ዘፍጥረት 13:8-18

ዘፍጥረት 13:8-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አብ​ራ​ምም ሎጥን አለው፥ “እኛ ወን​ድ​ማ​ማች ነንና በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በእ​ረ​ኞ​ቼና በእ​ረ​ኞ​ችህ መካ​ከል ጠብ አይ​ሁን። እነሆ፥ ምድር ሁሉ በፊ​ትህ አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ አንተ ወደ ግራው ብት​ሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄ​ዳ​ለሁ፤ አን​ተም ወደ ቀኙ ብት​ሄድ እኔ ወደ ግራ እሄ​ዳ​ለሁ።” ሎጥም ዓይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ው​ንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞ​ላ​በት መሆ​ኑን አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን ከማ​ጥ​ፋቱ አስ​ቀ​ድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነ​ትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ። ሎጥም ለራሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ውን ሀገር ሁሉ መረጠ፤ ሎጥም ወደ ምሥ​ራቅ ተጓዘ፤ አን​ዱም ከሌ​ላው እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ። አብ​ራም በከ​ነ​ዓን ምድር ተቀ​መጠ፤ ሎጥም በጎ​ረ​ቤት ሕዝ​ቦች ከተማ ተቀ​መጠ፤ ድን​ኳ​ኑ​ንም በሰ​ዶም ተከለ፤ የሰ​ዶም ሰዎች ግን ክፉ​ዎ​ችና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነበሩ። ሎጥ ከተ​ለ​የው በኋ​ላም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ራ​ምን አለው፥ “ዐይ​ን​ህን አን​ሣና አንተ ካለ​ህ​በት ስፍራ ወደ መስ​ዕና ወደ አዜብ፥ ወደ ምሥ​ራ​ቅና ወደ ምዕ​ራብ እይ፤ የም​ታ​ያ​ትን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እሰ​ጣ​ለ​ሁና። ዘር​ህ​ንም እንደ ባሕር አሸዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የባ​ሕር አሸ​ዋን ይቈ​ጥር ዘንድ የሚ​ችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈ​ጠ​ራል። ተነሣ፤ በም​ድር በር​ዝ​መ​ቷም፥ በስ​ፋ​ቷም ዙር፤ እር​ስ​ዋን ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እሰ​ጣ​ለ​ሁና።” አብ​ራ​ምም ድን​ኳ​ኑን ነቀለ፤ መጥ​ቶም በኬ​ብ​ሮን ባለው የመ​ምሬ ዛፍ ተቀ​መጠ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ።

ዘፍጥረት 13:8-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አብራምም ሎጥን እንዲህ አለው፤ “እኛ ወንድማማቾች ነንና፣ በአንተና በእኔ ወይም በእረኞቻችን መካከል ጠብ ሊኖር አይገባም። ይኸው እንደምታየው አገሩ ሰፊ ነው፤ ብንለያይ ይሻላል። አንተ ግራውን ብትመርጥ፣ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተ ቀኙን ብትመርጥ፣ እኔ ወደ ግራ አመራለሁ።” ሎጥ ዐይኑን አቅንቶ ሲመለከት፣ የዮርዳኖስ ረባዳ ሜዳ እንደ እግዚአብሔር ገነት፣ በዞዓር አቅጣጫ እንዳለው እንደ ግብጽ ምድር ውሃማ ቦታ ሆኖ አገኘው። እንዲህም የነበረው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነው። ሎጥ የዮርዳኖስን ረባዳ ሜዳ በሙሉ መርጦ ወደ ምሥራቅ አመራ፤ ሁለቱ ሰዎች በዚሁ ተለያዩ። አብራም መኖሪያውን በከነዓን ምድር አደረገ፤ ሎጥ ግን በረባዳው ሜዳ ውስጥ ባሉት ከተሞች መካከል በሰዶም አቅራቢያ ድንኳኑን ተከለ። የሰዶም ሰዎች ግን ክፉዎችና በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ኃጥኣን ነበሩ። ሎጥ ከተለየው በኋላ እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “ካለህበት ስፍራ ቀና ብለህ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ተመልከት፤ ዐይንህ የሚያየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁ። ዘርህን እንደ ምድር ትቢያ አበዛዋለሁ፤ ማንም የምድርን ትቢያ ሊቈጥር እንደማይችል ሁሉ የአንተም ዘር የማይቈጠር ይሆናል። እንግዲህ ምድሪቱን ስለምሰጥህ ተነሣ፤ በርዝመቷም፣ በስፋቷም ተመላለስባት።” አብራምም ድንኳኑን ነቀለ፤ ሄዶም ኬብሮን በሚገኙት ትልልቅ የመምሬ ዛፎች አጠገብ ተቀመጠ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።

ዘፍጥረት 13:8-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አብራምም ሎጥን አለው እኛ ወንድማምች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ። ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ። ሎጥም ዓይኑን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ እግዚአብሔር ገነት በግብፅ ምድር አምሳል ነበረ። ሎጥም በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን አገር ሁሉ መረጠ ሎጥም ወደ ምሥርቅ ተጓዘ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተሰያዩ። አብራም በከነዓን ምድር ተቀመጠ ሎጥም በአገሩ ሜድ ባሉት ከተሞች ተቀመጠ፥ እስከ ስዶም ሰዎች ድረስ ድንኳኑን አዘዋወረ። የሰዶም ሰዎች ግን ክፉዎችና በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ኃጢአተኞች ነበሩ። ሎጥ ከተለየው በኍላም እግዚአብሔር አብራምን አለው፤ ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁና። ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፤ የምድርን አሸዋን ይቆጥር ዘንድ የሚችል ስው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቆጠራል። ተነሣ በምድር በርዝመትዋም በስፋትዋም ሂድ እርስዋን ለአንተ እሰጣለሁና። አብራምም ድንኳኑን ነቀለ መጥቶም በኬብሮን ባለው በመምሬ የአድባር ዛፍ ተቀመጠ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ።

ዘፍጥረት 13:8-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚህ በኋላ አብራም ሎጥን እንዲህ አለው፤ “እኛ ወንድማማች ስለ ሆንን በእኔና በአንተ መካከል እንዲሁም በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ጠብ ሊነሣ አይገባም፤ ምድሪቱ ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ተለይተህ ሂድ፤ አንተ ወደ ግራ ብትሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ወደ ቀኝ ብትሄድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።” ሎጥ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ የዮርዳኖስ ሸለቆ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት ወይም እንደ ግብጽ ምድር ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ ይህን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነበር። ስለዚህ ሎጥ መላውን የዮርዳኖስን ሸለቆ ለራሱ መረጠና ወደ ምሥራቅ ሄደ፤ ሁለቱ የተለያዩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ አብራም በከነዓን ኖረ፤ ሎጥ ግን በሸለቆው ውስጥ ባሉት ከተሞች መካከል ተቀመጠ፤ በሰዶምም አጠገብ ድንኳኑን ተከለ፤ በዚያን ዘመን የሰዶም ሰዎች እጅግ ክፉዎችና እግዚአብሔርን የሚያሳዝኑ ኃጢአተኞች ነበሩ። ሎጥ ከሄደ በኋላ እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “ካለህበት ስፍራ ሆነህ ወደ ሰሜን፥ ወደ ደቡብ፥ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ተመልከት፤ ይህን የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ ለዘለዓለምም የእናንተ ይሆናል፤ ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ የምድር አሸዋ ሊቈጠር እንደማይቻል ሁሉ የአንተም ዘር እንዲሁ ሊቈጠር የማይቻል ይሆናል። ተነሥተህ በምድሪቱ ስፋትና ርዝመት ሂድ፤ ሁሉንም ለአንተ እሰጥሃለሁ።” ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቅሎ በኬብሮን የመምሬ የተቀደሱ የወርካ ዛፎች ወደአሉበት ስፍራ ለመኖር ሄደ፤ እዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።

ዘፍጥረት 13:8-18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አብራምም ሎጥን አለው፦ እኛ ወንድማማች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ። ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ፥ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፥ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ። ሎጥም ዓይኑን አነሣ፥ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፥ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ ጌታ ገነት በግብጽ ምድር አምሳል ነበረ። ሎጥም በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን አገር ሁሉ መረጠ፥ ሎጥም ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፥ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተለያዩ። አብራም በከነዓን ምድር ተቀመጠ ሎጥም በአገሩ ሜዳ ባሉት ከተሞች ተቀመጠ፥ እስከ ሰዶምም ድረስ ድንኳኑን አዘዋወረ። የሰዶም ሰዎች ግን ክፉዎችና በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ኃጢአተኞች ነበሩ። ሎጥ ከተለየው በኋላም ጌታ አብራምን አለው፦ “ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ፥ የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘለዓለም እሰጣለሁና። ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፥ የምድርን አሸዋን ይቈጥር ዘንድ የሚችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈጠራል። ተነሣ፥ በምድር በርዝመትዋም በስፋትዋም ሂድ እርሷን ለአንተ እሰጣለሁና።” አብራምም ድንኳኑን ነቀለ መጥቶም በኬብሮን ባለው በመምሬ የባሉጥ ዛፎች ተቀመጠ፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ።