መጽሐፈ ዕዝራ 2

2
ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ዝርዝር
1የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው። 2ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዔላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከቢልሻን፥ ከሚስፋር፥ ከቢግዋይ፥ ከሬሁምና፥ ከባዓና ጋር መጡ። የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው።
3የፓርዖሽ ልጆች፥ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ሁለት። 4የሸፋጥያ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት። 5የአራሕ ልጆች፥ ሰባት መቶ ሰባ አምስት። 6የፓሐት ሞዓብ ልጆች የኢያሱ ዮአብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዐሥራ ሁለት። 7የዔላም ልጆች፥ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 8የዛቱ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት። 9የዘካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ። 10የባኒ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት። 11የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ሦስት። 12የዓዝጋድ ልጆች፥ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ሀያ ሁለት። 13የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት። 14የቢግዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ አምሳ ስድስት። 15የዓዲን ልጆች፥ አራት መቶ አምሳ አራት። 16ከሕዝቅያ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት። 17የቤፃይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሃያ ሦስት። 18የዮራ ልጆች፥ መቶ ዐሥራ ሁለት። 19የሐሹም ልጆች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት። 20የጊባር ልጆች፥ ዘጠና አምስት። 21የቤተልሔም ልጆች፥ መቶ ሀያ ሦስት። 22የኔፆፋ ሰዎች፥ አምሳ ስድስት። 23የዓናቶት ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት። 24የዓዝማቬት ልጆች፥ አርባ ሁለት። 25የቂርያትዓሪም፥ ከፊራና ብኤሮት ልጆች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት። 26የራማና የጋባዕ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ። 27የሚክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት። 28የቤት-ኤልና የዐይ ሰዎች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት። 29የንቦ ልጆች፥ አምሳ ሁለት። 30የማግቢሽ ልጆች፥ አንድ መቶ አምሳ ስድስት። 31የሌላኛው ዔላም ልጆች፥ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 32የሐሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ። 33የሎድ የሐዲድና የኦኖ ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አምስት። 34የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት። 35የስናአ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሳ።
36ካህናቱ ከኢያሱ ቤት የሆነው ይዳዕያ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት። 37የኢሜር ልጆች፥ አንድ ሺህ አምሳ ሁለት። 38የፓሽሑር ልጆች፥ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት። 39የሐሪም ልጆች፥ አንድ ሺህ ዐሥራ ሰባት።
40ሌዋውያኑ፥ ከሆዳቭያ ወገን የኢያሱና የቃድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት።
41መዘምራኑ፦ የአሳፍ ልጆች፥ አንድ መቶ ሀያ ስምንት።
42የበር ጠባቂዎች ልጆች፦ የሻሉም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጣልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሾባይ ልጆች፥ ሁሉ አንድ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ።
43የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ የፂሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ የጣባዖት ልጆች 44የቄሮስ ልጆች፥ የሲዓሃ ልጆች፥ የፓዶን ልጆች፥ 45የልባና ልጆች፥ የሐጋባ ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ 46የሐጋብ ልጆች፥ የሻምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ 47የጊድል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ የርአያ ልጆች፥ 48የረፂን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ የጋዛም ልጆች፥ 49የዑዛ ልጆች፥ የፓሴሐ ልጆች፥ የቤሳይ ልጆች፥ 50የአስና ልጆች፥ የምዒኒም ልጆች፥ የንፊሲም ልጆች፥ 51የባቅቡቅ ልጆች፥ የሐቁፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥ 52የባፅሉት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ የሐርሻ ልጆች፥ 53የባርቆስ ልጆች፥ የሲሥራ ልጆች፥ የታማሕ ልጆች፥ 54የንፂሐ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች።
55የሰሎሞንም አገልጋዮች ልጆች፦ የሶጣይ ልጆች፥ የሃሶፌሬት ልጆች፥ የፕሩዳ ልጆች፥ 56የያዕላ ልጆች፥ የዳርቆን ልጆች፥ የጊዴል ልጆች፥ 57የሽፋጥያ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፎኬሬት ሃፂባይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች። 58እነዚህ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ሁሉና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።
59ከቴልሜላሕ፥ ቴልሐርሻ፥ ክሩብ፥ ዓዳን፥ ኢሜር የወጡ እነዚህ ነበሩ፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስታወቅ አልቻሉም፤ 60የድላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የንቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት ነበሩ። 61ከካህናቱም ልጆች፦ የሖባያ ልጆች፥ የሃቆፅ ልጆች፥ የባርዚላይ ልጆች ከገለዓዳዊው ባርዚላይ ሚስት ያገባ፥ በስማቸውም የተጠራ ነው። 62እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፥ ነገር ግን አልተገኙም፤ እንደ ርኩሳን ከክህነት ተከለከሉ። 63#ዘኍ. 27፥21።አስተዳዳሪውም፦ በኡሪምና በቱሚም የሚጠይቅ ካህን እስኪነሣ ድረስ ከቅዱሰ ቅዱሳን አትበሉም አላቸው። 64ከምርኮ የተመለሱ ሰዎች አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ። 65በተጨማሪም ወንዶች አገልጋይዮቻቸውና ሴቶች አገልጋዮቻቸው እነዚህ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ነበሩ ሌላ ሁለት መቶ ወንዶች መዘምራንና ሴቶች መዘምራን ነበሩአቸው። 66ፈረሶቻቸው ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት፥ በቅሎዎቻቸው ሁለት መቶ አርባ አምስት፥ 67ግመሎቻቸው አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ።
68ከአባቶች ቤቶች አለቆች አንዳንዶች፥ በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ጌታ ቤት በመጡ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው እንዲሠራ በፈቃዳቸው መባ ሰጡ። 69ስድሳ አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህ ምናን ብር፥ አንድ መቶ የካህናት ልብስ እንደየአቅማቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ።
70 # 1ዜ.መ. 9፥2፤ ነህ. 11፥3። ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንዶች፥ መዘምራኑ፥ በር ጠባቂዎቹና፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ፥ በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ