቀ ማንኛውም ሰው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ከመሰከሩበት ያለ ምሕረት ይገደል ነበር። ታዲያ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፣ የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ተራ ነገር የቈጠረ፣ የጸጋንም መንፈስ ያክፋፋ እንደ ምን ያለ የባሰ ቅጣት ይገባው ይመስላችኋል? “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቀዋለንና፤ ደግሞም፣ “ጌታ በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል። በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ እጅግ የሚያስፈራ ነው። ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ፣ በመከራ ውስጥ በብርቱ ተጋድሎ ጸንታችሁ የቆማችሁበትን የቀድሞውን ዘመን አስቡ። አንዳንድ ጊዜ በአደባባይ ለስድብና ለስደት ተጋልጣችሁ ነበር፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደዚህ ያለ መከራ ከደረሰባቸው ሰዎች ጋራ ዐብራችሁ መከራን ተቀብላችኋል። እናንተ ራሳችሁ የተሻለና ለዘወትር የሚኖር ሀብት ያላችሁ መሆናችሁን ስለምታውቁ ለታሰሩት ራራችሁ፤ ንብረታችሁም ሲዘረፍ በደስታ ተቀበላችሁ። ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጽማችሁ የተስፋ ቃሉን እንድትቀበሉ፣ ጸንታችሁ መቆም ያስፈልጋችኋል። ምክንያቱም “ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ የሚመጣው እርሱ ይመጣል፤ አይዘገይም። ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል፤ ወደ ኋላ ቢያፈገፍግ፣ ነፍሴ በርሱ ደስ አትሰኝም።” እኛ ግን አምነው ከሚድኑት ወገን እንጂ፣ ወደ ኋላ አፈግፍገው ከሚጠፉት አይደለንም።

ዕብራውያን 10:26-39 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥ የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ። የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት ቢመሰክሩበት ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል? በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ያለውን እናውቃለንና፤ ደግሞም፦ ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል። በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው። ነገር ግን ግማሽ በነቀፋና በጭንቅ እንደ መጫወቻ ስለ ሆናችሁ ግማሽም እንዲህ ካሉት ጋር ስለ ተካፈላችሁ፥ ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ መከራ በሆነበት በትልቅ ተጋድሎ የጸናችሁበትን የቀደመውን ዘመን አስቡ። የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና። ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም፤ ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም። እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም።

ዕብራውያን 10:26-39 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እው​ነ​ትን ካወ​ቅ​ናት በኋላ፥ ተጋ​ፍ​ተን ብን​በ​ድል ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አይ​ኖ​ርም። ነገር ግን የሚ​ያ​ስ​ፈራ ፍርድ ከሓ​ዲ​ዎ​ች​ንም የሚ​በ​ላ​ቸው የቅ​ናት እሳት ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል። ከሙሴ ሕግ የተ​ላ​ለፈ ቢኖር ሁለት፥ ወይም ሦስት ምስ​ክ​ሮች ከመ​ሰ​ከ​ሩ​በት ያለ ምሕ​ረት ይሞ​ታል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ የከዳ፥ ያን​ንም የተ​ቀ​ደ​ሰ​በ​ትን የኪ​ዳ​ኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቈ​ጠረ፥ የጸ​ጋ​ው​ንም መን​ፈስ ያክ​ፋፋ እን​ዴት ይልቅ የሚ​ብስ ቅጣት የሚ​ገ​ባው ይመ​ስ​ላ​ች​ኋል? “እኔ እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ እኔም ብድ​ራ​ትን እመ​ል​ሳ​ለሁ፥” ያለ​ውን እና​ው​ቀ​ዋ​ለ​ንና፤ ዳግ​መ​ኛም “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ይፈ​ር​ዳል።” በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ እጅግ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ነው። እና​ንተ የተ​ጠ​መ​ቃ​ች​ሁ​በ​ት​ንና ብዙ መከራ የታ​ገ​ሣ​ች​ሁ​በ​ትን የቀ​ደ​መ​ውን ዘመን አስቡ፤ እና​ንተ ተሰ​ድ​ባ​ችሁ ነበር፤ መከ​ራም አጽ​ን​ተ​ው​ባ​ችሁ ነበር፤ ተዘ​ባ​ብ​ተ​ው​ባ​ች​ሁም ነበር፤ በዚ​ህም መን​ገድ እን​ዲህ ከሆ​ኑት ጋር ተባ​ብ​ራ​ችሁ ነበር። በእ​ስ​ራ​ቴም ጊዜ ከእኔ ጋር በመ​ከራ ተባ​ብ​ራ​ች​ኋል፤ የገ​ን​ዘ​ባ​ች​ሁ​ንም መዘ​ረፍ በደ​ስታ ተቀ​ብ​ላ​ች​ኋል፤ በሰ​ማ​ያት ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ከዚህ የሚ​በ​ል​ጥና የተ​ሻለ ገን​ዘብ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና። ትል​ቁን ዋጋ​ች​ሁን የም​ታ​ገ​ኙ​ባ​ትን መታ​መ​ና​ች​ሁን አት​ጣሉ። ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ አድ​ር​ጋ​ችሁ የተ​ሰ​ጣ​ች​ሁን ተስፋ ታገኙ ዘንድ መታ​ገሥ ያስ​ፈ​ል​ጋ​ች​ኋል። “ገና ጥቂት ቀን አለና፤ የሚ​መ​ጣ​ውም ፈጥኖ ይደ​ር​ሳል፥ አይ​ዘ​ገ​ይ​ምም። ጻድቅ በእ​ም​ነት ይድ​ናል፤ ወደ​ኋላ ቢመ​ለስ ግን ልቡ​ናዬ በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ትም።” እኛ ግን ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ሊያ​ድኑ ከሚ​ያ​ም​ኑት ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚ​ያ​ፈ​ገ​ፍ​ጉት አይ​ደ​ለ​ንም።

ዕብራውያን 10:26-39 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእውነትን ዕውቀት ከተቀበልን በኋላ ሆነ ብለን በኀጢአት ጸንተን ብንመላለስ፣ ከእንግዲህ ለኀጢአት የሚሆን ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤ የሚቀረው ግን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚበላ ብርቱ እሳት መጠበቅ ብቻ ነው። የሙሴን ሕግ የናቀ ማንኛውም ሰው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ከመሰከሩበት ያለ ምሕረት ይገደል ነበር። ታዲያ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፣ የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ተራ ነገር የቈጠረ፣ የጸጋንም መንፈስ ያክፋፋ እንደ ምን ያለ የባሰ ቅጣት ይገባው ይመስላችኋል? “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቀዋለንና፤ ደግሞም፣ “ጌታ በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል። በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ እጅግ የሚያስፈራ ነው። ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ፣ በመከራ ውስጥ በብርቱ ተጋድሎ ጸንታችሁ የቆማችሁበትን የቀድሞውን ዘመን አስቡ። አንዳንድ ጊዜ በአደባባይ ለስድብና ለስደት ተጋልጣችሁ ነበር፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደዚህ ያለ መከራ ከደረሰባቸው ሰዎች ጋራ ዐብራችሁ መከራን ተቀብላችኋል። እናንተ ራሳችሁ የተሻለና ለዘወትር የሚኖር ሀብት ያላችሁ መሆናችሁን ስለምታውቁ ለታሰሩት ራራችሁ፤ ንብረታችሁም ሲዘረፍ በደስታ ተቀበላችሁ። ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጽማችሁ የተስፋ ቃሉን እንድትቀበሉ፣ ጸንታችሁ መቆም ያስፈልጋችኋል። ምክንያቱም “ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ የሚመጣው እርሱ ይመጣል፤ አይዘገይም። ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል፤ ወደ ኋላ ቢያፈገፍግ፣ ነፍሴ በርሱ ደስ አትሰኝም።” እኛ ግን አምነው ከሚድኑት ወገን እንጂ፣ ወደ ኋላ አፈግፍገው ከሚጠፉት አይደለንም።

ዕብራውያን 10:26-39 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥ የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ። የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት ቢመሰክሩበት ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል? በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ያለውን እናውቃለንና፤ ደግሞም፦ ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል። በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው። ነገር ግን ግማሽ በነቀፋና በጭንቅ እንደ መጫወቻ ስለ ሆናችሁ ግማሽም እንዲህ ካሉት ጋር ስለ ተካፈላችሁ፥ ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ መከራ በሆነበት በትልቅ ተጋድሎ የጸናችሁበትን የቀደመውን ዘመን አስቡ። የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና። ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም፤ ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም። እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም።

ዕብራውያን 10:26-39 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እውነትን ካወቅን በኋላ ሆን ብለን ኃጢአት ብንሠራ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት የሚቀርብ ምንም መሥዋዕት አይኖረንም። አሁን የሚቀረው ግን ወደ ፊት የሚሆነው አስፈሪ ፍርድና ተቃዋሚዎችን የሚያቃጥል አስፈሪ እሳት ነው። የሙሴን ሕግ የጣሰ ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ከመሰከሩበት ያለ ምሕረት በሞት ይቀጣል። ታዲያ፥ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፥ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳን ደም ያረከሰ፥ የጸጋን መንፈስ የሰደበ፥ እንዴት ያለ የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል! “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ተገቢ ዋጋን እከፍላለሁ” ያለው ማን መሆኑን እናውቃለን፤ እንዲሁም “እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል ጌታ። ስለዚህ በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ እጅግ የሚያስፈራ ነው። ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ ብዙ መከራ ተቀብላችሁ የታገሣችሁባቸውን እነዚያን የቀድሞዎቹን ቀኖች አስታውሱ። አንዳንድ ጊዜ በሰው ፊት ተሰድባችኋል፤ ተንገላታችኋል፤ አንዳንድ ጊዜም ይህ ዐይነት ሥቃይ ከደረሰባቸው ሰዎች ጋር ጓደኞች በመሆናችሁ መከራ ተቀብላችኋል። እናንተ የተሻለና ነዋሪ ሀብት በሰማይ እንዳላችሁ በማወቃችሁ ለእስረኞች ራራችሁላቸው፤ ንብረታችሁም ሲወሰድባችሁ ታግሣችሁ ሁኔታውን በደስታ ተቀበላችሁ። እንግዲህ፥ ታላቅ ሽልማት የምታገኙበትን መተማመኛችሁን አትጣሉት። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጽማችሁ እግዚአብሔር ሊሰጣችሁ ቃል የገባላችሁን ነገር ለማግኘት በትዕግሥት መጠበቅ ያስፈልጋችኋል። ለዚህም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ “ያ የሚመጣው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ይመጣል፤ አይዘገይምም፤ የእኔ የሆነ ጻድቁ ሰው ግን በእምነት ሕይወትን ያገኛል፤ ወደ ኋላው ቢያፈገፍግ ግን እኔ በእርሱ አልደሰትም።” እኛ ግን አምነው ከሚድኑት ወገን ነን እንጂ ወደ ኋላ አፈግፍገው ከሚጠፉት ሰዎች ወገን አይደለንም።

ዕብራውያን 10:26-39 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርብልንም፤ ነገር ግን የሚያስፈራ የፍርድና ተቃዋሚዎችንም ለመብላት የሚጠብቅ የእሳት ግለት አለ። የሙሴን ሕግ የተላለፈ ሰው “በሁለት እና በሦስት ምስክሮች ምስክርነት” ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤ እንግዲህ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፥ የተቀደሰበትን ያንን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቆጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያስቆጣ፥ ቅጣቱ እጅግ የከፋ እንዴት የማይሆን ይመስላችኋል? “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፤” ያለውን እናውቃለን፤ ደግሞም “ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል።” በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው። ነገር ግን ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ በትልቅ ተጋድሎ የጸናችሁባቸውን እነዚያን የመከራ ቀናት አስታውሱ፤ አንዳንድ ጊዜ በግላጭ ለነቀፋና ለስደት የተዳረጋችሁ ነበራችሁ፤ አንዳንዴም እንዲህ ካሉት ጋር በሚደርስባቸው ነገር ተካፋይ ሆናችሁ ነበር፤ በሰማይ የበለጠና ፍጻሜ የሌለው ሀብት እንዳላችሁ በማወቃችሁ፥ የንብረታችሁን መነጠቅ በደስታ ተቀበላችሁ፤ በእስራት ላይ የነበሩትን የስቃያቸው ተካፋይ ሆናችሁ። ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ ጽናት ያስፈልጋችኋል። ምክንያቱም ገና “በጣም ጥቂት ጊዜ፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል፥ አይዘገይምም፤ ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል፤ ነፍሴ ወደ ኋላም በሚያፈገፍግ በእርሱ ደስ አትሰኝም።” እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑት ጋር ነን እንጂ፥ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ ጋር አይደለንም።