የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም ከጥፋት ውኃ በኋላ በሁለተኛው ዓመት አርፋክስድን በወለደ ጊዜ የመቶ ዓመት ሰው ነበረ። ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። አርፋክስድም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ቃይናንንም ወለደ፤ አርፋክስድም ቃይናንን ከወለደ በኋላ አራት መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ቃይናንም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ሳላንም ወለደ፤ ቃይናንም ሳላን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ልጆች ወለደ፤ ሞተም። ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ዔቦርንም ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ዔቦርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፤ ፋሌቅንም ወለደ፤ ዔቦርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ራግውንም ወለደ፤ ፋሌቅም ራግውን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ሴሮሕንም ወለደ፤ ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ናኮርንም ወለደ፤ ሴሮሕም ናኮርን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ ታራንም ወለደ፤
ኦሪት ዘፍጥረት 11 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 11:10-24
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች