ዘፍጥረት 25:1-18

ዘፍጥረት 25:1-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አብ​ር​ሃ​ምም ደግሞ ስምዋ ኬጡራ የተ​ባ​ለች ሚስት አገባ። እር​ስ​ዋም ዘን​በ​ሪን፥ ዮቃ​ጤ​ንን፥ ሜዳ​ንን፥ ዮብ​ቅን፥ ምድ​ያ​ም​ንና ሴሂን ወለ​ደ​ች​ለት። ዮቃ​ጤ​ንም ሶቤ​ቅን፥ ቲማ​ን​ንና ድዳ​ንን ወለደ። የድ​ዳ​ንም ልጆች ራጉ​ኤል፥ ንበ​ከዝ፥ እስ​ራ​ኦ​ምና ሎአም ናቸው። የም​ድ​ያ​ምም ልጆች ጌፌር፥ ዔፋር፥ ሄኖኅ፥ አቢ​ሮ​ንና ቲያ​ሮስ ናቸው። እነ​ዚ​ህም ሁሉ የኬ​ጡራ ልጆች ናቸው። አብ​ር​ሃ​ምም በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ለልጁ ለይ​ስ​ሐቅ ሰጠው፤ አብ​ር​ሃ​ምም ለቁ​ባ​ቶቹ ልጆች ሀብ​ትን ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ገና በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ከልጁ ከይ​ስ​ሐቅ ለይቶ ወደ ምሥ​ራቅ ሀገር ሰደ​ዳ​ቸው። አብ​ር​ሃ​ምም የኖ​ረ​በት የዕ​ድ​ሜው ዓመ​ታት እነ​ዚህ ናቸው፤ መቶ ሰባ አም​ስት ዓመት ኖረ። አብ​ር​ሃ​ምም መል​ካም ሽም​ግ​ል​ናን ሸም​ግሎ፥ ዘመ​ኑ​ንም ፈጽሞ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ። ልጆቹ ይስ​ሐ​ቅና ይስ​ማ​ኤ​ልም በመ​ምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬ​ጢ​ያ​ዊው በሰ​ዓር ልጅ በኤ​ፍ​ሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆ​ነው ዋሻ ውስጥ ቀበ​ሩት። ይህም አብ​ር​ሃም ከኬጢ ልጆች የገ​ዛው እርሻ ነው፤ አብ​ር​ሃ​ም​ንና ሚስ​ቱን ሣራን በዚያ ቀበ​ሩ​አ​ቸው። እን​ዲ​ህም ሆነ፥ አብ​ር​ሃ​ምም ከሞተ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ባረ​ከው፤ ይስ​ሐ​ቅም ዐዘ​ቅተ ራእይ ተብሎ በሚ​ጠ​ራው ምንጭ አጠ​ገብ ኖረ። የሣራ ባሪያ ግብ​ፃ​ዊቱ አጋር ለአ​ብ​ር​ሃም የወ​ለ​ደ​ች​ለት የአ​ብ​ር​ሃም ልጅ የይ​ስ​ማ​ኤል ትው​ልድ ይህ ነው፤ የይ​ስ​ማ​ኤ​ልም የል​ጆቹ ስም በየ​ስ​ማ​ቸ​ውና በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው እን​ዲህ ነው። የይ​ስ​ማ​ኤል የበ​ኵር ልጁ ናቡ​አት፥ ቄዳር፥ ነብ​ዳ​ኤል፥ መብ​ሳን፥ ማሴሜ፥ ዱማ፥ ማሤን፥ ኩዳን፥ ቴማን፥ ኤያ​ጤር፥ ናፌስ፥ ቄድን። የይ​ስ​ማ​ኤል ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ስማ​ቸ​ውም በየ​መ​ን​ደ​ራ​ቸ​ውና በየ​ሰ​ፈ​ራ​ቸው ይህ ነው፤ በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውም ዐሥራ ሁለት አለ​ቆች ናቸው። እር​ሱም ከኤ​ው​ላጥ አን​ሥቶ በግ​ብፅ ፊት ለፊት እስ​ከ​ም​ት​ገኝ እስከ ሴይር ባለው ሀገር ኖረ፤ ወደ አሦ​ር​ዮ​ንም ደረሰ፤ እን​ዲ​ህም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ሁሉ ፊት ተቀ​መጠ። ይስ​ማ​ኤ​ልም የኖ​ረ​በት የዕ​ድ​ሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው ፤ ሸም​ግሎ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።

ዘፍጥረት 25:1-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አብርሃም ኬጡራ የተባለች ሌላ ሚስት አገባ። እርሷም፦ ዘምራንን፣ ዮቅሳንን፣ ሜዳንን፣ ምድያምን፣ የስቦቅንና ስዌሕን ወለደችለት። ዮቅሳንም ሳባንና ድዳንን ወለደ፤ የድዳንም ልጆች፦ አሦራውያን፣ ለጡሳውያንና ለኡማውያን ናቸው። የምድያም ልጆች፦ ጌፌር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው። አብርሃም ያለውን ሀብት ሁሉ ለይሥሐቅ አወረሰው፤ ለቁባቶቹ ልጆች ግን በሕይወት እያለ ስጦታ አደረገላቸው፤ ከልጁ ከይሥሐቅም ርቀው እንዲኖሩ ወደ ምሥራቅ ምድር ሰደዳቸው። አብርሃም በጠቅላላው መቶ ሰባ ዐምስት ዓመት ኖረ። ከዚያም ዐረፈ፤ ዕድሜ ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። ልጆቹ ይሥሐቅና እስማኤል በመምሬ አጠገብ በምትገኝ በኬጢያዊው በሰዓር ልጅ በኤፍሮን ዕርሻ በመክፈላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም የዕርሻ ቦታ አብርሃም ከኬጢያውያን የገዛው ነበር፤ ከሚስቱ ከሣራ አጠገብ በዚያ ተቀበረ። አብርሃም ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር ይሥሐቅን ባረከው፤ በዚህ ጊዜ ይሥሐቅ በብኤርላሃይሮኢ አቅራቢያ ይኖር ነበር። ግብጻዊቷ የሣራ አገልጋይ አጋር፣ ለአብርሃም የወለደችለት የእስማኤል ትውልድ ይህ ነው። የእስማኤል ልጆች ስም እንደ ዕድሜያቸው ቅደም ተከተል እንዲህ ነው፦ የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብዳኤል፣ መብሳም፣ ማስማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣ ኩዳን፣ ቴማን፣ ኢጡር፣ ናፌስና ቄድማ። እነዚህ የእስማኤል ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም በኖሩባቸውና በሰፈሩባቸው ቦታዎች የዐሥራ ሁለት ነገድ አለቆች ስሞች ናቸው። እስማኤል በጠቅላላው መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። ዘሮቹም መኖሪያቸውን ከግብጽ ድንበር አጠገብ፣ ወደ አሦር በሚወስደው መንገድ፣ በኤውላጥና በሱር መካከል አደረጉ፤ ከወንድሞቻቸውም ሁሉ ጋራ በጠላትነት ኖሩ።

ዘፍጥረት 25:1-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አብርሃምም ደግሞ ስምዋ ኬጡራ የተባላች ሚስት አገባ። እርስዋም ዘምራንን ዩቅሳንን ሜዳንን ምድያምን የስቦቅን ስዌሕን ወለደችለት። ዩቅሳንም ሳባንና ድዳንን ወለደ። የድዳንም ልጆች አሦርያውያን ለጡሳውያን ለኡማውያን ናቸው፥ የምድይምም ስጆች ጌፌር ዔፌት ሄኖኅ እቢዳዕ ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው። አብርሃምም የነበረውን ሁሉ ለይስሐቅ ሰጠው፤ የአብርሃም ለነበሩ ለቁብቶቹ ልጆች አብርሃም ስጦታን ሰጣቸው እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሕቅ ለይቶ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አገር ሰደዳቸው። አብርሃምም የኖረበት የዕድሜው ዓመታት እነዚህ ናቸው መቶ ሰባ አምስት ዓመት ኖረ። አብርሃናም ነፍሱን ሰጠ በመልካም ሽምግልናም ሞተ ሸመገለ፥ ብዙ ዘመንም ጠገበ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ። ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤልም በመምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬጢያዊ በሰዓርልጅ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት። አብርሃምም ከኬጢ ልጆች የገዛው እርሻ ይህ ነው አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ። አብርሃምም ከሞተ በኍላ እግዚአብሔር ልጁን ይስሐቅን ባረከው ይስሐቅም ብኤርለሃይሮኢ ተብሎ በሚጠራው ምንጭ አጠገብ ኖረ። የሣራ ባሪያ ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችው የአብርሃም ልጅ የእስማኤል ትውልድ ይህ ነው፤ የእስማኤልም የልጆቹ ስም በየስማቸውን በየትውልዳቸው እንዲህ ነው፤ የእስማኤል የበኵር ልጁ፥ ነባዮት፥ ቄዳር፥ ነብዳኤል፥ መብሳም፥ ማስማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን፥ ኢጡር፥ ናፊስ፥ ቄድማ። የእስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰደራቸው ይኸው ነው በየወገናቸውም አሥራ ሁለት አለቆች ናቸው። እስማኤልም የኖረበት የዕድሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው፤ ነፍሱን ሰጠ ሞትንም፤ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ። መኖሪያቸውም ከኤውላጥ አንሥቶ በግብፅ ፊት ለፊት እስከምትገኝ እስከሱር ድረስ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ ላይ ነበረ፤ እንዲህም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት ተቀመጠ።

ዘፍጥረት 25:1-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አብርሃም ቀጡራ የምትባል ሌላ ሚስት አገባ፤ እርስዋም ዚምራንን፥ ዮቅሻንን፥ መዳንን፥ ምድያምን፥ ዩሽባቅንና ሹሐን ወለደችለት። ዮቅሻንም ሳባንና ደዳንን ወለደ፤ የደዳንም ዘሮች አሹራውያን፥ ሌጡሻውያንና ሌኡማውያን ናቸው። የምድያምም ልጆች ዔፋ፥ ዔፈር፥ ሐኖክ፥ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የቀጡራ ዘሮች ናቸው። አብርሃም ያለውን ሀብት ሁሉ ለይስሐቅ አወረሰው፤ ከሌሎች ሴቶች ለተወለዱትም ልጆች ገና በሕይወት ሳለ ስጦታ ሰጣቸው፤ ከዚህ በኋላ እነዚህ ሌሎች ልጆች ከይስሐቅ ርቀው ወደ ምሥራቅ አገር እንዲሄዱ አደረጋቸው። የአብርሃም ዕድሜ በአጠቃላይ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤ በዚህም ዐይነት አብርሃም በቂ ዕድሜ አግኝቶ ካረጀ በኋላ ሞተ፤ ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤል ማክፌላ በተባለ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ ከመምሬ በስተምሥራቅ በሒታዊው በጾሐር ልጅ በዔፍሮን እርሻ ውስጥ የሚገኘው ነው፤ እርሱም አብርሃም ከሒታውያን ላይ የገዛው የመቃብር ቦታ ነው፤ በዚህ ዐይነት አብርሃም ሚስቱ ሣራ በተቀበረችበት ዋሻ ተቀበረ። አብርሃም ከሞተ በኋላ ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር ባረከው፤ ይስሐቅም “ብኤርላሐይ ሮኢ ወይም የሚያየኝ ሕያው አምላክ” ተብሎ በሚጠራው ኲሬ አጠገብ ይኖር ነበር። የሣራ አገልጋይ ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል፥ ከዚህ በታች በዕድሜአቸው ቅደም ተከተል ተራ የተዘረዘሩትን ልጆች ወለደ፤ እነርሱም፦ ነባዮት፥ ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥ ሚሽማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ሐዳድ፥ ቴማ፥ ይጡር፥ ናፊሽ እና ቄድማ ናቸው። እነዚህ የእስማኤል ልጆች ለዐሥራ ሁለት ነገዶች ቅድመ አያቶች ነበሩ፤ ስማቸውም በኖሩባቸው ከተሞችና ስፍራዎች ሲጠራ ይኖራል። እስማኤል መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ሲሆነው ሞተ፤ የእስማኤል ዘሮች ከግብጽ በስተምሥራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ይኖሩ ነበር፤ የኖሩትም ከሌሎቹ የአብርሃም ዘሮች ጋር በጥላቻ ተራርቀው ነበር።

ዘፍጥረት 25:1-18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አብርሃም ኬጡራ የምትባል ሌላ ሚስት አገባ። እርሷም ዚምራንን፥ ዮቅሻንን፥ ሜዳንን፥ ምድያምን፥ የሽቦቅን፥ እና ሹሐን ወለደችለት። ዮቅሻንም ሳባንና ድዳንን ወለደ። የድዳንም ልጆች አሹራውያን፥ ለጡሻውያንና፥ ለኡማውያን ናቸው። የምድያምም ልጆች ዔፋ፥ ዔፈር፥ ሐኖክ፥ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው። አብርሃምም የነበረውን ሁሉ ለይስሐቅ ሰጠው፥ ነገር ግን የአብርሃም ለነበሩትም ለቁባቶቹ ልጆች አብርሃም ስጦታ ሰጣቸው፥ እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሐቅ ለይቶ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አገር ሰደዳቸው። አብርሃምም በሕይወት የኖረበት የዕድሜው ዘመን መቶ ሰባ አምስት ዓመታት ናቸው። በመጨረሻዋ እስትንፋሱ አብርሃም ነፍሱን ሰጠ፥ በመልካምም ሽምግልና ሞተ፥ ሸምግሎ፥ ብዙ ዘመንም ጠገበ፥ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤል፥ ከመምሬ በስተ ምሥራቅ በሒታዊው በጾሐር ልጅ በዔፍሮን እርሻ ውስጥ፥ ማክፌላ በተባለ ዋሻ ቀበሩት። የእርሻው ቦታ አብርሃም ከሒታውያን ላይ የገዛው ነው፤ ከዚያም አብርሃም ከሚስቱ ሣራ ጋር ተቀበረ። ከአብርሃም ሞት በኋላም እግዚአብሔር ልጁን ይስሐቅን ባረከው፤ ይስሐቅም ብኤር-ላሃይ-ሮኢ ተብሎ በሚጠራው ምንጭ አጠገብ ኖረ። የሣራ አገልጋይ ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችው የአብርሃም ልጅ የእስማኤል ትውልድ ይህ ነው፤ በትውልዳቸው ቅደም ተከተል የተዘረዘሩት የእስማኤል የልጆቹ ስም እንዲህ ነው፥ የእስማኤል የበኩር ልጁ ነባዮት፥ እና ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥ ሚሽማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ሐዳድ፥ ቴማ፥ ይጡር፥ ናፊሽ እና ቄድማ ናቸው። የእስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰፈራቸው ይኸው ነው፥ በየወገናቸውም ዐሥራ ሁለት አለቆች ናቸው። እስማኤልም የኖረበት የዕድሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው፥ የመጨረሻዋ እስትንፋሱን ተንፍሶም ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። ዘሮቹም ከግብጽ በስተ ምሥራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ሲሰፍሩ፤ የኖረውም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት በተቃርኖ ነበር።