ዘፍጥረት 48:8-19

ዘፍጥረት 48:8-19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እስ​ራ​ኤ​ልም የዮ​ሴ​ፍን ልጆች ለይቶ፥ “እነ​ዚህ ምኖ​ችህ ናቸው?” አለው። ዮሴ​ፍም ለአ​ባቱ ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ የሰ​ጠኝ ልጆች ናቸው” አለው። ያዕ​ቆ​ብም፥ “እባ​ር​ካ​ቸው ዘንድ ወደ እኔ አቅ​ር​ብ​ልኝ” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዐይ​ኖች ከሽ​ም​ግ​ልና የተ​ነሣ ከብ​ደው ነበር፤ ማየ​ትም አይ​ች​ልም ነበር፤ ወደ እር​ሱም አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ ሳማ​ቸ​ውም፤ አቀ​ፋ​ቸ​ውም። እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ከፊ​ትህ አል​ተ​ለ​የ​ሁም፤ እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘር​ህን ደግሞ አሳ​የኝ” አለው። ዮሴ​ፍም ከጕ​ል​በቱ ፈቀቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ወደ ምድ​ርም በግ​ን​ባሩ ሰገደ። ዮሴ​ፍም ሁለ​ቱን ልጆ​ቹን ወሰደ፤ ኤፍ​ሬ​ም​ንም በቀኙ በእ​ስ​ራ​ኤል ግራ፥ ምና​ሴ​ንም በግ​ራው በእ​ስ​ራ​ኤል ቀኝ አቆ​ማ​ቸው፤ ወደ አባ​ቱም አቀ​ረ​ባ​ቸው። እስ​ራ​ኤ​ልም ቀኝ እጁን ዘር​ግቶ በኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ አኖ​ረው፤ እር​ሱም ታናሽ ነበረ፤ ግራ​ው​ንም በም​ናሴ ራስ ላይ አኖረ፤ እጆ​ቹ​ንም አስ​ተ​ላ​ለፈ። ያዕ​ቆ​ብም ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አባ​ቶች አብ​ር​ሃ​ምና ይስ​ሐቅ በፊቱ ደስ ያሰ​ኙት እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከታ​ና​ሽ​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመ​ገ​በኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤” ዮሴ​ፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ ጭኖ በአየ ጊዜ ከባድ ነገር ሆነ​በት፤ ዮሴ​ፍም የአ​ባ​ቱን እጅ በም​ናሴ ራስ ላይ ይጭ​ነው ዘንድ ከኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ አነ​ሣው። ዮሴ​ፍም አባ​ቱን፥ “አባቴ ሆይ፥ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝ​ህን በራሱ ላይ አድ​ርግ” አለው። አባ​ቱም እንቢ አለ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አው​ቃ​ለሁ ልጄ ሆይ፥ አው​ቃ​ለሁ፤ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆ​ናል፤ ታላ​ቅም ይሆ​ናል፤ ነገር ግን ታናሽ ወን​ድሙ ከእ​ርሱ ይበ​ል​ጣል፤ ዘሩም ብዙ ሕዝብ ይሆ​ናል።”

ዘፍጥረት 48:8-19 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እስራኤልም የዮሴፍን ልጆች ባየ ጊዜ፣ “እነዚህ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀ። ዮሴፍም፣ “እነዚህ እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ብሎ ለአባቱ መለሰለት። እስራኤልም፣ “አቅርባቸውና ልመርቃቸው” አለ። በዚህ ጊዜ እስራኤል ዐይኖቹ በእርጅና ምክንያት በመድከማቸው አጥርቶ ማየት ይሳነው ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን አባቱ ዘንድ አቀረባቸው፤ አባቱም ስሞ ዐቀፋቸው። እስራኤልም ዮሴፍን፣ “ዐይንህን እንደ ገና አያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ልጆችህን ጭምር ለማየት አበቃኝ” አለው። ዮሴፍም ልጆቹን ከእስራኤል ጕልበት ፈቀቅ በማድረግ አጐንብሶ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ። ከዚያም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ኤፍሬምን ከራሱ በስተቀኝ፣ ከእስራኤል በስተግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተግራ፣ ከእስራኤል በስተቀኝ በኩል አቀረባቸው። እስራኤል ግን ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረ፤ ግራ እጁንም በቀኝ እጁ ላይ አስተላልፎ በበኵሩ በምናሴ ራስ ላይ አኖረ። ከዚህ በኋላ ዮሴፍን ባረከ፤ እንዲህም አለው፤ “አባቶቼ አብርሃምና ይሥሐቅ በፊቱ የተመላለሱት እግዚአብሔር፣ ለእኔም እስከ ዛሬ ድረስ በዘመኔ ሁሉ እረኛ የሆነኝ አምላክ፣ ከጕዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይሥሐቅ ስም ይጠሩ፤ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።” ዮሴፍ፣ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማድረጉን ሲያይ ተከፋ፤ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንሥቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤ ዮሴፍም፣ “አባቴ ሆይ፤ እንዲህ አይደለም፤ በኵሩ ይህኛው ስለ ሆነ፣ ቀኝ እጅህን እርሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው። አባቱ ግን፣ “ዐውቃለሁ፤ ልጄ ዐውቃለሁ፤ እርሱም እኮ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ይሁን እንጂ ታናሽ ወንድሙ ከርሱ ይበልጣል፤ ዘሮቹም ታላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” ብሎ እንቢ አለው።

ዘፍጥረት 48:8-19 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እስራኤልም የዮሴፍን ልጆችን አይቶ፦ እነዚህ እነማን ናችው? አለው። ዮሴፍም ለአባቱ፦ እግዚአብሔር በዚህ የሰጠኝ ልጆቼ ናቸው አለ። እርሱም፦ እባርካቸው ዘንድ ወደዚህ አቅርብልኝ አለ። የእስራኤልም ዓይኖች ከሸምግልና የተነሣ ከብደው ነበር። ማየትም አይችልም ነበር ወደ እርሱም አቀረባቸው ሳማቸውም አቀፋቸውም። እስራኤልም ዮሴፍን፦ ፊትህን አያለሁ ብዬ አላሰብሁም ነበር እነሆም እግዚአብሔር ዘርህን ደግሞ አሳየኝ አለው። ዮሴፍም ከጕልበቱ ፈቀቅ አደረጋቸው ወደ ምድርም በግምባሩ ሰገደ። ዮሴፍም ሁለቱን ልጆቹን ወሰደ ኤፍሬምንም በቀኙ በእስራኤል ቀኝ አደረገው ወደ እርሱም አቀረባቸው። እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው እርሱም ታናሽ ነበረ ግራውንም በምናሴ ራስ ላይ አኖረ እጆቹንም አስተላለፈ፥ ምናሴ ራስ ላይ አኖረ፤ እጆቹንም አስተላለፈ ምናሴ በኵር ነበርና ያዕቆብም ዮሴፍን ባረከው እንዲህም አለ፦ አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ ዛሬ ድርስ እኔን የመገባኝ እግዚአብሔር ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር ከክፋ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምን የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ በምድርም መካከል ይብዙ። ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ጭኖ ባየ ጊዜ አሳዘነው የአባቱንም እጅ በምናሴ ራስ ላይ ይጭነው ዘንድ ከኤፍሬም ራስ ላይ አነሣው። ዮሴፍም አባቱን፦ አባቴ ሆይ እንዲህ አይደለም፥ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝህን በራሱ ላይ አድርግ አለው። አባቱም እንቢ አለ እንዲህ ሲል፦ አወቅሁ ልጄ ሆይ አወቅሁ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል ታላቅም ይሆናል ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል ዘሩም የአሕዛብ ሙላት ይሆናል።

ዘፍጥረት 48:8-19 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች ባየ ጊዜ “እነዚህ ልጆች እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀ። ዮሴፍም “እነዚህ እግዚአብሔር በዚህ አገር ሳለሁ የሰጠኝ የእኔ ልጆች ናቸው” ብሎ ለአባቱ መለሰለት። ያዕቆብም “እባርካቸው ዘንድ ወደ እኔ አቅርብልኝ” አለው። የያዕቆብ ዐይኖች በእርጅናው ምክንያት ስለ ደከሙ አጥርቶ ማየት አይችልም ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን ወደ እርሱ አቀረበለት፤ እርሱም ዕቅፍ አድርጎ ሳማቸው። ዮሴፍንም “አንተን እንደገና አያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ እግዚአብሔር ግን አንተን ብቻ ሳይሆን ልጆችህንም ጭምር አሳየኝ” አለው። ዮሴፍ ልጆቹን ከያዕቆብ ጒልበት ፈቀቅ አደረገና ወደ መሬት ጐንበስ ብሎ ሰገደ። ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ወስዶ ኤፍሬምን በቀኙ ለያዕቆብ በስተግራው በኩል፥ ምናሴን በግራው ለያዕቆብ በስተቀኝ በኩል አድርጎ አቀረበለት። ያዕቆብ ግን እጆቹን በማመሳቀል አስተላልፎ ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ፥ ግራ እጁን በበኲሩ በምናሴ ራስ ላይ አኖረ። ከዚህ በኋላ ዮሴፍን እንዲህ ሲል ባረከው፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ መንገዱን በመከተል ያገለገሉትና እኔንም ሕይወቴን ሙሉ እስከ ዛሬ ድረስ እረኛ ሆኖ የጠበቀኝ አምላክ እነዚህን ልጆች ይባርክ! እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።” ዮሴፍ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ማድረጉን ባየ ጊዜ ቅር ተሰኘ፤ ስለዚህ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንሥቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤ “አባቴ ሆይ፥ እንደዚህ አይደለም፤ በኲሩ ይህኛው ስለ ሆነ ቀኝ እጅህን በእርሱ ራስ ላይ አኑር” አለው። አባቱ ግን “ዐውቄአለሁ፤ ልጄ ዐውቄአለሁ፤ የምናሴም ዘር ታላቅ ሕዝብ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ የእርሱ ታናሽ ወንድም ከእርሱ ይበልጥ ታላቅ ይሆናል፤ ዘሮቹም ታላላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” አለ።

ዘፍጥረት 48:8-19 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እስራኤልም የዮሴፍን ልጆች አይቶ፦ “እነዚህ እነማን ናቸው?” አለው። ዮሴፍም ለአባቱ፦ “እግዚአብሔር በዚህ የሰጠኝ ልጆቼ ናቸው” አለ። እርሱም፦ “እባርካቸው ዘንድ ወደዚህ አቅርብልኝ” አለ። የእስራኤልም ዐይኖች ከሽምግልና የተነሣ ደክመው ነበር፥ ማየትም አይችልም ነበር፥ ወደ እርሱም አቀረባቸው፥ ሳማቸውም፥ አቀፋቸውም። እስራኤልም ዮሴፍን፦ “ፊትህን አያለሁ ብዬ አላሰብሁም ነበር፥ እነሆም እግዚአብሔር ዘርህን ደግሞ አሳየኝ” አለው። ዮሴፍም ከጉልበቱ ፈቀቅ አደረጋቸው፥ ወደ ምድርም በግምባሩ ሰገደ። ዮሴፍም ሁለቱን ልጆቹን ወሰደ፥ ኤፍሬምንም በቀኙ በእስራኤል ግራ፥ ምናሴንም በግራው በእስራኤል ቀኝ አደረገው፥ ወደ እርሱም አቀረባቸው። እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው፥ እርሱም ታናሽ ነበረ፥ ግራውንም በምናሴ ራስ ላይ አኖረ፥ እጆቹንም አስተላለፈ፥ ምናሴ በኩር ነበርና። ያዕቆብም ዮሴፍን ባረከ እንዲህም አለ፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ እግዚአብሔር፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፥ ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፥ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፥ በምድርም መካከል ይብዙ።” ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ጭኖ ባየ ጊዜ አሳዘነው፥ የአባቱንም እጅ በምናሴ ራስ ላይ ይጭነው ዘንድ ከኤፍሬም ራስ ላይ አነሣው። ዮሴፍም አባቱን፦ “አባቴ ሆይ እንዲህ አይደለም፥ በኩሩ ይህ ነውና፥ ቀኝህን በራሱ ላይ አድርግ” አለው። አባቱም እንዲህ ሲል እንቢታውን ገለጸ፦ “አውቄአለሁ ልጄ ሆይ፥ አውቄአለሁ፥ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል ታላቅም ይሆናል፥ ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፥ ዘሩም የአሕዛብ ሙላት ይሆናል።”