ዕዝራ 2:40-58

ዕዝራ 2:40-58 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሌዋ​ው​ያኑ፤ ከሁ​ድያ ልጆች ወገን የኢ​ዮ​ስ​ስና የቀ​ዳ​ም​ሔል ልጆች ሰባ አራት። መዘ​ም​ራኑ የአ​ሳፍ ልጆች መቶ ሃያ ስም​ንት። የበ​ረ​ኞች ልጆች፥ የሰ​ሎም ልጆች፥ የአ​ጤር ልጆች፥ የጤ​ል​ሞን ልጆች፥ የዓ​ቁብ ልጆች፥ የሐ​ጢጣ ልጆች፥ የሰ​በ​ዋይ ልጆች ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ። ናታ​ኒም፤ የሲሓ ልጆች፥ የሐ​ሡፊ ልጆች፥ የጠ​ብ​ዖት ልጆች፤ የቃ​ዴስ ልጆች፥ የሲ​ሔል ልጆች፥ የፋ​ዶን ልጆች፤ የል​ባና ልጆች፥ የአ​ጋባ ልጆች፥ የዓ​ቁብ ልጆች፥ የአ​ጋብ ልጆች፥ የሰ​ላሚ ልጆች፥ የሐ​ናን ልጆች፤ የጋ​ዱል ልጆች፥ የጋ​ሐር ልጆች፥ የራ​እያ ልጆች፤ የረ​አ​ሶን ልጆች፥ የኒ​ቆዳ ልጆች፥ የጋ​ሴም ልጆች፤ የዓ​ዝ​ያት ልጆች፥ የፋ​ሒስ ልጆች፥ የባሲ ልጆች፤ የአ​ሲና ልጆች፥ የም​ዑ​ና​ው​ያን ልጆች፥ የና​ፌ​ሶን ልጆች፤ የበ​ቅ​ቡቅ ልጆች፥ የሐ​ቁፋ ልጆች፥ የሐ​ር​ሑር ልጆች፤ የበ​ስ​ሎት ልጆች፥ የማ​ሁድ ልጆች፥ የአ​ሪስ ልጆች፤ የበ​ር​ቆስ ልጆች፥ የሲ​ሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥ የን​ስያ ልጆች፥ የአ​ጡፋ ልጆች። የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች፤ የሳጢ ልጆች፥ የሰ​ፌ​ርታ ልጆች፥ የፋ​ዱ​ርሓ ልጆች፤ የኢ​ያ​ሔል ልጆች፥ የደ​ር​ቆን ልጆች፥ የጌ​ዴል ልጆች፤ የሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች፥ የአ​ጤል ልጆች፥ የፎ​ኬ​ርት ልጆች፥ የሐ​ፂ​ባ​ይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች። እነ​ዚህ ናታ​ኒም ሁሉና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።

ዕዝራ 2:40-58 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሌዋውያኑ፤ ከሆዳይዋ ወገን የኢያሱና የቀድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት። መዘምራኑ፤ የአሳፍ ልጆች፥ መቶ ሀያ ስምንት። የበረኞች ልጆች፤ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጢልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ። ናታኒም፤ የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ የጠብዖት ልጆች፥ የኬራስ ልጆች፥ የሲዓ ልጆች፥ የፋዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥ የአጋባ ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የአጋብ ልጆች፥ የሰምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ የራያ ልጆች፥ የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ የጋሴም ልጆች፥ የዖዛ ልጆች፥ የፋሴሐ ልጆች፥ የቤሳይ ልጆች፥ የአስና ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥ የንፋሰሲም ልጆች፥ የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቁፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥ የበስሎት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ የሐርሳ ልጆች፥ የበርቆስ ልጆች፥ የሲሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች። የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች፤ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥ የየዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈክራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች። እነዚህ ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።

ዕዝራ 2:40-58 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከምርኮ የተመለሱት የሌዋውያን ቤተሰቦች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ የሆዳውያ ዘሮች የሆኑት የኢያሱና የቃድሚኤል ቤተሰቦች 74 የአሳፍ ዘሮች የሆኑት የቤተ መቅደስ መዘምራን ብዛት 128 የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች የሆኑት የሻሉም፥ የአጤር፥ የጣልሞን፥ የዓቁብ፥ የሐጢጣና የሾባይ ዘሮች 139 ለቤተ መቅደስ ሥራ ከተመደቡትም መካከል ከምርኮ የተመለሱት ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ጺሐ፥ ሐሱፋ፥ ጣባዖት፥ ቄሮስ፥ ሲዓሃ፥ ፋዶን፥ ለባና፥ ሐጋባ፥ ዓቁብ፥ ሐጋብ፥ ሻምላይ፥ ሐናን፥ ጊዴል፥ ጋሐር፥ ረአያ፥ ረጺን፥ ነቆዳ፥ ጋዛም፥ ዑዛ፥ ፓሴሐ፥ ቤሳይ፥ አስና፥ መዑኒም፥ ነፊሲም፥ ባቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥ ባጽሉት፥ መሒዳ፥ ሐርሻ፥ ባርቆስ፥ ሲሣራ ቴማሕ፥ ነጺሐና ሐጢፋ። ከሰሎሞን አገልጋዮችም ወገን ከምርኮ የተመለሱት ጐሣዎች፥ ሶጣይ፥ ሀሶፌሬት፥ ፐሩዳ፥ ያዕላ፥ ዳርቆን፥ ጊዴል፥ ሸፋጥያ፥ ሐጢል፥ ፖኬሬት፥ ሐጸባይምና አሚ ተብለው የሚጠሩ ናቸው። ለቤተ መቅደስ ሥራ የተመደቡት ወገኖችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች ጠቅላላ ድምር 392 ነበር።

ዕዝራ 2:40-58 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሌዋውያኑ፥ ከሆዳቭያ ወገን የኢያሱና የቃድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት። መዘምራኑ፦ የአሳፍ ልጆች፥ አንድ መቶ ሀያ ስምንት። የበር ጠባቂዎች ልጆች፦ የሻሉም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጣልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሾባይ ልጆች፥ ሁሉ አንድ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ። የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ የፂሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ የጣባዖት ልጆች የቄሮስ ልጆች፥ የሲዓሃ ልጆች፥ የፓዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥ የሐጋባ ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጋብ ልጆች፥ የሻምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ የጊድል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ የርአያ ልጆች፥ የረፂን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ የጋዛም ልጆች፥ የዑዛ ልጆች፥ የፓሴሐ ልጆች፥ የቤሳይ ልጆች፥ የአስና ልጆች፥ የምዒኒም ልጆች፥ የንፊሲም ልጆች፥ የባቅቡቅ ልጆች፥ የሐቁፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥ የባፅሉት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ የሐርሻ ልጆች፥ የባርቆስ ልጆች፥ የሲሥራ ልጆች፥ የታማሕ ልጆች፥ የንፂሐ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች። የሰሎሞንም አገልጋዮች ልጆች፦ የሶጣይ ልጆች፥ የሃሶፌሬት ልጆች፥ የፕሩዳ ልጆች፥ የያዕላ ልጆች፥ የዳርቆን ልጆች፥ የጊዴል ልጆች፥ የሽፋጥያ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፎኬሬት ሃፂባይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች። እነዚህ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ሁሉና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።