የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 13

13
1አብራምም ከግብፅ ወጣ እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ አዜብ ወጡ። 2አብራምም በከብት በብርና በወርቅ እጅግ በለጠገ። 3ከአዜብ ባደረገው በጉዞውም ወደ ቤቴል በኩል ሄደ ያም ስፍራ አስቀድሞ በቤቴልና በጋይ መካከል ድንኳን ተክሎበት የነበረው ነው፤ 4ያም ስፍራ አስቀድሞ መሠውይ የሠራበት ነው በዚያም አብራም የእግዚአብሔርን ስም ጠራ። 5ከአብራም ጋር የሄደው ሎጥ ደግሞ የላምና የበግ መንጋ ድንኳንም ነበረው። 6በአንድነትም ይቀመጡ ዘንድ ምድር አልበቃቸውም የነበራቸው እጅግ ነበረና በአንድነት ሊቀመጡ አልቻሉም። 7የአብራምንና የሎጥን መንጎች በሚጠብቁት መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያም ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር። 8አብራምም ሎጥን አለው እኛ ወንድማምች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ። 9ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ። 10ሎጥም ዓይኑን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ እግዚአብሔር ገነት በግብፅ ምድር አምሳል ነበረ። 11ሎጥም በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውን አገር ሁሉ መረጠ ሎጥም ወደ ምሥርቅ ተጓዘ አንዱም ከሌላው እርስ በርሳቸው ተሰያዩ። 12አብራም በከነዓን ምድር ተቀመጠ ሎጥም በአገሩ ሜድ ባሉት ከተሞች ተቀመጠ፥ እስከ ስዶም ሰዎች ድረስ ድንኳኑን አዘዋወረ። 13የሰዶም ሰዎች ግን ክፉዎችና በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ኃጢአተኞች ነበሩ። 14ሎጥ ከተለየው በኍላም እግዚአብሔር አብራምን አለው፤ 15ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁና። 16ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፤ የምድርን አሸዋን ይቆጥር ዘንድ የሚችል ስው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቆጠራል። 17ተነሣ በምድር በርዝመትዋም በስፋትዋም ሂድ እርስዋን ለአንተ እሰጣለሁና። 18አብራምም ድንኳኑን ነቀለ መጥቶም በኬብሮን ባለው በመምሬ የአድባር ዛፍ ተቀመጠ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ