የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ዕዝራ 2

2
ከምርኮ ወደ አገራቸው የተመለሱ የሰዎች ስም ዝርዝር
(ነህ. 7፥6-73)
1የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው። 2ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዕላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጉዋይ፥ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ።
የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ 3የፋሮስ ልጆች፥ ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት። 4የሰፋጥያስ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት። 5የኤራ ልጆች፥ ሰባት መቶ ሰባ አምስት። 6ከኢያሱና ከኢዮአብ ልጆች የሆኑ የፈሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አሥራ ሁለት። 7የኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 8የዛቱዕ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት። 9የዘካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ። 10የባኒ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት። 11የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ሦስት። 12የዓዝጋድ ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ ሀያ ሁለት። 13የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት። 14የበጉዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ አምሳ ስድስት። 15የዓዲን ልጆች፥ አራት መቶ አምሳ አራት። 16ከሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት። 17የቤሳይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሃያ ሦስት። 18የዮራ ልጆች፥ መቶ አሥራ ሁለት። 19የሐሱም ልጆች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት። 20-21የጋቤር ልጆች፥ ዘጠና አምስት። የቤተልሔም ልጆች፥ መቶ ሀያ ሦስት። 22የነጦፋ ሰዎች፥ አምሳ ስድስት። 23የዓናቶት ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት። 24የዓዝሞት ልጆች፥ አርባ ሁለት። 25የቂርያትይዓሪምና የከፊራ የብኤሮትም ልጆች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት። 26የራማና የጌባ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ። 27የማክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት። 28የቤቴልና የጋይ ሰዎች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት። 29የናባው ልጆች፥ አምሳ ሁለት። 30የመጌብስ ልጆች፥ መቶ አምሳ ስድስት። 31የሁለተኛውም ኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 32የካሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ። 33የሎድና የሐዲድ፥ የኦኖም ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አምስት። 34የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት። 35የሴናዓ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሳ።
36ካህናቱ ከኢያሱ ወገን የዮዳኤ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት። 37የኢሜር ልጆች፥ ሺህ አምሳ ሁለት። 38የፋስኮር ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት። 39የካሪም ልጆች፥ ሺህ አሥራ ሰባት።
40ሌዋውያኑ፤ ከሆዳይዋ ወገን የኢያሱና የቀድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት።
41መዘምራኑ፤ የአሳፍ ልጆች፥ መቶ ሀያ ስምንት።
42የበረኞች ልጆች፤ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጢልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ።
43ናታኒም፤ የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ 44የጠብዖት ልጆች፥ የኬራስ ልጆች፥ የሲዓ ልጆች፥ 45የፋዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥ የአጋባ ልጆች፥ 46የዓቁብ ልጆች፥ የአጋብ ልጆች፥ የሰምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ 47የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ የራያ ልጆች፥ 48የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ 49የጋሴም ልጆች፥ የዖዛ ልጆች፥ የፋሴሐ ልጆች፥ 50የቤሳይ ልጆች፥ የአስና ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥ የንፋሰሲም ልጆች፥ 51የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቁፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥ 52የበስሎት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ 53የሐርሳ ልጆች፥ የበርቆስ ልጆች፥ 54የሲሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች።
55የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች፤ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥ 56የየዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ 57የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈክራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች። 58እነዚህ ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።
59ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ነበሩ፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፤ 60የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት ነበሩ። 61ከካህናቱም ልጆች፤ የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች። 62እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አልተገኘም፤ ከክህነትም ተከለከሉ። 63ሐቴርሰታም “በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ድረስ ከቅዱሰ ቅዱሳን አትበሉም” አላቸው።
64-65ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነበሩ ከሎሌዎቻቸውና ከገረዶቻቸው ሌላ ጉባኤው ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ። ሁለት መቶም ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሩአቸው። 66ፈረሶቻቸውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት፥ በቅሎቻቸውም ሁለት መቶ አርባ አምስት፥ 67ግመሎቻቸውም አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ።
68በኢየሩሳሌምም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአባቶች ቤቶች አለቆች አያሌዎች ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው ይሠራ ዘንድ በፈቃዳቸው ሰጡ። 69ስድሳ አንድ ሺህም የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህም ምናን ብር፥ አንድ መቶም የካህናት ልብስ እንደ ችሎታቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ።
70ካህናቱና ሌዋውያኑ፥ ከሕዝቡም አያሌዎች፥ መዘምራኑና በረኞቹ፥ ናታኒምም በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ