ዘፍጥረት 37:1-17

ዘፍጥረት 37:1-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ያዕ​ቆ​ብም አባቱ በስ​ደት በኖ​ረ​በት ሀገር በከ​ነ​ዓን ምድር ተቀ​መጠ። የያ​ዕ​ቆ​ብም ትው​ልድ እን​ዲህ ነው። ዮሴፍ ዐሥራ ሰባት ዓመት በሆ​ነው ጊዜ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር የአ​ባ​ቱን በጎች ይጠ​ብቅ ነበር፤ እር​ሱም ከአ​ባቱ ሚስ​ቶች ከባ​ላና ከዘ​ለፋ ልጆች ጋር ሳለ ብላ​ቴና ነበረ፤ ዮሴ​ፍም የክ​ፋ​ታ​ቸ​ውን ወሬ ወደ አባ​ታ​ቸው ወደ እስ​ራ​ኤል ያመጣ ነበር። ያዕ​ቆ​ብም ዮሴ​ፍን ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወ​ድ​ደው ነበር፤ እርሱ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደው ነበ​ርና። በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ችም ቀሚስ አደ​ረ​ገ​ለት። ወን​ድ​ሞ​ቹም አባ​ታ​ቸው ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ እን​ደ​ሚ​ወ​ድ​ደው በአዩ ጊዜ ጠሉት፤ በሰ​ላም ይና​ገ​ሩ​ትም ዘንድ አል​ቻ​ሉም። ዮሴ​ፍም ሕል​ምን አለመ፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ነገ​ራ​ቸው። እር​ሱም አላ​ቸው፥ “እኔ ያለ​ም​ሁ​ትን ሕልም ስሙ፤ እነሆ፥ እኛ በእ​ርሻ መካ​ከል ነዶ ስና​ስር ነበ​ርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእ​ና​ን​ተም ነዶ​ዎች በዙ​ርያ ከብ​በው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።” ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ “በእኛ ላይ ልት​ነ​ግ​ሥ​ብን ይሆን? ወይስ ገዢ ትሆ​ነን ይሆን?” አሉት። እን​ደ​ገ​ናም ስለ ሕል​ሙና ስለ ነገሩ የበ​ለጠ ጠሉት። ደግ​ሞም ሌላ ሕል​ምን አየ፤ ለአ​ባ​ቱና ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ነገ​ራ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ ደግሞ ሌላ ሕልም አለ​ምሁ፤ ሕል​ሙም እን​ዲህ ነው፦ ፀሐ​ይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋ​ክ​ብ​ትም ይሰ​ግ​ዱ​ልኝ ነበር።” አባ​ቱም ገሠ​ጸው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ይህ ያለ​ም​ኸው ሕልም ምን​ድን ነው? በውኑ እኔና እና​ትህ፥ ወን​ድ​ሞ​ች​ህም መጥ​ተን በም​ድር ላይ እን​ሰ​ግ​ድ​ልህ ይሆን?” ወን​ድ​ሞ​ቹም ቀኑ​በት፤ አባቱ ግን ይህን ነገር በልቡ ይጠ​ብ​ቀው ነበር። ወን​ድ​ሞ​ቹም በሴ​ኬም የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን በጎች ይጠ​ብቁ ዘንድ ሄዱ። እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ወን​ድ​ሞ​ችህ በሴ​ኬም በጎ​ችን የሚ​ጠ​ብቁ አይ​ደ​ሉ​ምን? ወደ እነ​ርሱ እል​ክህ ዘንድ ና” አለው። እር​ሱም፥ “እሺ” አለው። እር​ሱም፥ “ሄደህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፤ ወሬ​አ​ቸ​ው​ንም አም​ጣ​ልኝ” አለው። ወደ ኬብ​ሮ​ንም ቆላ ላከው፤ ወደ ሴኬ​ምም መጣ። እነ​ሆም፥ በም​ድረ በዳ ሲቅ​በ​ዘ​በዝ ሳለ አንድ ሰው አገ​ኘው፤ ሰው​የ​ውም፥ “ምን ትፈ​ል​ጋ​ለህ?” ብሎ ጠየ​ቀው። እር​ሱም፥ “ወን​ድ​ሞ​ችን እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ በጎ​ቹን የሚ​ጠ​ብ​ቁ​በት ወዴት እንደ ሆነ እባ​ክህ ንገ​ረኝ?” አለ። ሰው​የ​ውም፥ “ከዚህ ተነ​ሥ​ተ​ዋል፤ ወደ ዶታ​ይን እን​ሂድ ሲሉም ሰም​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው። ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን ተከ​ታ​ትሎ ሄደ፤ በዶ​ታ​ይ​ንም አገ​ኛ​ቸው።

ዘፍጥረት 37:1-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ያዕቆብ አባቱ በኖረበት በከነዓን ምድር ተቀመጠ። የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ ይህ ነው። ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረ ጊዜ፣ ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዘለፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋራ የአባቱን በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር። እርሱም ስለ ወንድሞቹ ድርጊት ለአባቱ መጥፎ ወሬ ይዞለት መጣ። እስራኤል ዮሴፍን በስተርጅናው ስለ ወለደው፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ይወድደው ነበር፤ በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ ጠባብም አደረገለት። ወንድሞቹም፣ አባታቸው ከእነርሱ አብልጦ የሚወድደው መሆኑን ሲያዩ፣ ዮሴፍን ጠሉት፤ በቅን አንደበትም ሊያናግሩት አልቻሉም። ዮሴፍም ሕልም ዐለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ሲነግራቸው የባሰ ጠሉት። እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ ስሙኝ እኛ ሁላችን በዕርሻ ውስጥ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ በድንገት ተነሥታ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶዎች ዙሪያዋን ከብበው ለእኔ ነዶ ሰገዱላት።” ወንድሞቹም፣ “ለካስ በላያችን ለመንገሥ ታስባለህና! ለመሆኑ አንተ እኛን ልትገዛ!” አሉት፤ ስለ ሕልሙና ስለ ተናገረው ቃል ከፊት ይልቅ ጠሉት። እንደ ገናም ሌላ ሕልም ዐለመ፤ ለወንድሞቹም፣ “እነሆ፤ ሌላ ሕልም ዐለምሁ፤ ፀሓይና ጨረቃ፣ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ሲሰግዱልኝ አየሁ” ብሎ ነገራቸው። ሕልሙን ለአባቱና ለወንድሞቹ በነገራቸው ጊዜ፣ አባቱ “ይህ ያየኸው ሕልም ምንድን ነው? እኔና እናትህ ወንድሞችህም በፊትህ ወደ ምድር ተጐንብሰን በርግጥ ልንሰግድልህ ነው?” ሲል ገሠጸው። ወንድሞቹ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው። ከዚህም በኋላ የዮሴፍ ወንድሞች የአባታቸውን በጎችና ፍየሎች ለማሰማራት ወደ ሴኬም አካባቢ ሄዱ፤ እስራኤልም ዮሴፍን “እንደምታውቀው ወንድሞችህ መንጎቹን በሴኬም አካባቢ አሰማርተዋል፤ በል ተነሥ፣ ወደ እነርሱ ልላክህ።” አለው። ዮሴፍም “ይሁን ዕሺ” አለው። ያዕቆብም፣ “ሄደህ ወንድሞችህም፣ መንጎቹም ደኅና መሆናቸውን አይተህ ወሬያቸውን አምጣልኝ” አለው፤ ከኬብሮንም ሸለቆ ወደ ሴኬም ላከው። ዮሴፍም ሴኬም በደረሰ ጊዜ፣ ሜዳ ላይ ወዲያ ወዲህ ሲባዝን አንድ ሰው አግኝቶት “ምን እየፈለግህ ነው?” ሲል ጠየቀው። ዮሴፍም፣ “ወንድሞቼን እየፈለግኋቸው ነው፤ መንጎቻቸውን የት እንዳሰማሩ ልትነግረኝ ትችላለህ?” አለው። ሰውየውም፣ “ከዚህ ሄደዋል፤ ደግሞም፣ ‘ወደ ዶታይን እንሂድ’ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ” አለው። ከዚያም ዮሴፍ ወንድሞቹን ፍለጋ ሄደ፣ ዶታይን አቅራቢያም አገኛቸው።

ዘፍጥረት 37:1-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ያዕቆብም አባቱ በስደት በኖረበት አገር በከነዓን ምድር ተቀመጠ። የያዕቆብም ትውልድ ይህ ነው። ዮሴፍ የአሥራ ሰባት ዓመት ልጅ በሆን ጊዜ ከወንድሞቹ ጋር በጎችን ይጠብቅ ነበር፤ እርሱም ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዘለፋ ልጆች ጋር ሳለ ብላቴና ነበረ፤ ዮሴፍም የክራታቸውን ወሬ ወደ አባታቸው አመጣ። እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወደው ነበር እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበር በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት። ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንዲወደው ባዩ ጊዜ ጠሉት፥ በሰላም ይናገሩትም ዘንድ አልቻሉም። ዮሴፍም ሕልምን አለመ ለወንድሞቹም ነገራቸው፤ እነርሱም እንደ ገና በብዙ ጠሉት እርሱ አላቸው፦ እኔ ያለምሁትን ሕልም ስሙ፤ እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበርና እነሆም የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ። ወንድሞቹም፦ በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ልትገዛ ይሆን? አሉት። እንደ ገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ ይልቁን ጠሉት። ደግሞም ሌላ ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እንዲህም አለ፦ እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ እነሆ ፀሐይን ጨረቃ አሥራ አንድ ከዋክብርም ሲሰግዱልኝ አየሁ። ለአባቱና ለወንድሞቹም ነገራቸው አባቱም ገሠጸው እንዲህም አለው፦ ይህ ያለምኸው ሕልም ምንድር ነው? በውኑ እኔና እናትህ ወንድሞችህም መጥተን በምድር ላይ እንስገድልህ ይሆን? ወንድሞቹም ቀኑበት አባቱ ግን ነገሩን ይጠብቅው ነበር። ወንድሞቹ በሴኬም የአባታቸውን በጎች ይጠብቁ ዘንድ ሄዱ። እስራኤልም ዮሴፍን፦ ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን የሚጠብቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እልክህ ዘንድ ና አለው። እርሱም እነሆኝ አለው። እርሱም፦ ሄደህ ወንድሞችህና በጎቹ ደኅን እንደ ሆኑ እይ ወሬአቸውንም አምጣክኝ አለው። እንዲንም ከኬብሮን ቆላ ሰደደው ወደ ሴኬምም መጣ። እነሆም በምድረ በዳ ስቅበዘብዝ ሳለ አንድ ሰው አገኘው ሰውዮውም፦ ምን ትፈልጋለህ? ብሎ ጠየቀው። እርሱም ወንድሞቼን እፈልጋለሁ በጎቹን የሚጠብቁበት ወዴት እንደ ሆነ እባክህ ንገረኝ አለ። ሰውዮውም፦ ከዚህ ተነሥተዋል ወደ ዶታይን እንሂድ ሲሉም ስምቼአቸዋለሁ አለው። ዮሴፍም ወንድሞቹን ተከታትሎ ሄደ በዶታይንም አገኛቸው።

ዘፍጥረት 37:1-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ያዕቆብ ተቀማጭነቱን አባቱ በኖረበት በከነዓን ምድር አደረገ። የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ እንደሚከተለው ነው፤ ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረበት ጊዜ ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዚልፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋር በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር፤ ወንድሞቹ የሚፈጽሙትንም በደል እያመጣ ለአባቱ ይነግር ነበር። በስተርጅና የወለደው ስለ ሆነ ያዕቆብ ዮሴፍን ከሌሎች ልጆች ሁሉ አብልጦ ይወደው ነበር፤ ስለዚህም ጌጠኛ የሆነ እጀ ጠባብ ሰፋለት። ወንድሞቹም አባታቸው ከእነርሱ ይልቅ ዮሴፍን እንደሚወድ ባዩ ጊዜ በመቅናት ጠሉት፤ መልካም ቃልም ሊናገሩት አልወደዱም። አንድ ሌሊት ዮሴፍ ሕልም አየ፤ ሕልሙን ለወንድሞቹ በነገራቸውም ጊዜ ከቀድሞው ይበልጥ ጠሉት። እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ፤ እኛ ሁላችን በእርሻ ውስጥ የስንዴ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ ተነሣና ቀጥ ብሎ ቆመ፤ የእናንተ ነዶዎች ዙሪያውን ተሰብስበው ለእኔ ነዶ ሰገዱለት።” ወንድሞቹም “ታዲያ በእኛ ላይ ንጉሥ ሆነህ ልትገዛን ታስባለህን?” ብለው ጠየቁት። ስላየው ሕልምና ስለ ተናገረው ቃል ከበፊቱ ይበልጥ ጠሉት። ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ሌላ ሕልም አይቶ ወንድሞቹን “እነሆ፥ ሌላ ሕልም አየሁ፤ በሕልሜም ፀሐይ፥ ጨረቃና ዐሥራ አንድ ከዋክብት ሰገዱልኝ” አላቸው። ይህንኑ ለወንድሞቹ የነገራቸውን ሕልም ለአባቱም በነገረው ጊዜ፥ አባቱ “ይህ ምን ዐይነት ሕልም ነው? እኔና እናትህ ወንድሞችህም የምንሰግድልህ ይመስልሃልን?” በማለት ገሠጸው። የዮሴፍ ወንድሞች እጅግ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ይህን ነገር በልቡ እያሰላሰለ ይጠብቀው ነበር። አንድ ቀን የዮሴፍ ወንድሞች የአባታቸውን መንጋዎች ይዘው ወደ ሴኬም ተሰማሩ፤ እስራኤልም ዮሴፍን “እነሆ፥ ወንድሞችህ መንጋውን ይዘው ወደ ሴኬም መሰማራታቸውን ታውቃለህ፤ ስለዚህ ወደ እነርሱ ልልክህ እፈልጋለሁ” አለው። ዮሴፍም “እሺ እሄዳለሁ” አለ። አባቱም “በል እንግዲህ ሂድና የወንድሞችህንና የመንጋዎቹን ደኅንነት አይተህ ንገረኝ” አለው። በዚህ ዐይነት እስራኤል ዮሴፍን ከኬብሮን ሸለቆ ላከው። ዮሴፍም ሴኬም ደረሰ። እዚያም በየሜዳው ሲባዝን ሳለ አንድ ሰው አገኘውና “ምን እየፈለግህ ነው?” ብሎ ጠየቀው። ዮሴፍም “ወንድሞቼን እየፈለግሁ ነው፤ መንጋዎቻቸውን ይዘው ወዴት እንደ ተሰማሩ ልትነግረኝ ትችላለህን?” አለው። ሰውየውም “እነርሱ ከዚህ ሄደዋል፤ ‘ወደ ዶታን እንሂድ’ ሲሉ ሰምቼአቼዋለሁ” አለው። ስለዚህ የወንድሞቹን ዱካ ተከትሎ ሄደና በዶታን አገኛቸው።

ዘፍጥረት 37:1-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ያዕቆብም አባቱ በስደት በኖረበት አገር በከነዓን ምድር ተቀመጠ።። የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ እንደሚከተለው ነው፤ ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረበት ጊዜ ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዚልፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋር በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር፤ የእነርሱንም ክፋት ነገር ዮሴፍ ወደ አባታቸው አመጣ። እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወደው ነበር፥ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና፥ በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት። ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንደሚወደው ባዩ ጊዜ ጠሉት፥ በሰላም ሊያናግሩትም አልቻሉም። ዮሴፍም ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እነርሱም እንደገና አብዝተው ጠሉት። እርሱም አላቸው፦ “እኔ ያለምሁትን ሕልም ስሙ፥ እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበር፥ እነሆም፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፥ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።” ወንድሞቹም፦ “በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ልትገዛ ይሆን?” አሉት። እንደገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ የበለጠ ጠሉት። ደግሞም ሌላ ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም፦ “እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ፥ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ሲሰግዱልኝ አየሁ።” ሲል ነገራቸው። ለአባቱና ለወንድሞቹም በነገራቸው ጊዜ፥ “ይህ ያለምኸው ሕልም ምንድነው? በውኑ እኔና እናትህ ወንድሞችህም መጥተን በምድር ላይ እንሰግድልህ ይሆን?” በማለት አባቱ ገሠጸው። ወንድሞቹም ቀኑበት፥ አባቱ ግን ነገሩን ጠብቆ አኖረው። ወንድሞቹ በሴኬም የአባታቸውን በጎች ይጠብቁ ዘንድ ሄዱ። እስራኤልም ዮሴፍን፦ “ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን እየጠበቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እንድልክህ ና” አለው። እርሱም “እነሆኝ” አለው። እርሱም፦ “ሄደህ ወንድሞችህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፥ ወሬአቸውንም አምጣልኝ” አለው። በዚህ ዓይነት ከኬብሮን ሸለቆ ላከው፥ ወደ ሴኬምም መጣ። እነሆም በየሜዳው ሲባዝን አንድ ሰው አገኘው፤ ሰውዮውም፦ “ምን ትፈልጋለህ?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም “ወንድሞቼን እየፈለግሁ ነው፥ በጎቹን የሚጠብቁበት ወዴት እንደሆነ እባክህ ንገረኝ” አለ። ሰውዮውም፦ “ከዚህ ተነሥተዋል፥ ወደ ዶታይን እንሂድ ሲሉም ሰምቼአቸዋለሁ” አለው። ዮሴፍም ወንድሞቹን ተከታትሎ ሄደ፥ በዶታይንም አገኛቸው።