የሴም ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፦ ከጥፋት ውሃ በኋላ ሁለት ዓመት ቈይቶ ሴም 100 ዓመት በሆነው ጊዜ አርፋክስድ የተባለ ልጅ ወለደ፤ አርፋክስድን ከወለደ በኋላ 500 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችንና ሴቶችን ልጆች ወለደ። አርፋክስድም 35 ዓመት ሲሆነው ሳላሕን ወለደ። ከዚህ በኋላ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ሳላሕ 30 ዓመት ሲሆነው ዔቦርን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 403 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ዔቦር 34 ዓመት ሲሆነው ፋሌቅን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 430 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ፋሌቅ 30 ዓመት ሲሆነው ረዑን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 209 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ረዑ 32 ዓመት ሲሆነው ሰሩግን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 207 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ሰሩግ 30 ዓመት ሲሆነው ናኮርን ወለደ፤ ከዚህ በኋላ 200 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችን ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። ናኮር 29 ዓመት ሲሆነው ታራን ወለደ፤
ኦሪት ዘፍጥረት 11 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 11:10-24
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos