ኦሪት ዘፍጥረት 11:10-24

ኦሪት ዘፍጥረት 11:10-24 አማ54

የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም የመቶ ዓመት ሰው ነበረ፥ አርፋክስድንም ከጥፋት ውኃ በኍላ በሁለተኛው ዓመት ወለደ። ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኍላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። አርፋክስድም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ ቃይንምንም ወለደ፤ አርፋክስድም ቃይንምንም ከወለደ በኍላ አራት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችም ወለደ፥ ሞተም። ቃይንምም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም ሴቶቸም ወለደ፤ ሞተም። ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ዔቦርንም ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኍላ ሦስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ዔበርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፥ ፋሌቅንም ወለደ፤ ዔበርም ፋሌቅን ከወለደ በኍላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ራግውንም ወለደ፤ ራግውንም ከወለደ በኍላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችን፥ ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ ሴሮሕንም ወለደ፤ ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኍላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ናኮርንም ወለደ፤ ናኮርንም ከወለደ በኍላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}