ዘፍጥረት 1:6-25
ዘፍጥረት 1:6-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ውሃውን ከውሃ የሚለይ ጠፈር ይሁን” አለ፤ በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ጠፈርን ፈጠረ፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር “ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉት ውሆች ይለያዩ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ፥ ሌሊቱም ነጋ፤ ሁለተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “የብሱ ግልጥ ሆኖ እንዲታይ ከሰማይ በታች ያለው ውሃ ሁሉ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” ብሎ ሰየመው፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር አትክልትን፥ የእህል አዝርዕትን፥ ፍሬ የሚያፈሩ የፍሬ ዛፎችንና ተክሎችን በየዐይነቱ ታብቅል” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። በዚህ ዐይነት ምድር አትክልትን፥ በየዐይነቱ የእህል አዝርዕትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን አበቀለች፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ ሦስተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ቀንን ከሌሊት ለመለየት ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ ይሁኑ፤ ለዕለታት፥ ለክፍላተ ዓመትና ለዓመታት መለያ ምልክት ይሁኑ፤ ለምድር ብርሃን ለመስጠት በሰማይ ጠፈር ላይ ሆነው ያብሩ” እንዲሁም ሆነ። በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን ፈጠረ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን፥ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲያበሩ አደረገ፤ እንዲሁም ከዋክብትን ፈጠረ፤ ለምድር ብርሃንን እንዲሰጡ እነዚህን ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ አኖራቸው፤ ይህንንም ያደረገው በቀንና በሌሊት ላይ ሥልጣን እንዲኖራቸውና ጨለማን ከብርሃን እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ አራተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ውሃ ሕይወት ባላቸው በልዩ ልዩ ፍጥረቶች የተሞላ ይሁን፤ ወፎችም ከምድር በላይ ባለው በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ። በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ታላላቅ የባሕር አውሬዎችን፥ ሌሎችንም በውሃ ውስጥ የሚኖሩና የሚንቀሳቀሱ ልዩ ልዩ ፍጥረቶችን እንደየዐይነታቸው፥ እንዲሁም ልዩ ልዩ ወፎችን እንደየዐይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። እግዚአብሔር “ብዙ ተባዙ፤ ዘራችሁ የባሕርን ውሃ ይሙላ፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ አምስተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር ሕይወት ያላቸው ፍጥረቶችን፥ እንደየዐይነታቸው እንስሶችን፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችንና አራዊትን እንደየዐይነታቸው ታስገኝ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር የምድር አራዊትን በየዐይነቱ፥ እንስሶችን በየዐይነታቸው በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችን በየዐይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ።
ዘፍጥረት 1:6-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር፣ “ውሃን ከውሃ የሚለይ ጠፈር በውሆች መካከል ይሁን” አለ። ስለዚህ እግዚአብሔር ጠፈርን አድርጎ ከጠፈሩ በላይና ከጠፈሩ በታች ያለውን ውሃ ለየ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። መሸ፤ ነጋም፤ ሁለተኛ ቀን። ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ ደረቁ ምድር ይገለጥ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር ደረቁን ምድር፣ “የብስ”፣ በአንድነት የተሰበሰበውን ውሃ፣ “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔር፣ “ምድር ዕፀዋትንም፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በምድር ላይ ዘር ያዘሉ ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ታብቅል” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። ምድር ዕፀዋትን፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በውስጣቸው ዘር ያለባቸው ፍሬ የሚያፈሩትን ዛፎች በየወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። መሸ፤ ነጋም፤ ሦስተኛ ቀን። ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ቀኑን ከሌሊት እንዲለዩ፣ የዓመት ወቅቶች፣ ቀናትና ዓመታት የሚጀምሩበትንም እንዲያመለክቱ፣ ለምድር ብርሃን የሚሰጡ ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ይሁኑ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር፣ ለምድር ብርሃን ይሰጡ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናት አደረገ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፣ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲሠለጥን አደረገ። እንዲሁም ከዋክብትን አደረገ። ለምድር ብርሃን እንዲሰጡ እግዚአብሔር እነዚህን በሰማይ ጠፈር አኖራቸው። ይኸውም በቀንና በሌሊት እንዲሠለጥኑ፣ ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። መሸ፤ ነጋም፣ አራተኛ ቀን። እግዚአብሔር፣ “ውሆች ሕይወት ባላቸው በሕያዋን ፍጥረታት ይሞሉ፤ ወፎች ከምድር በላይ በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ። በዚህ መሠረት፣ እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ የሚኖሩ ታላላቅ ፍጥረታትን፣ በውሃ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ እንደየወገናቸው እንዲሁም ክንፍ ያላቸውን ወፎች ሁሉ እንደየወገናቸው ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ የባሕርንም ውሃ ሙሏት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው። መሸ፤ ነጋም፤ ዐምስተኛ ቀን። እግዚአብሔር፣ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትንና የዱር እንስሳትን እያንዳንዱን እንደ ወገኑ ታስገኝ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን እንደየወገናቸው፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን እንደየወገናቸው አደረገ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።
ዘፍጥረት 1:6-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም፤ በዉኖች መካከል ጠፈር ይሁን በዉኂ መካከል ይከፈል አለ። እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፤ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኖች ለየ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን ሰማይ ብሎ ጠራዉ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ ሁሉተኚ ቀን። እግዚአብሔርም፤ ከሰማይ በታች ያለዉ ውኂ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የብሱን ምድር ብሎ ጠራዉ የዉኂ መከማቻዉንም ባሕር አለዉ፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም፤ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ። ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ሦስተኚ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፤ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ እንዲሁም ሆነ። እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን ከዋክብትም ደግሞ አደረገ። እግዚአሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር አኖራቸው፤ በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ አራተኚ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፤ ዉኂ ሕያዉ ነፍስ ያላቸዉን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ። እግዚእብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን ውኂይቱ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚእብሔርም እንድህ ብሎ ባረካቸው፤ ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኂ ሙሉአት ውፎችም በምድር ላይ ይብዙ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ አምስተኚ ቀን። እግዚአብሔርም አለ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ ታዉጣ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ አደረገ እንስሳዉንም እንደ ወገኑ የመሬት ተንቀሳቃሾችም እንደ ወገኑ አደረገ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።
ዘፍጥረት 1:6-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም፥ “በውኃው መካከል ጠፈር ይሁን፤ በውኃና በውኃ መካከልም ይለይ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፤ ከጠፈር በላይና ከጠፈር በታች ያሉትንም ውኆች ለየ። እግዚአብሔር ያን ጠፈር “ሰማይ” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ሁለተኛም ቀን ሆነ። እግዚአብሔርም ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ። ከሰማይ በታች ያለው ውኃም በመጠራቀሚያው ተሰበሰበ፤ የብሱም ተገለጠ። እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ የውኃ መጠራቀሚያውንም “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። እግዚአብሔርም “ምድር በየዘሩ፥ በየወገኑና በየመልኩ ዘር የሚሰጥ ቡቃያን፥ በምድርም ላይ በየወገኑ ዘሩ በውስጡ የሚገኘውንና ፍሬ የሚያፈራውን ዛፍ ታብቅል” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። ምድርም በየዘሩ፥ በየወገኑና በየመልኩ የሚዘራ ቡቃያን፥ በምድር ላይ በየወገኑ ዘሩ በውስጡ የሚገኘውንና ፍሬ የሚያፈራውን ዛፍ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ። ሦስተኛም ቀን ሆነ። እግዚአብሔርም አለ፥ “በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በቀንና በሌሊትም ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች፥ ለዘመናት፥ ለዕለታት፥ ለዓመታትም ይሁኑ። በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በሰማይ ጠፈር ለማብራት ይሁኑ፤” እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን ቀንን እንዲመግብ፥ ትንሹ ብርሃንም ከከዋክብት ጋር ሌሊትን እንዲመግብ አደረገ። እግዚአብሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር አኖራቸው፤ መዓልትንና ሌሊትንም እንዲመግቡ፥ በመዓልትና በሌሊትም መካከል እንዲለዩ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ አራተኛም ቀን ሆነ። እግዚአብሔርም አለ፥ “ውኃ የሕይወት እስትንፋስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾችና በምድር ላይ ከሰማይ በታች የሚበርሩ አዕዋፍን ታስገኝ፥” እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም ታላላቅ አንበሪዎችን፥ ውኃ ያስገኘውን ተንቀሳቃሽ ሕያው ፍጥረትን ሁሉ በየወገኑ፥ የሚበርሩ አዕዋፍንም ሁሉ በየወገናቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙም፤ የባሕርንም ውኃ ሙሉአት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ።” ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ አምስተኛም ቀን ሆነ። እግዚአብሔርም አለ፥ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን፥ የምድር አራዊትንም እንደየወገኑ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የምድር አራዊትን እንደየወገኑ፥ እንስሳትንም እንደየወገኑ፥ በምድር የሚንቀሳቀሰውንም ሁሉ እንደየወገኑ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ዘፍጥረት 1:6-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር፣ “ውሃን ከውሃ የሚለይ ጠፈር በውሆች መካከል ይሁን” አለ። ስለዚህ እግዚአብሔር ጠፈርን አድርጎ ከጠፈሩ በላይና ከጠፈሩ በታች ያለውን ውሃ ለየ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። መሸ፤ ነጋም፤ ሁለተኛ ቀን። ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ ደረቁ ምድር ይገለጥ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር ደረቁን ምድር፣ “የብስ”፣ በአንድነት የተሰበሰበውን ውሃ፣ “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔር፣ “ምድር ዕፀዋትንም፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በምድር ላይ ዘር ያዘሉ ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን እንደየወገናቸው ታብቅል” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። ምድር ዕፀዋትን፣ እንደየወገናቸው ዘር የሚሰጡ ተክሎችንና በውስጣቸው ዘር ያለባቸው ፍሬ የሚያፈሩትን ዛፎች በየወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። መሸ፤ ነጋም፤ ሦስተኛ ቀን። ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ቀኑን ከሌሊት እንዲለዩ፣ የዓመት ወቅቶች፣ ቀናትና ዓመታት የሚጀምሩበትንም እንዲያመለክቱ፣ ለምድር ብርሃን የሚሰጡ ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ይሁኑ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር፣ ለምድር ብርሃን ይሰጡ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናት አደረገ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፣ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲሠለጥን አደረገ። እንዲሁም ከዋክብትን አደረገ። ለምድር ብርሃን እንዲሰጡ እግዚአብሔር እነዚህን በሰማይ ጠፈር አኖራቸው። ይኸውም በቀንና በሌሊት እንዲሠለጥኑ፣ ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። መሸ፤ ነጋም፣ አራተኛ ቀን። እግዚአብሔር፣ “ውሆች ሕይወት ባላቸው በሕያዋን ፍጥረታት ይሞሉ፤ ወፎች ከምድር በላይ በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ። በዚህ መሠረት፣ እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ የሚኖሩ ታላላቅ ፍጥረታትን፣ በውሃ ውስጥ የሚርመሰመሱ ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ እንደየወገናቸው እንዲሁም ክንፍ ያላቸውን ወፎች ሁሉ እንደየወገናቸው ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ የባሕርንም ውሃ ሙሏት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው። መሸ፤ ነጋም፤ ዐምስተኛ ቀን። እግዚአብሔር፣ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትንና የዱር እንስሳትን እያንዳንዱን እንደ ወገኑ ታስገኝ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ። እግዚአብሔር የዱር እንስሳትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን እንደየወገናቸው፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትን እንደየወገናቸው አደረገ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም እንደ ሆነ አየ።
ዘፍጥረት 1:6-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም፤ በዉኖች መካከል ጠፈር ይሁን በዉኂ መካከል ይከፈል አለ። እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፤ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኖች ለየ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን ሰማይ ብሎ ጠራዉ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ ሁሉተኚ ቀን። እግዚአብሔርም፤ ከሰማይ በታች ያለዉ ውኂ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የብሱን ምድር ብሎ ጠራዉ የዉኂ መከማቻዉንም ባሕር አለዉ፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም፤ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ። ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ሦስተኚ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፤ ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፤ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ እንዲሁም ሆነ። እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን ከዋክብትም ደግሞ አደረገ። እግዚአሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር አኖራቸው፤ በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ አራተኚ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፤ ዉኂ ሕያዉ ነፍስ ያላቸዉን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ። እግዚእብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን ውኂይቱ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፤ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። እግዚእብሔርም እንድህ ብሎ ባረካቸው፤ ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኂ ሙሉአት ውፎችም በምድር ላይ ይብዙ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፤ አምስተኚ ቀን። እግዚአብሔርም አለ ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ ታዉጣ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ አደረገ እንስሳዉንም እንደ ወገኑ የመሬት ተንቀሳቃሾችም እንደ ወገኑ አደረገ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ።
ዘፍጥረት 1:6-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ውሃውን ከውሃ የሚለይ ጠፈር ይሁን” አለ፤ በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ጠፈርን ፈጠረ፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር “ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉት ውሆች ይለያዩ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ፥ ሌሊቱም ነጋ፤ ሁለተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “የብሱ ግልጥ ሆኖ እንዲታይ ከሰማይ በታች ያለው ውሃ ሁሉ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” ብሎ ሰየመው፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር አትክልትን፥ የእህል አዝርዕትን፥ ፍሬ የሚያፈሩ የፍሬ ዛፎችንና ተክሎችን በየዐይነቱ ታብቅል” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። በዚህ ዐይነት ምድር አትክልትን፥ በየዐይነቱ የእህል አዝርዕትንና ዘር በውስጡ ያለውን ፍራፍሬ የሚያስገኙ ተክሎችን አበቀለች፤ እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ ሦስተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ቀንን ከሌሊት ለመለየት ልዩ ልዩ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ ይሁኑ፤ ለዕለታት፥ ለክፍላተ ዓመትና ለዓመታት መለያ ምልክት ይሁኑ፤ ለምድር ብርሃን ለመስጠት በሰማይ ጠፈር ላይ ሆነው ያብሩ” እንዲሁም ሆነ። በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን ፈጠረ፤ ታላቁ ብርሃን በቀን፥ ታናሹ ብርሃን በሌሊት እንዲያበሩ አደረገ፤ እንዲሁም ከዋክብትን ፈጠረ፤ ለምድር ብርሃንን እንዲሰጡ እነዚህን ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ላይ አኖራቸው፤ ይህንንም ያደረገው በቀንና በሌሊት ላይ ሥልጣን እንዲኖራቸውና ጨለማን ከብርሃን እንዲለዩ ነው። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ አራተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ውሃ ሕይወት ባላቸው በልዩ ልዩ ፍጥረቶች የተሞላ ይሁን፤ ወፎችም ከምድር በላይ ባለው በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ። በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ታላላቅ የባሕር አውሬዎችን፥ ሌሎችንም በውሃ ውስጥ የሚኖሩና የሚንቀሳቀሱ ልዩ ልዩ ፍጥረቶችን እንደየዐይነታቸው፥ እንዲሁም ልዩ ልዩ ወፎችን እንደየዐይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ። እግዚአብሔር “ብዙ ተባዙ፤ ዘራችሁ የባሕርን ውሃ ይሙላ፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱም ነጋ፤ አምስተኛ ቀን ሆነ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ምድር ሕይወት ያላቸው ፍጥረቶችን፥ እንደየዐይነታቸው እንስሶችን፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችንና አራዊትን እንደየዐይነታቸው ታስገኝ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር የምድር አራዊትን በየዐይነቱ፥ እንስሶችን በየዐይነታቸው በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችን በየዐይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ።
ዘፍጥረት 1:6-25 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እግዚአብሔርም፦ “በውኆች መካከል ጠፈር ይሁን፥ በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል” አለ። እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፥ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኆች ለየ፥ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር ጠፈርን “ሰማይ” ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሁለተኛ ቀን ሆነ። እግዚአብሔርም፦ “ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፥ በአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ “ባሕር” አለው፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። እግዚአብሔርም፦ “ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል” አለ፥ እንዲሁም ሆነ። ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሦስተኛ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፦ “ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፥ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ፥ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ፥” እንዲሁም ሆነ። እግዚእብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ፥ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን፥ ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ። እግዚአሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር አኖራቸው፥ በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ፥ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አራተኛ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፦ “ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፥ ወፎችም ከምድር በላይ ከሰማይ ጠፈር በታች ይብረሩ።” እግዚእብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን፥ ውኃይቱ እንደ ወገኑ ያስገኘቻቸውን ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፥ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፥ እግዚእብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። እግዚእብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፦ “ብዙ ተባዙም የባሕርንም ውኃ ሙሉአት፥ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ።” ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አምስተኛ ቀን። እግዚአብሔርም አለ፦ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን የምድር አራዊትንም እንደ ወገኑ፥ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ። እግዚአብሔር የምድር አራዊትን እንደ ወገኑ አደረገ፥ እንስሳውንም እንደ ወገኑ፥ የመሬት ተንቀሳቃሾችንም እንደ ወገኑ አደረገ፥ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።