ዘፍጥረት 31:6-7
ዘፍጥረት 31:6-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እኔ ባለኝ ጕልበቴ ሁሉ አባታችሁን እንዳገለገልሁ ታውቃላችሁ። አባታችሁ ግን አሳዘነኝ፥ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለወጠ፤ እግዚአብሔር ግን ክፉን ያደርግብኝ ዘንድ አልፈቀደለትም።
ዘፍጥረት 31:6-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
መቼም ባለኝ ዐቅም አባታችሁን ማገልገሌ ከእናንተ የተሰወረ አይደለም። አባታችሁ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ እየለዋወጠ አታልሎኛል፣ ሆኖም እንዲጐዳኝ እግዚአብሔር አልፈቀደለትም።
ዘፍጥረት 31:6-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እኔ ባለኝ ጕልበቴ ሁሉ እንዳገለገልሁ ታውቃላችሁ። አባታችሁ ግን አታለለኝ ደመወዜንም አሥር ጊዜ ለወጠ እግዚአብሔር ግን ክፋን ያደርግብኝ ዘንድ አልፈቀደለትም።