ኦሪት ዘፍጥረት 25
25
1አብርሃምም ደግሞ ስምዋ ኬጡራ የተባላች ሚስት አገባ። 2እርስዋም ዘምራንን ዩቅሳንን ሜዳንን ምድያምን የስቦቅን ስዌሕን ወለደችለት። 3ዩቅሳንም ሳባንና ድዳንን ወለደ። የድዳንም ልጆች አሦርያውያን ለጡሳውያን ለኡማውያን ናቸው፥ 4የምድይምም ስጆች ጌፌር ዔፌት ሄኖኅ እቢዳዕ ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው። 5አብርሃምም የነበረውን ሁሉ ለይስሐቅ ሰጠው፤ 6የአብርሃም ለነበሩ ለቁብቶቹ ልጆች አብርሃም ስጦታን ሰጣቸው እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሕቅ ለይቶ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አገር ሰደዳቸው። 7አብርሃምም የኖረበት የዕድሜው ዓመታት እነዚህ ናቸው መቶ ሰባ አምስት ዓመት ኖረ። 8አብርሃናም ነፍሱን ሰጠ በመልካም ሽምግልናም ሞተ ሸመገለ፥ ብዙ ዘመንም ጠገበ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ። 9ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤልም በመምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬጢያዊ በሰዓርልጅ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት። 10አብርሃምም ከኬጢ ልጆች የገዛው እርሻ ይህ ነው አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ። 11አብርሃምም ከሞተ በኍላ እግዚአብሔር ልጁን ይስሐቅን ባረከው ይስሐቅም ብኤርለሃይሮኢ ተብሎ በሚጠራው ምንጭ አጠገብ ኖረ።
12የሣራ ባሪያ ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችው የአብርሃም ልጅ የእስማኤል ትውልድ ይህ ነው፤ 13የእስማኤልም የልጆቹ ስም በየስማቸውን በየትውልዳቸው እንዲህ ነው፤ የእስማኤል የበኵር ልጁ፥ 14ነባዮት፥ ቄዳር፥ ነብዳኤል፥ መብሳም፥ ማስማዕ፥ 15ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን፥ ኢጡር፥ ናፊስ፥ ቄድማ። 16የእስማኤል ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ስማቸውም በየመንደራቸውና በየሰደራቸው ይኸው ነው በየወገናቸውም አሥራ ሁለት አለቆች ናቸው። 17እስማኤልም የኖረበት የዕድሜው ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው፤ ነፍሱን ሰጠ ሞትንም፤ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ። 18መኖሪያቸውም ከኤውላጥ አንሥቶ በግብፅ ፊት ለፊት እስከምትገኝ እስከሱር ድረስ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ ላይ ነበረ፤ እንዲህም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት ተቀመጠ።
19የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ትውልድም ይህ ነው አብርሃም ይስሐቅም አርባ ዓመት ሲሆነውም ርብቃን አገባ። 20እርስዋም በሁለት ወንዞች መካከል ያለ የሶርያዊው የባቱኤል ልጅና የሶርይዊው የላባ እኅት ናት። 21ይስሐቅም ስለሚስቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ መካን ነበረችና፤ እግዚአብሔርም ተለመነው፥ ርብቃም ሚስቱ ፀነሰች። 22ልጆችም በሆድዋ ውስጥ ይገፋፋ ነበር፤ እርስዋም፦ እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔም ምኔ ነው? አለች። ከእግዚአብሔርም ትጠይቅ ዘንድ ሄደች። 23እግዚአብሔርም አላት፦ ሁለት ወገኖች በማኅፀንሽ ናቸው ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል። 24ትወልድ ዘንድ ዘመንዋ በተፈጸመ ጊዜም እነሆ በማኅፀንዋ መንታ ነበሩ። 25በፊትም የወጣው ቀይ ነበረ፥ ሁለንትናውም ጠጕር ለብሶ ነበር፤ ስሙም ዔሳው ተባለ። 26ከዚይም በኍላ ወንድሙ ወጣ በእጁም፥ የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙም ያዕቆብ ተባለ። እርስዋ ልጆችን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።
27ብላቴኖቹም አደጉ፤ ዔሳውም አደን የሚያውቅ የበረሃ ሰው ሆነ ያዕቆብ ግን ጭምት ሰው ነበረ፥ በድንኳንም ይቀመጥ ነበር። 28ይስሐቅም ዔሳውን ይወድ ነበረ ካደነው ይበላ ነበርና፤ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበረች። 29ያዕቆብም ወጥ ሠራ ዔሳውም ደክሞ ከበረሃ ገባ፤ 30ዔሳውም ያዕቆብን፦ ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና አለው ስለዚህ ስሙ ኤዶም ተባለ። 31ያዕቆብም፦ በመጀመሪያ ብኵርናህን ሽጥልኝ አለው። 32ዔሳውም፦ እነሆ እኔ ልሞት ነኝ ይህች ብኵርና ለምኔ ናት? አለ። 33ያዕቆብም፦ እስኪ በመጀመሪያ ማልልኝ አለው። ማለለትም ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠ። 34ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራን የምስር ወጥ ሰጠው በላ ጠጣ ተነሥቶም ሄደ፤ እንዲሁም ዔሳው ብኵርናውን አቃለላት።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 25: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ