ገላትያ 6:2-3
ገላትያ 6:2-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከእናንተ እያንዳንዱ የባልንጀራውን ሸክም ይሸከም፤ በዚህም የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ። አንዱም ምንም ሳይሆን ምንም የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና።
ያጋሩ
ገላትያ 6 ያንብቡገላትያ 6:2-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህም ሁኔታ የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ። አንድ ሰው ምንም ሳይሆን ትልቅ የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላል።
ያጋሩ
ገላትያ 6 ያንብቡገላትያ 6:2-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ። አንዱ ምንም ሳይሆን ምንም የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና።
ያጋሩ
ገላትያ 6 ያንብቡገላትያ 6:2-3 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከእናንተ እያንዳንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህ ዐይነት የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ። ማንም ሰው ከሌሎች የሚሻልበት ነገር ሳይኖረው “እኔ ከሌሎች እበልጣለሁ” ብሎ ቢያስብ ራሱን ያታልላል።
ያጋሩ
ገላትያ 6 ያንብቡ