የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዕዝራ 8:21-36

ዕዝራ 8:21-36 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በአ​ም​ላ​ካ​ችን ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ዋ​ርድ ዘንድ፥ ከእ​ር​ሱም የቀ​ና​ውን መን​ገድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን፥ ለን​ብ​ረ​ታ​ች​ንም ሁሉ እን​ለ​ምን ዘንድ በዚያ በአ​ኅዋ ወንዝ አጠ​ገብ ጾምን አወ​ጅሁ። ንጉ​ሡ​ንም፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ችን እጅ በሚ​ሹት ሁሉ ላይ ለመ​ል​ካም ነው፤ ኀይ​ሉና ቍጣው ግን እር​ሱን በሚ​ተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተና​ግ​ረን ነበ​ርና፤ በመ​ን​ገድ ካለው ጠላት ያድ​ኑን ዘንድ ጭፍ​ራና ፈረ​ሰ​ኞች ከን​ጉሡ እለ​ምን ዘንድ አፍሬ ነበ​ርና። ስለ​ዚ​ህም ነገር ጾምን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ንን፤ እር​ሱ​ም​ሰ​ማን። ከካ​ህ​ና​ቱም አለ​ቆች ዐሥራ ሁለት ሰዎ​ችን፥ ሰራ​ብ​ያ​ንና ሐሳ​ብ​ያን፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ዐሥር ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ለየሁ፤ ንጉ​ሡና አማ​ካ​ሪ​ዎቹ፥ አለ​ቆ​ቹም፥ በዚ​ያም የተ​ገ​ኙት እስ​ራ​ኤል ሁሉ ያቀ​ረ​ቡ​ትን፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት የቀ​ረ​በ​ውን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ ዕቃ​ው​ንም መዝኜ ሰጠ​ኋ​ቸው። ስድ​ስት መቶ አምሳ መክ​ሊት ብር፥ አንድ መቶም መክ​ሊት የብር ዕቃ​ዎች፥ አንድ መቶም መክ​ሊት ወርቅ፥ ሃያም ባለ ሺህ ዳሪክ የወ​ርቅ ጽዋ​ዎች፥ ሁለ​ትም እንደ ወርቅ የከ​በሩ ከጥ​ሩና ከሚ​ያ​ን​ጸ​በ​ርቅ ናስ የተ​ሠሩ ዕቃ​ዎ​ችን መዝኜ በእ​ጃ​ቸው ሰጠሁ። እኔም “እና​ንተ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀ​ድ​ሳ​ች​ኋል፤ ዕቃ​ዎ​ቹም ቅዱ​ሳን ናቸው፤ ብሩና ወር​ቁም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃድ የቀ​ረበ ነው፤ በካ​ህ​ና​ትና በሌ​ዋ​ው​ያን አለ​ቆች፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጓዳ​ዎች ውስጥ እስ​ክ​ት​መ​ዝኑ ድረስ ተግ​ታ​ችሁ ጠብቁ” አል​ኋ​ቸው። ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም በሚ​ዛን ተቀ​በሉ። በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ሄድ ዘንድ ከአ​ኅዋ ወንዝ ተነ​ሣን፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም እጅ በላ​ያ​ችን ነበረ፤ በመ​ን​ገ​ድም ከጠ​ላ​ትና ከሚ​ሸ​ምቅ ሰው እጅ አዳ​ነን። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን ተቀ​መ​ጥን። በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን ብሩና ወርቁ፥ ዕቃ​ዎ​ቹም በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት በካ​ህኑ በኦ​ርያ ልጅ በሜ​ሪ​ሞት እጅ ተመ​ዘኑ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የፊ​ን​ሐስ ልጅ አል​ዓ​ዛር ነበረ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሌዋ​ው​ያን የኢ​ያሱ ልጅ ኢዮ​ዛ​ብ​ድና የቤ​ንዊ ልጅ ናሕ​ድያ ነበሩ። ሁሉም በቍ​ጥ​ርና በሚ​ዛን ተመ​ዘነ፤ ሚዛ​ኑም ሁሉ በዚያ ጊዜ ተጻፈ። ከም​ር​ኮም የወ​ጡት የም​ር​ኮ​ኞች ልጆች ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ስለ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይ​ፈ​ኖች፥ ዘጠና ስድ​ስ​ትም አውራ በጎች፥ ሰባ ሰባ​ትም ጠቦ​ቶች፥ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየ​ሎ​ችን አቀ​ረቡ። ይህ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነበረ። የን​ጉ​ሡ​ንም ትእ​ዛዝ በወ​ንዙ ማዶ ላሉት ለን​ጉሡ ሹሞ​ችና ገዢ​ዎች ሰጡ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝ​ቡ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አከ​በሩ።

ዕዝራ 8:21-36 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ራሳችንን በአምላካችን ፊት ዝቅ እንድናደርግ፣ ጕዞውም ለእኛና ለልጆቻችን፣ ለንብረታችንም ሁሉ የተቃና እንዲሆንልን፣ እዚያው በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም ዐወጅሁ። “መልካሚቱ የአምላካችን እጅ በሚፈልጉት ሁሉ ላይ ናት፤ እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ግን ቍጣው ትወርድባቸዋለች” ብለን ለንጉሡ ነግረነው ስለ ነበር፣ በመንገድ ላይ ከጠላት የሚጠብቁን ወታደሮችንና ፈረሰኞችን እንዲሰጠን ንጉሡን ለመጠየቅ ዐፍሬ ነበር። ስለዚህ ጾምን፤ ወደ አምላካችንም ስለዚህ ነገር ልመና አቀረብን፤ እርሱም ጸሎታችንን ሰማ። እኔም ከዋና ዋናዎቹ ካህናትም ዐሥራ ሁለት ሰዎችን፣ ከእነርሱም ጋር ሰራብያን፣ ሐሸቢያንና ከወንድሞቻቸውም መካከል ዐሥር ሰዎችን ለየሁ፤ ንጉሡ፣ አማካሪዎቹ፣ ሹሞቹና በዚያ የነበሩ እስራኤል ሁሉ ለአምላካችን ቤት የሰጡትን ብር፣ ወርቅና ዕቃ ሁሉ መዝኜ ሰጠኋቸው። ስድስት መቶ አምሳ መክሊት ብር፣ አንድ መቶ መክሊት የብር ዕቃዎች፣ አንድ መቶ መክሊት ወርቅ፣ አንድ ሺሕ ዳሪክ የሚያወጡ ሃያ የወርቅ ወጭቶችና እንደ ወርቅ ነጥረው ከሚያብረቀርቅ ናስ የተሠሩ ሁለት ዕቃዎችን መዝኜ በእጃቸው አስረከብኋቸው። እንዲህም አልኋቸው፤ “እናንተና እነዚህ ዕቃዎች ለእግዚአብሔር ተቀድሳችኋል፤ ብሩና ወርቁ ለአባቶቻችሁ አምላክ ለእግዚአብሔር በበጎ ፈቃድ የቀረበ መባ ነው። ኢየሩሳሌም በሚገኘው በእግዚአብሔር ቤት ክፍሎች ውስጥ በዋና ዋናዎቹ ካህናት፣ በሌዋውያኑና በየቤተ ሰቡ የእስራኤል አለቆች ፊት እስክትመዝኗቸው ድረስ በጥንቃቄ ጠብቋቸው።” ከዚያም ካህናቱና ሌዋውያኑ ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ አምላካችን ቤት እንዲሄድ የተመዘነውን ብር፣ ወርቅና ንዋያተ ቅድሳት ተረከቡ። እኛም በመጀመሪያው ወር ዐሥራ ሁለተኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ከአኅዋ ወንዝ ተነሣን። የአምላካችን እጅ በላያችን ነበረች፤ እርሱም ከጠላቶቻችንና በመንገድ ላይ ከሚሸምቁ አዳነን። ኢየሩሳሌምም ደረስን፤ በዚያም ሦስት ቀን ዐረፍን። በአራተኛው ቀን ብሩን፣ ወርቁንና ንዋያተ ቅድሳቱን በአምላካችን ቤት መዝነን ለኦሪዮ ልጅ ለካህኑ ለሜሪሞት በእጁ አስረከብነው፤ ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር፣ ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ። ሁሉም ነገር ተቈጠረ፤ ተመዘነም፤ የተመዘነውም ሁሉ በዚያኑ ጊዜ ተመዘገበ። ከዚያም ከምርኮ የተመለሱት፣ ለእስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይፈኖችን፣ ዘጠና ስድስት አውራ በጎችን፣ ሰባ ሰባት ተባዕት ጠቦቶችን፣ ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ ለኀጢአት መሥዋዕት ደግሞ ዐሥራ ሁለት ተባዕት ፍየሎችን አቀረቡ። ይህም ሁሉ ለእግዚአብሔር የቀረበ የሚቃጠል መሥዋዕት ነበር። የንጉሡንም ትእዛዝ ለንጉሡ እንደራሴዎችና በኤፍራጥስ ማዶ ለሚገኙት አገረ ገዦች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት ረዱ።

ዕዝራ 8:21-36 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ። ንጉሡንም፦ “የአምላካችን እጅ በሚሹት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፤ ኃይሉና ቍጣው ግን እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተናግረን ነበርና በመንገድ ካለው ጠላት ያድኑን ዘንድ ጭፍራና ፈረሰኞች ከንጉሡ እለምን ዘንድ አፍሬ ነበርና። ስለዚህም ነገር ጾምን፤ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን፤ እርሱም ተለመነን። ከካህናቱም አለቆች አሥራ ሁለት ሰዎችን፥ ሰራብያንና ሐሸቢያን ከእነርሱም ጋር አሥር ወንድሞቻቸውን ለየሁ፤ ንጉሡና አማካሪዎቹ፥ አለቆቹና በዚያም የተገኙት እስራኤል ሁሉ ያቀረቡትን ለአምላካችን ቤት የቀረበውን ብሩንና ወርቁን ዕቃውንም መዝኜ ሰጠኋቸው። ስድስት መቶ አምሳ መክሊት ብር፥ አንድ መቶም መክሊት የብር ዕቃዎች፥ አንድ መቶም መክሊት ወርቅ፥ ሀያም ባለሺህ ዳሪክ የወርቅ ጽዋዎች፥ ሁለትም እንደ ወርቅ የከበሩ ከጥሩ ከሚያንጸባርቅ ናስ የተሠሩ ዕቃዎች መዝኜ በእጃቸው ሰጠሁ። እኔም፦ “እናንተ ለእግዚአብሔር ተቀድሳችኋል፤ ዕቃዎቹም ቅዱስ ናቸው፤ ብሩና ወርቁም ለአባቶቻችን አምላክ ለእግዚአብሔር በፈቃድ የቀረበ ነው፤ በካህናትና በሌዋውያን አለቆች፥ በእስራኤልም አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ቤት ጓዳዎች ውስጥ እስክትመዝኑ ድረስ ተግታችሁ ጠብቁ” አልኋቸው። ካህናቱና ሌዋውያኑም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አምላካችን ቤት ይወስዱት ዘንድ ብሩንና ወርቁን፥ ዕቃዎቹንም በሚዛን ተቀበሉ። በመጀመሪያውም ወር በአሥራ ሁለተኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም እንሄድ ዘንድ ከአኅዋ ወንዝ ተነሣን፤ የአምላካችንም እጅ በላያችን ነበረ፤ በመንገድም ከጠላትና ከሚሸምቅ ሰው እጅ አዳነን። ወደ ኢየሩሳሌም ደረስን፤ በዚያም ሦስት ቀን ተቀመጥን። በአራተኛውም ቀን ብሩና ወርቁ፥ ዕቃዎቹም በአምላካችን ቤት በካህኑ በኦርዮ ልጅ በሜሪሞት እጅ ተመዘኑ፤ ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ። ከእነርሱም ጋር ሌዋውያን የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ። ሁሉም በቍጥርና በሚዛን ተመዘነ፤ ሚዛኑም ሁሉ በዚያን ጊዜ ተጻፈ። ከምርኮም የወጡት ምርኮኞች ለእስራኤል አምላክ ለሚቃጠል መሥዋዕት ስለ እስራኤል ሁሉ አሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ ዘጠና ስድስት አውራ በጎች፥ ሰባ ሰባት ጠቦቶችና ለኃጢአት መሥዋዕት አሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ። ይህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ። የንጉሡንም ትእዛዝ በወንዝ ማዶ ላሉት ለንጉሡ ሹማምቶችና ገዦች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት አገዙ።

ዕዝራ 8:21-36 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ጒዞአችንን እንዲያቃናልን፥ እኛንና ልጆቻችንን፥ እንዲሁም ንብረታችንን ሁሉ እንዲጠብቅልን በእርሱ ፊት ራሳችንን ዝቅ አድርገን እንለምነው ዘንድ በዚያው በአሀዋ ወንዝ አጠገብ ጾም ዐወጅኩ። ከዚህ በፊት ለንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ ባስረዳሁት ጊዜ “አምላካችን እግዚአብሔር በእርሱ የሚታመኑትን ሁሉ ይባርካል፤ እርሱን የሚተዉትን ግን በብርቱ ይቀጣቸዋል” በማለት ገልጬለት ስለ ነበረ በመንገድ ከሚገጥሙን ጠላቶቻችን እንዲጠብቁን ወታደሮችንና ፈረሰኞችን ይሰጠን ዘንድ ንጉሡን ጠይቄው ቢሆን ኖሮ ባፈርኩ ነበር። ስለዚህም እግዚአብሔር ራሱ እንዲጠብቀን በጾምና በጸሎት ተማጠንነው፤ እርሱም ጸሎታችንን ሰማ። መሪዎች ከሆኑት ካህናት መካከል ሼሬብያን፥ ሐሻብያንና ሌሎችንም ዐሥር ሰዎች መረጥሁ፤ ከዚህ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ፥ አማካሪዎቹ፥ ባለሟሎቹና በዚያ የተገኙት እስራኤላውያን ለቤተ መቅደስ መገልገያ ይሆን ዘንድ የሰጡትን ብር፥ ወርቅና ሌሎቹንም ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ በሚዛን መዝኜ ለእነዚህ ካህናት አስረከብኳቸው። ያስረከብኳቸውም የቤተ መቅደስ ንብረት ከዚህ የሚከተለው ነው፦ 22000 ኪሎ የሚመዝን ብር፥ 70 ኪሎ የሚመዝኑ አንድ መቶ ከብር የተሠሩ ዕቃዎች፥ 3400 ኪሎ የሚመዝን ወርቅ፥ 8 ኪሎ ከ 400 ግራም የሚመዝኑ ኻያ ከወርቅ የተሠሩ ወጭቶች፥ ከወርቅ ከተሠሩት ወጭቶች ጋር እኩል ዋጋ ያላቸው ከንጹሕ ነሐስ የተሠሩ ሁለት ወጭቶች። እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ “እነሆ እናንተ ለቀድሞ አባቶቻችን አምላክ ለእግዚአብሔር የተለያችሁ ናችሁ፤ እንዲሁም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ሆነው የቀረቡት ከብርና ከወርቅ የተሠሩት ዕቃዎች ሁሉ ለቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ ለእግዚአብሔር የበጎ ፈቃድ መባ ናቸው። ወደ ቤተ መቅደስ መግባት እስኪችሉ ድረስ በጥንቃቄ ጠብቁአቸው፤ እዚያም ለካህናቱ በተመደበው ክፍል ውስጥ እነዚህን ሁሉ ንዋያተ ቅድሳት መዝናችሁ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ መሪዎች እንዲሁም በኢየሩሳሌም ለሚገኙት የሕዝቡ መሪዎች አስረክቡአቸው።” ስለዚህም ካህናቱና ሌዋውያኑ ብሩንና ወርቁን፥ ጠቅላላውንም ንዋያተ ቅድሳት ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ለመውሰድ ኀላፊነትን ተረከቡ። ከአሀዋ ወንዝ ተነሥተን ወደ ኢየሩሳሌም ጒዞ የጀመርነውም የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ነበር፤ በምንጓዝበትም ጊዜ አምላካችን ከእኛ ጋር ስለ ነበር ከጠላት አደጋና ከደፈጣ ተዋጊዎች ሽመቃ ጠበቀን። ኢየሩሳሌም በደረስንም ጊዜ በዚያ የሦስት ቀኖች ዕረፍት አደረግን፤ ከዚህም በኋላ በአራተኛው ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ሄድን፤ ብሩን፥ ወርቁንና ንዋያተ ቅድሳቱንም ሁሉ መዝነን ለኡሪያ ልጅ ለካህኑ ለመሬሞት አስረከብነው፤ የፊንሐስ ልጅ አልዓዛርና እንዲሁም ሌዋውያኑ ዮዛባድ ተብሎ የሚጠራው የኢያሱ ልጅና ኖዓዲያ ተብሎ የሚጠራው የቢኑይ ልጅ ከእርሱ ጋር አብረው ነበሩ። ሁሉም ነገር በዚያኑ ሰዓት ተቈጥሮና ተመዝኖ በትክክል ተመዘገበ። ከዚያም ቀጥሎ እነዚያ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን መባ ሁሉ አመጡ፤ በዚህ ዐይነት በመላው እስራኤል ሕዝብ ስም ዐሥራ ሁለት ኰርማዎችን፥ ዘጠና ስድስት የበግ አውራዎችንና ሰባ ሰባት የበግ ጠቦቶችን አቀረቡ፤ እንዲሁም ስለ ኃጢአታቸው ስርየት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎችን አቀረቡ፤ እነዚህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበሩ። ንጉሠ ነገሥቱ የሰጣቸውንም ሰነድ በኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ላሉት ገዢዎችና ባለሥልጣኖች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ በማገዝ ድጋፋቸውን ሰጡ።

ዕዝራ 8:21-36 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በአምላካችን ፊት ራሳችንን ዝቅ እንድናደርግ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንድንለምን በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ። ንጉሡንም፦ “የአምላካችን እጅ በሚፈልጉት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፥ ኃይሉና ቁጣውም እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተናግረን ነበርና በመንገድ ካለው ጠላት እንዲያድኑን ወታደሮችና ፈረሰኞች ከንጉሡ ለመጠየቅ አፍሬ ነበር። ጾምን፥ አምላካችንን ስለዚህ ነገር ለመንን፤ እርሱም ልመናችንን ሰማ። ከካህናቱ መሪዎች ዐሥራ ሁለት ሰዎችን፥ ሼሬብያን፥ ሐሻብያንና ከእነርሱም ጋር ዐሥር ወንድሞቻቸውን ለየሁ፤ ንጉሡ፥ አማካሪዎቹ፥ ባለሥልጣናቱ በዚያም የተገኙት እስራኤል ሁሉ፤ ለአምላካችን ቤት የሰጡትን የብሩንና፥ የወርቁን፥ የዕቃውንም ስጦታ መዝኜ ሰጠኋቸው። ስድስት መቶ ሃምሳ መክሊት ብር፥ አንድ መቶ መክሊት የብር ዕቃዎች፥ አንድ መቶ መክሊት ወርቅ፥ አንድ ሺህ ዳሪክ የሚያወጡ ሀያ የወርቅ ሳሕኖች፥ ሁለት እንደ ወርቅ የከበሩ ከጥሩ ከሚያንጸበርቅ ናስ የተሠሩ ዕቃዎች መዝኜ በእጃቸው ሰጠኋቸው። እኔም አልኋቸው፦ “እናንተ ለጌታ ተቀድሳችኋል፥ ዕቃዎቹም ቅዱስ ናቸው፤ ብሩና ወርቁም ለአባቶቻችን አምላክ ለጌታ በበጎ ፈቃድ የቀረበ መባ ነው፤ በካህናት አለቆች፥ በሌዋውያን በእስራኤል አባቶች አለቆች ፊት በኢየሩሳሌም በጌታ ቤት ክፍሎች ውስጥ እስክትመዝኑ ድረስ በጥንቃቄ ጠብቋቸው።” ካህናቱና ሌዋውያኑም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አምላካችን ቤት ለመውሰድ ብሩንና ወርቁን ዕቃዎቹንም በሚዛን ተቀበሉ። በመጀመሪያው ወር በዓሥራ ሁለተኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ከአኅዋ ወንዝ ተነሣን። የአምላካችንም እጅ በላያችን ነበረ፥ እርሱም ከጠላት እጅና በመንገድ ላይም ከሚሸምቅ አዳነን። ወደ ኢየሩሳሌም ደረስን፥ በዚያም ሦስት ቀን ቆየን። በአራተኛውም ቀን ብሩ፥ ወርቁና ዕቃዎቹም በአምላካችን ቤት በካህኑ በኡሪያ ልጅ በምሬሞት እጅ ተመዘነ፤ ከእርሱም ጋር የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር ነበረ። ከእነርሱም ጋር ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባድና የቢኑይ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ። በዚያን ሰዓት ሁሉም ነገር ተመዘነ፤ በሚዛንና በቍጥር ም ተመዘገበ። ከእስር የመጡት ከምርኮ የተመለሱት ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ ስለ እስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ ዘጠና ስድስት አውራ በጎች፥ ሰባ ሰባት ጠቦቶች፥ ለኃጢአት መሥዋዕት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየሎች አቀረቡ። ይህ ሁሉ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ። የንጉሡንም ትእዛዝ በወንዝ ማዶ ላሉት ለንጉሡ እንደራሴዎችና ገዢዎች ሰጡ፥ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት አገዙ።