ዘፍጥረት 11:10-24
ዘፍጥረት 11:10-24 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የሴም ትውልድ ይህ ነው፦ ሁለት ዓመት ከጥፋት ውሃ በኋላ ሴም በ100 ዓመቱ አርፋክስድን ወለደ። ሴም፣ አርፋክስድን ከወለደ በኋላ 500 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። አርፋክስድ በ35 ዓመቱ ሳላን ወለደ፤ ሳላን ከወለደ በኋላ አርፋክስድ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶችን ወለደ። ሳላ በ30 ዓመቱ ዔቦርን ወለደ፤ ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሳላ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ዔቦር በ34 ዓመቱ ፋሌቅን ወለደ፤ ፋሌቅን ከወለደ በኋላ ዔቦር 430 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ፋሌቅ በ30 ዓመቱ ራግውን ወለደ፤ ራግውን ከወለደ በኋላ ፋሌቅ 209 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ራግው በ32 ዓመቱ ሴሮሕን ወለደ፤ ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ራግው 207 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ሴሮሕ በ30 ዓመቱ ናኮርን ወለደ፤ ናኮርን ከወለደ በኋላ ሴሮሕ 200 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ናኮር በ29 ዓመቱ ታራን ወለደ፤
ዘፍጥረት 11:10-24 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የሴም ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፦ ከጥፋት ውሃ በኋላ ሁለት ዓመት ቈይቶ ሴም 100 ዓመት በሆነው ጊዜ አርፋክስድ የተባለ ልጅ ወለደ፤ አርፋክስድን ከወለደ በኋላ 500 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችንና ሴቶችን ልጆች ወለደ። አርፋክስድም 35 ዓመት ሲሆነው ሳላሕን ወለደ። ከዚህ በኋላ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ሳላሕ 30 ዓመት ሲሆነው ዔቦርን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ዔቦር 34 ዓመት ሲሆነው ፋሌቅን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 430 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ፋሌቅ 30 ዓመት ሲሆነው ረዑን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 209 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ረዑ 32 ዓመት ሲሆነው ሰሩግን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 207 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ሰሩግ 30 ዓመት ሲሆነው ናኮርን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 200 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችን ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ናኮር 29 ዓመት ሲሆነው ታራን ወለደ፤
ዘፍጥረት 11:10-24 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም ከጥፋት ውኃ በኋላ በሁለተኛው ዓመት አርፋክስድን በወለደ ጊዜ የመቶ ዓመት ሰው ነበረ። ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። አርፋክስድም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ቃይናንንም ወለደ፤ አርፋክስድም ቃይናንን ከወለደ በኋላ አራት መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ቃይናንም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ሳላንም ወለደ፤ ቃይናንም ሳላን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ልጆች ወለደ፤ ሞተም። ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ዔቦርንም ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ዔቦርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፤ ፋሌቅንም ወለደ፤ ዔቦርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ራግውንም ወለደ፤ ፋሌቅም ራግውን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ሴሮሕንም ወለደ፤ ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ናኮርንም ወለደ፤ ሴሮሕም ናኮርን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ታራንም ወለደ፤
ዘፍጥረት 11:10-24 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የሴም ትውልድ ይህ ነው፦ ሁለት ዓመት ከጥፋት ውሃ በኋላ ሴም በ100 ዓመቱ አርፋክስድን ወለደ። ሴም፣ አርፋክስድን ከወለደ በኋላ 500 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። አርፋክስድ በ35 ዓመቱ ሳላን ወለደ፤ ሳላን ከወለደ በኋላ አርፋክስድ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶችን ወለደ። ሳላ በ30 ዓመቱ ዔቦርን ወለደ፤ ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሳላ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ዔቦር በ34 ዓመቱ ፋሌቅን ወለደ፤ ፋሌቅን ከወለደ በኋላ ዔቦር 430 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ፋሌቅ በ30 ዓመቱ ራግውን ወለደ፤ ራግውን ከወለደ በኋላ ፋሌቅ 209 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ራግው በ32 ዓመቱ ሴሮሕን ወለደ፤ ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ራግው 207 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ሴሮሕ በ30 ዓመቱ ናኮርን ወለደ፤ ናኮርን ከወለደ በኋላ ሴሮሕ 200 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ናኮር በ29 ዓመቱ ታራን ወለደ፤
ዘፍጥረት 11:10-24 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም የመቶ ዓመት ሰው ነበረ፥ አርፋክስድንም ከጥፋት ውኃ በኍላ በሁለተኛው ዓመት ወለደ። ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኍላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። አርፋክስድም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ቃይንምንም ወለደ፤ አርፋክስድም ቃይንምንም ከወለደ በኍላ አራት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችም ወለደ፥ ሞተም። ቃይንምም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም ሴቶቸም ወለደ፤ ሞተም። ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ዔቦርንም ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኍላ ሦስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ዔበርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፥ ፋሌቅንም ወለደ፤ ዔበርም ፋሌቅን ከወለደ በኍላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ራግውንም ወለደ፤ ራግውንም ከወለደ በኍላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችን፥ ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሴሮሕንም ወለደ፤ ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኍላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ናኮርንም ወለደ፤ ናኮርንም ከወለደ በኍላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥
ዘፍጥረት 11:10-24 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የሴም ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፦ ከጥፋት ውሃ በኋላ ሁለት ዓመት ቈይቶ ሴም 100 ዓመት በሆነው ጊዜ አርፋክስድ የተባለ ልጅ ወለደ፤ አርፋክስድን ከወለደ በኋላ 500 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችንና ሴቶችን ልጆች ወለደ። አርፋክስድም 35 ዓመት ሲሆነው ሳላሕን ወለደ። ከዚህ በኋላ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ሳላሕ 30 ዓመት ሲሆነው ዔቦርን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ዔቦር 34 ዓመት ሲሆነው ፋሌቅን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 430 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ፋሌቅ 30 ዓመት ሲሆነው ረዑን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 209 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ረዑ 32 ዓመት ሲሆነው ሰሩግን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 207 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ሰሩግ 30 ዓመት ሲሆነው ናኮርን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 200 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችን ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ናኮር 29 ዓመት ሲሆነው ታራን ወለደ፤
ዘፍጥረት 11:10-24 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የሴም ትውልድ ይህ ነው። ከጥፋት ውኃ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ሴም መቶ ዓመት በሆነው ጊዜ፥ አርፋክስድ የተባለ ልጅ ወለደ። ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ወለደ። አርፋክስድም ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ሼላሕንም ወለደ፥ አርፋክስድም ሼላሕን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፥ ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ቃይንምም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ሳላንም ወለደ፥ ቃይንምም ሳላን ከወለደ በኋላ ሶስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ዔቦርንም ወለደ፥ ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሦስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ዔቦርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፥ ፋሌቅንም ወለደ፥ ዔቦርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ራግውንም ወለደ፥ ራግውንም ከወለደ በኋላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሴሮሕንም ወለደ፥ ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ናኮርንም ወለደ፥ ናኮርንም ከወለደ በኋላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ታራንም ወለደ፥