ሕዝቅኤል 23:1-39

ሕዝቅኤል 23:1-39 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ከአንድ እናት የተወለዱ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩ፤ ገና በወጣትነታቸው ዘማውያት በመሆን በግብጽ ሳሉ አመነዘሩ፤ በዚያችም ምድር አጐጠጐጤአቸው ተዳበሰ፤ የድንግልናቸውም ጕያ በእጅ ተሻሸ። የታላቂቱ ስም ኦሖላ፣ የእኅቷም ኦሖሊባ ነበር፤ ሁለቱም የእኔ ሆኑ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ወለዱ። ስማቸውም፣ ኦሖላ ሰማርያ ናት፤ ኦሖሊባም ኢየሩሳሌም። “ኦሖላ የእኔ ሆና ሳለ በእኔ ላይ አመነዘረች፤ ጦረኞች ከሆኑት ጎረቤቶቿ ከአሦራውያን ውሽሞቿ ጋራ ሴሰነች፤ እነርሱም ሐምራዊ የለበሱ፣ ገዦችና አዛዦች፣ ሁሉም መልከ ቀና ጐበዛዝትና ፈጣን ፈረሰኞች ነበሩ። እርሷ በዝሙት ራሷን ምርጥ ለሆኑት አሦራውያን ሁሉ አሳልፋ ሰጠች፤ ዐብረዋት ባመነዘሩት ሰዎች ጣዖት ሁሉ ረከሰች። በግብጽ የጀመረችውን አመንዝራነቷን አልተወችም፤ በዚያ ወንዶች በወጣትነቷ ከርሷ ጋራ ተኙ፤ የድንግልናዋን ጡት አሻሹ፤ ፍትወታቸውን አፈሰሱባት። “ስለዚህ ዐብራቸው ላመነዘረች ለአሦራውያን ውሽሞቿ አሳልፌ ሰጠኋት። እነርሱም ዕርቃን አስቀሯት፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቿን ነጠቋት፤ እርሷንም በሰይፍ ገደሏት፤ በሴቶችም ዘንድ መተረቻ ሆና ቀረች፤ ፍርድም ተፈጸመባት። “እኅቷ ኦሖሊባ ይህን አይታ ነበር፤ ሆኖም በፍትወቷና በዘማዊነቷ ከእኅቷ የባሰች ብልሹ ሆነች። ደግሞም ገዦችና አዛዦች፣ ጌጠኛ ልብስ የለበሱ ጦረኞች፣ ፈጣን ፈረሰኞችና፣ ሁሉም መልከ ቀና ከሆኑት አሦራውያን ጐበዛዝት ጋራ አመነዘረች። ይህችም እንደ ረከሰች አየሁ፤ ሁለቱም በአንድ መንገድ ሄዱ። “በአመንዝራነቷ እየባሰች ሄደች፤ በደማቅ ቀይ ቀለም በግድግዳ ላይ የተቀረጹ የከለዳውያንን ወንዶች ምስል አየች፤ እነርሱም ወገባቸውን በቀበቶ የታጠቁና በራሳቸው ላይ ተንጠልጣይ ያለው ጥምጥም የጠመጠሙ ነበሩ፤ ሁሉም የከለዳውያን ተወላጆችና የባቢሎን ሠረገላ አዛዦች ይመስሉ ነበር። ባየቻቸውም ጊዜ በፍትወት ተቃጠለች፤ ወደ ከላውዴዎን መልእክተኞች ላከችባቸው። ባቢሎናውያንም መጥተው ወደ ፍቅር መኝታዋ ገቡ፤ በፍትወታቸውም አረከሷት፤ እርሷም በእነርሱ ከረከሰች በኋላ ጠልታቸው ከእነርሱ ዘወር አለች። ግልሙትናዋን በአደባባይ በፈጸመችና ዕርቃን በገለጠች ጊዜ ከእኅቷ ዘወር እንዳልሁ፣ ጠልቻት ከርሷም ዘወር አልሁ። እርሷ ግን በግብጽ ያመነዘረችበት የወጣትነት ዘመኗ ትዝ እያላት የባሰ ዘማዊት ሆነች። በዚያም አባለዘራቸው እንደ አህያ፣ የዘር ፍሰታቸውም እንደ ድንጕላ ፈረስ ዘር ፍሰት ከሆነ ውሽሞቿ ጋራ አመነዘረች፤ በግብጽ ምድር ጕያሽን የታሸሽበትንና የወጣትነት ጡቶችሽን የተዳበስሽበትን የኰረዳነትሽን ብልግና ተመኘሽ። “ስለዚህ፣ ኦሖሊባ ሆይ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጠልተሻቸው ከእነርሱ ዘወር ያልሽውን ውሽሞችሽን በአንቺ ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱንም ከየአቅጣጫው አመጣብሻለሁ፤ እነርሱም ባቢሎናውያንና ከለዳውያን ሁሉ፣ የፋቁድ፣ የሱሔና የቆዓ ሰዎች፣ ከእነርሱም ጋራ አሦራውያን ሁሉ ናቸው። እነዚህም መልከ ቀና ጐበዛዝት ሲሆኑ፣ ሁላቸውም በፈረስ ላይ የተቀመጡ ገዦችና አዛዦች፣ የሠረገላ አዛዦችና ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ነበሩ። እነርሱም የጦር መሣሪያ፣ ሠረገላና ጋሪ በመያዝ ብዙ ሕዝብ ሆነው ይመጡብሻል፤ ትላልቅና መለስተኛ ጋሻ በማንገብና የራስ ቍር በመድፋት በየአቅጣጫው ይሰለፉብሻል፤ እኔም ለፍርድ በእጃቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ በሕጋቸውም መሠረት ይቀጡሻል። የቅናት ቍጣዬን በአንቺ ላይ አመጣለሁ፤ እነርሱም በአንቺ ላይ በቍጣ ይወጣሉ፤ አፍንጫሽንና ጆሮሽን ይቈርጣሉ፤ ከአንቺ ወገን የተረፉትም በሰይፍ ይወድቃሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ይወስዱብሻል፤ የተረፉትንም እሳት ይበላቸዋል። ልብስሽን ይገፉሻል፤ ምርጥ ጌጣጌጥሽንም ይወስዱብሻል። በግብጽ የጀመርሽውን ብልግናና ሴሰኛነት ከአንቺ አስወግዳለሁ፤ አንቺም ዐይንሽን ወደ እነዚህ አታነሺም፤ ከእንግዲህ ግብጽን አታስቢም። “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ እነሆ ተጸይፈሻቸው ከእነርሱ ዘወር ላልሽው ለጠላሻቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ። እነርሱም በጥላቻ ይቀርቡሻል፤ የለፋሽበትንም ሁሉ ይቀሙሻል፤ ከማሕፀን እንደ ወጣሽ ዕርቃንሽን ያስቀሩሻል፤ የሴሰኝነትሽ ኀፍረት ይገለጣል። ብልግናሽና ገደብ የለሽ ርኩሰትሽ፣ ይህን አምጥተውብሻል፤ ከአሕዛብ ጋራ በማመንዘር በጣዖቶቻቸው ረክሰሻልና። በእኅትሽ መንገድ ስለ ሄድሽ የእርሷን ጽዋ በእጅሽ አስጨብጥሻለሁ። “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰፊና ጥልቅ የሆነውን ጽዋ፣ የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ ብዙም ስለሚይዝ ስድብና ነቀፌታ ትጠግቢአለሽ። በእኅትሽ በሰማርያ ጽዋ፣ በመፍረስና በጥፋት ጽዋ፣ በስካርና በሐዘን ትሞዪአለሽ። ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽም፤ ከዚያም ጽዋውን ትሰባብሪዋለሽ፤ ጡትሽንም ትቈራርጪአለሽ፤ እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ረስተሽኛል፤ ወደ ኋላም ገሸሽ አድርገሽኛልና የብልግናሽንና የሴሰኝነትሽን ውጤት ትሸከሚአለሽ።” እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? እንግዲያውስ ጸያፍ ተግባራቸውን ንገራቸው። አመንዝረዋል፤ እጃቸውም በደም ተበክሏልና። ከጣዖቶቻቸው ጋራ አመነዘሩ፤ የወለዱልኝን ልጆቻቸውን እንኳ ለእነርሱ መብል ይሆኑ ዘንድ በእሳት ሠውተውላቸዋል። ደግሞም ይህን አደረጉብኝ፤ በዚያ ቀን ቤተ መቅደሴን አረከሱ፤ ሰንበታቴንም አቃለሉ። ልጆቻቸውን ለጣዖቶቻቸው በሠዉባት ዕለት ወደ መቅደሴ ገብተው አረከሷት፤ እንግዲህ በቤቴ ውስጥ ያደረጉት እንዲህ ያለውን ነው።

ሕዝቅኤል 23:1-39 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፥ የአ​ን​ዲት እናት ልጆች የሆኑ ሁለት ሴቶች ነበሩ። በግ​ብፅ ሀገር አመ​ነ​ዘሩ፤ በኮ​ረ​ዳ​ነ​ታ​ቸው ሳሉ አመ​ነ​ዘሩ፤ በዚ​ያም ጡቶ​ቻ​ቸው ወደቁ፤ በዚ​ያም ድን​ግ​ል​ና​ቸ​ውን አጡ። ስማ​ቸ​ውም የታ​ላ​ቂቱ ሐላ የታ​ናሽ እኅ​ቷም ሐሊባ ነበረ፤ እኔም አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም ወለዱ። ስማ​ቸ​ውም ሐላ ሰማ​ርያ ናት፤ ሐሊባ ደግሞ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ናት። “ሐላም አመ​ነ​ዘ​ረ​ች​ብኝ፤ ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንም የሚ​ቀ​ር​ቡ​አ​ትን አሦ​ራ​ው​ያ​ንን በፍ​ቅር ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው። እነ​ር​ሱም ሰማ​ያዊ ሐር የለ​በሱ መሳ​ፍ​ን​ትና መኳ​ን​ንት፥ መልከ መል​ካ​ሞች ጐበ​ዛ​ዝት፥ በፈ​ረስ ላይ የሚ​ቀ​መጡ የተ​መ​ረጡ ፈረ​ሰ​ኞች ነበሩ። ዝሙ​ቷ​ንም ከተ​መ​ረጡ ከአ​ሦር ሰዎች ሁሉ ጋር አደ​ረ​ገች፤ በፍ​ቅር በተ​ከ​ተ​ለ​ቻ​ቸ​ውም ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ረከ​ሰች። በግ​ብ​ፅም የነ​በ​ረ​ውን ዝሙ​ቷን አል​ተ​ወ​ችም፤ በዚ​ያም በኮ​ረ​ዳ​ነቷ ጊዜ ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኝ​ተው ነበር፤ የድ​ን​ግ​ል​ና​ዋ​ንም ጡቶች ዳብ​ሰው ነበር፤ ዝን​የ​ታ​ቸ​ው​ንም አፍ​ስ​ሰ​ው​ባት ነበር። ስለ​ዚህ በፍ​ቅር በተ​ከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው በወ​ዳ​ጆ​ችዋ በአ​ሦ​ራ​ው​ያን እጆች አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋት። እነ​ር​ሱም ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋን ገለጡ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ዋ​ንም ማር​ከው ወሰዱ፤ እር​ስ​ዋ​ንም በሰ​ይፍ ገደሉ፤ በእ​ር​ስ​ዋና በሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ላይ በቀ​ልን ስላ​ደ​ረ​ጉ​ባ​ቸው በሴ​ቶች መካ​ከል መተ​ረቻ ሆነች። “እኅ​ቷም ሐሊባ ይህን አየች፤ ሆኖም ከእ​ር​ስዋ ይልቅ በፍ​ቅር በመ​ከ​ተ​ልዋ ረከ​ሰች፤ ዝሙ​ቷ​ንም ከእ​ኅቷ ዝሙት ይልቅ አበ​ዛች። የሚ​ቀ​ር​ቡ​አ​ትን መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና መኳ​ን​ን​ቱን ጌጠኛ ልብስ የለ​በ​ሱ​ትን፥ በፈ​ረ​ሶች ላይ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ትን ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሁሉ​ንም መልከ መል​ካ​ሞ​ችን ጐበ​ዛ​ዝት አሦ​ራ​ው​ያ​ንን በፍ​ቅር ተከ​ተ​ለ​ቻ​ቸው። እንደ ረከ​ሱም አየሁ፤ ሁለ​ቱም አንድ መን​ገድ ሄደ​ዋል። ዳግ​መ​ኛም ዝሙ​ቷን አበ​ዛች፤ በግ​ንብ ላይ የተ​ሣሉ የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሰዎች ሥዕ​ል​ንም አየሁ። በጥ​ቍር ቀለም የተ​ሣሉ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን መልክ አየሁ፤ በወ​ገ​ባ​ቸው ዝናር የታ​ጠቁ ናቸው፤ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ጥልፍ ሰበን የጠ​መ​ጠሙ ናቸው፤ ፊታ​ቸ​ውም ሦስት ወገን ነው፤ ሁሉም በት​ው​ልድ ሀገ​ራ​ቸው የሚ​ኖሩ የባ​ቢ​ሎን ሰዎ​ችን ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን ይመ​ስ​ላሉ። ዐይ​ን​ዋ​ንም ወደ እነ​ርሱ አቅ​ንታ አየ​ቻ​ቸው፤ ወደ ከላ​ው​ዴ​ዎ​ንም ምድር ወደ እነ​ርሱ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከች። የባ​ቢ​ሎ​ንም ልጆች ወደ እር​ስዋ መጥ​ተው በመ​ኝ​ታዋ ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኙ፤ በዝ​ሙ​ታ​ቸ​ውም አረ​ከ​ሱ​አት፤ እር​ስ​ዋም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ረከ​ሰች፤ ነፍ​ስ​ዋም ከእ​ነ​ርሱ ተለ​የች። ዝሙ​ቷ​ንም ገለ​ጠች፤ ኀፍ​ረተ ሥጋ​ዋ​ንም ገለ​ጠች፤ ነፍ​ሴም ከእ​ኅቷ እንደ ተለ​የች እን​ዲሁ ነፍሴ ከእ​ር​ስዋ ተለ​የች። ነገር ግን በግ​ብፅ ምድር ያመ​ነ​ዘ​ረ​ሽ​በ​ትን የወ​ጣ​ት​ነ​ት​ሽን ዘመን አስ​በሽ ዝሙ​ት​ሽን አበ​ዛሽ። አካ​ላ​ቸ​ውም እንደ አህ​ዮች አካል፤ ዘራ​ቸ​ውም እንደ ፈረ​ሶች ዘር የሆ​ነ​ውን እነ​ዚ​ያን የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ልጆች በፍ​ቅር ተከ​ተ​ል​ሻ​ቸው። ጡትሽ በአ​ጐ​ጠ​ጐጠ ጊዜ በማ​ደ​ሪ​ያሽ በግ​ብፅ ሀገር የሠ​ራ​ሽ​ውን የወ​ጣ​ት​ነ​ት​ሽን ኀጢ​አት አሰ​ብሽ።” ስለ​ዚህ ሐሊባ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ነፍ​ስሽ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ለ​የች ወዳ​ጆ​ች​ሽን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም በአ​ንቺ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ። እነ​ር​ሱም የባ​ቢ​ሎን ልጆች፥ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሁሉ፥ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አሦ​ራ​ው​ያን ሁሉ፥ መልከ መል​ካ​ሞች ጐበ​ዛ​ዝት፥ መሳ​ፍ​ን​ትና መኳ​ን​ንት ሁሉ፥ መሳ​ፍ​ን​ትና አማ​ካ​ሪ​ዎች ሁሉ፥ በሦ​ስት ወገን በፈ​ረስ ላይ የተ​ቀ​መጡ ናቸው። ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ሰዎች ሁሉ በመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ርና በሠ​ረ​ገላ፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ጉባኤ ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ ጋሻና አላ​ባሽ ጋሻ፥ ራስ ቍርም ይዘው በዙ​ሪ​ያሽ ጥበቃ ያደ​ር​ጋሉ፤ ፍር​ድ​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ፍር​ዳ​ቸ​ውም ይፈ​ር​ዱ​ብ​ሻል። ቅን​አ​ቴ​ንም በአ​ንቺ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በመ​ዓ​ትም ያደ​ር​ጉ​ብ​ሻል፤ አፍ​ን​ጫ​ሽ​ንና ጆሮ​ሽ​ንም ከአ​ንቺ ይቈ​ር​ጣሉ፤ ከአ​ን​ቺም የቀረ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃል፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ሽ​ንም ማር​ከው ይወ​ስ​ዳሉ፤ ከአ​ን​ቺም የቀ​ሩ​ትን እሳት ትበ​ላ​ቸ​ዋ​ለች። ልብ​ስ​ሽ​ንም ይገ​ፍ​ፉ​ሻል፤ የክ​ብ​ር​ሽ​ንም ጌጥ ይወ​ስ​ዳሉ። ሴሰ​ኝ​ነ​ት​ሽ​ንም፥ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሽ​ውን ዝሙ​ት​ሽ​ንም ከአ​ንቺ አስ​ቀ​ራ​ለሁ፤ ዐይ​ን​ሽ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ወደ እነ​ርሱ አታ​ነ​ሺም፤ ግብ​ፅ​ንም ከዚያ ወዲያ አታ​ስ​ቢም። ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በጠ​ላ​ሻ​ቸው እጅ፥ ነፍ​ስ​ሽም በተ​ለ​የ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም በጥል ያደ​ር​ጉ​ብ​ሻል፤ የደ​ከ​ም​ሽ​በ​ት​ንም ሁሉ ይወ​ስ​ዳሉ፤ ዕራ​ቁ​ት​ሽ​ንና ዕር​ቃ​ን​ሽን አድ​ር​ገ​ውም ይተ​ዉ​ሻል፤ የግ​ል​ሙ​ት​ና​ሽ​ንም ነውር፥ ሴሰ​ኝ​ነ​ት​ሽ​ንና ግል​ሙ​ት​ና​ሽ​ንም ሁሉ ይገ​ል​ጣሉ። ከአ​ሕ​ዝብ ጋር ስላ​መ​ነ​ዘ​ርሽ፤ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም ስለ ረከ​ስሽ ይህን ያደ​ር​ጉ​ብ​ሻል። በእ​ኅ​ትሽ መን​ገድ ሄደ​ሻል፤ ስለ​ዚህ ጽዋ​ዋን በእ​ጅሽ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የጠ​ለ​ቀ​ው​ንና የሰ​ፋ​ውን፥ ብዙም የሚ​ይ​ዘ​ውን የእ​ኅ​ት​ሽን ጽዋ ትጠ​ጪ​አ​ለሽ፤ ብዙ መጠ​ጥን በሚ​ጠጡ ሰዎ​ችም ዘንድ መሳ​ቂ​ያና መሳ​ለ​ቂያ ትሆ​ኛ​ለሽ። በእ​ኅ​ትሽ በሰ​ማ​ርያ ጽዋ፥ በድ​ን​ጋ​ጤና በጥ​ፋት ጽዋ፥ በስ​ካ​ርና በው​ር​ደት ትሞ​ሊ​ያ​ለሽ። ትጠ​ጪ​ዋ​ለሽ፥ ትጨ​ል​ጪ​ው​ማ​ለሽ፤ በዓ​ላ​ት​ሽ​ንና መባ​ቻ​ዎ​ች​ሽን እሽ​ራ​ለሁ፤ እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ዘን​ግ​ተ​ሽ​ኛ​ልና፥ ወደ ኋላ​ሽም ጥለ​ሽ​ኛ​ልና አንቺ ደግሞ ሴሰ​ኝ​ነ​ት​ሽ​ንና ኀጢ​አ​ት​ሽን ተሸ​ከሚ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ሐላ​ንና ሐሊ​ባን ተፋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም አስ​ታ​ው​ቃ​ቸው፤ አመ​ን​ዝ​ረ​ዋ​ልና፥ ደምም በእ​ጃ​ቸው አለና፥ ዝሙ​ታ​ቸ​ው​ንም ወድ​ደ​ዋ​ልና፥ ለእ​ኔም የወ​ለ​ዱ​አ​ቸ​ውን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን መብል እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ቸው በእ​ሳት አሳ​ል​ፈ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና። ይህን ደግሞ አድ​ር​ገ​ው​ብ​ኛል፤ በዚያ ቀን መቅ​ደ​ሴን አር​ክ​ሰ​ዋል፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ሽረ​ዋል። ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው በሠዉ ጊዜ ፥ በዚ​ያው ቀን ያረ​ክ​ሱት ዘንድ ወደ መቅ​ደሴ ገቡ፤ እነ​ሆም በቤቴ ውስጥ እን​ደ​ዚህ አደ​ረጉ።

ሕዝቅኤል 23:1-39 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ከአንድ እናት የተወለዱ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩ፤ ገና በወጣትነታቸው ዘማውያት በመሆን በግብጽ ሳሉ አመነዘሩ፤ በዚያችም ምድር አጐጠጐጤአቸው ተዳበሰ፤ የድንግልናቸውም ጕያ በእጅ ተሻሸ። የታላቂቱ ስም ኦሖላ፣ የእኅቷም ኦሖሊባ ነበር፤ ሁለቱም የእኔ ሆኑ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ወለዱ። ስማቸውም፣ ኦሖላ ሰማርያ ናት፤ ኦሖሊባም ኢየሩሳሌም። “ኦሖላ የእኔ ሆና ሳለ በእኔ ላይ አመነዘረች፤ ጦረኞች ከሆኑት ጎረቤቶቿ ከአሦራውያን ውሽሞቿ ጋራ ሴሰነች፤ እነርሱም ሐምራዊ የለበሱ፣ ገዦችና አዛዦች፣ ሁሉም መልከ ቀና ጐበዛዝትና ፈጣን ፈረሰኞች ነበሩ። እርሷ በዝሙት ራሷን ምርጥ ለሆኑት አሦራውያን ሁሉ አሳልፋ ሰጠች፤ ዐብረዋት ባመነዘሩት ሰዎች ጣዖት ሁሉ ረከሰች። በግብጽ የጀመረችውን አመንዝራነቷን አልተወችም፤ በዚያ ወንዶች በወጣትነቷ ከርሷ ጋራ ተኙ፤ የድንግልናዋን ጡት አሻሹ፤ ፍትወታቸውን አፈሰሱባት። “ስለዚህ ዐብራቸው ላመነዘረች ለአሦራውያን ውሽሞቿ አሳልፌ ሰጠኋት። እነርሱም ዕርቃን አስቀሯት፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቿን ነጠቋት፤ እርሷንም በሰይፍ ገደሏት፤ በሴቶችም ዘንድ መተረቻ ሆና ቀረች፤ ፍርድም ተፈጸመባት። “እኅቷ ኦሖሊባ ይህን አይታ ነበር፤ ሆኖም በፍትወቷና በዘማዊነቷ ከእኅቷ የባሰች ብልሹ ሆነች። ደግሞም ገዦችና አዛዦች፣ ጌጠኛ ልብስ የለበሱ ጦረኞች፣ ፈጣን ፈረሰኞችና፣ ሁሉም መልከ ቀና ከሆኑት አሦራውያን ጐበዛዝት ጋራ አመነዘረች። ይህችም እንደ ረከሰች አየሁ፤ ሁለቱም በአንድ መንገድ ሄዱ። “በአመንዝራነቷ እየባሰች ሄደች፤ በደማቅ ቀይ ቀለም በግድግዳ ላይ የተቀረጹ የከለዳውያንን ወንዶች ምስል አየች፤ እነርሱም ወገባቸውን በቀበቶ የታጠቁና በራሳቸው ላይ ተንጠልጣይ ያለው ጥምጥም የጠመጠሙ ነበሩ፤ ሁሉም የከለዳውያን ተወላጆችና የባቢሎን ሠረገላ አዛዦች ይመስሉ ነበር። ባየቻቸውም ጊዜ በፍትወት ተቃጠለች፤ ወደ ከላውዴዎን መልእክተኞች ላከችባቸው። ባቢሎናውያንም መጥተው ወደ ፍቅር መኝታዋ ገቡ፤ በፍትወታቸውም አረከሷት፤ እርሷም በእነርሱ ከረከሰች በኋላ ጠልታቸው ከእነርሱ ዘወር አለች። ግልሙትናዋን በአደባባይ በፈጸመችና ዕርቃን በገለጠች ጊዜ ከእኅቷ ዘወር እንዳልሁ፣ ጠልቻት ከርሷም ዘወር አልሁ። እርሷ ግን በግብጽ ያመነዘረችበት የወጣትነት ዘመኗ ትዝ እያላት የባሰ ዘማዊት ሆነች። በዚያም አባለዘራቸው እንደ አህያ፣ የዘር ፍሰታቸውም እንደ ድንጕላ ፈረስ ዘር ፍሰት ከሆነ ውሽሞቿ ጋራ አመነዘረች፤ በግብጽ ምድር ጕያሽን የታሸሽበትንና የወጣትነት ጡቶችሽን የተዳበስሽበትን የኰረዳነትሽን ብልግና ተመኘሽ። “ስለዚህ፣ ኦሖሊባ ሆይ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጠልተሻቸው ከእነርሱ ዘወር ያልሽውን ውሽሞችሽን በአንቺ ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱንም ከየአቅጣጫው አመጣብሻለሁ፤ እነርሱም ባቢሎናውያንና ከለዳውያን ሁሉ፣ የፋቁድ፣ የሱሔና የቆዓ ሰዎች፣ ከእነርሱም ጋራ አሦራውያን ሁሉ ናቸው። እነዚህም መልከ ቀና ጐበዛዝት ሲሆኑ፣ ሁላቸውም በፈረስ ላይ የተቀመጡ ገዦችና አዛዦች፣ የሠረገላ አዛዦችና ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ነበሩ። እነርሱም የጦር መሣሪያ፣ ሠረገላና ጋሪ በመያዝ ብዙ ሕዝብ ሆነው ይመጡብሻል፤ ትላልቅና መለስተኛ ጋሻ በማንገብና የራስ ቍር በመድፋት በየአቅጣጫው ይሰለፉብሻል፤ እኔም ለፍርድ በእጃቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ በሕጋቸውም መሠረት ይቀጡሻል። የቅናት ቍጣዬን በአንቺ ላይ አመጣለሁ፤ እነርሱም በአንቺ ላይ በቍጣ ይወጣሉ፤ አፍንጫሽንና ጆሮሽን ይቈርጣሉ፤ ከአንቺ ወገን የተረፉትም በሰይፍ ይወድቃሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ይወስዱብሻል፤ የተረፉትንም እሳት ይበላቸዋል። ልብስሽን ይገፉሻል፤ ምርጥ ጌጣጌጥሽንም ይወስዱብሻል። በግብጽ የጀመርሽውን ብልግናና ሴሰኛነት ከአንቺ አስወግዳለሁ፤ አንቺም ዐይንሽን ወደ እነዚህ አታነሺም፤ ከእንግዲህ ግብጽን አታስቢም። “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ እነሆ ተጸይፈሻቸው ከእነርሱ ዘወር ላልሽው ለጠላሻቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ። እነርሱም በጥላቻ ይቀርቡሻል፤ የለፋሽበትንም ሁሉ ይቀሙሻል፤ ከማሕፀን እንደ ወጣሽ ዕርቃንሽን ያስቀሩሻል፤ የሴሰኝነትሽ ኀፍረት ይገለጣል። ብልግናሽና ገደብ የለሽ ርኩሰትሽ፣ ይህን አምጥተውብሻል፤ ከአሕዛብ ጋራ በማመንዘር በጣዖቶቻቸው ረክሰሻልና። በእኅትሽ መንገድ ስለ ሄድሽ የእርሷን ጽዋ በእጅሽ አስጨብጥሻለሁ። “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰፊና ጥልቅ የሆነውን ጽዋ፣ የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ ብዙም ስለሚይዝ ስድብና ነቀፌታ ትጠግቢአለሽ። በእኅትሽ በሰማርያ ጽዋ፣ በመፍረስና በጥፋት ጽዋ፣ በስካርና በሐዘን ትሞዪአለሽ። ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽም፤ ከዚያም ጽዋውን ትሰባብሪዋለሽ፤ ጡትሽንም ትቈራርጪአለሽ፤ እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ረስተሽኛል፤ ወደ ኋላም ገሸሽ አድርገሽኛልና የብልግናሽንና የሴሰኝነትሽን ውጤት ትሸከሚአለሽ።” እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? እንግዲያውስ ጸያፍ ተግባራቸውን ንገራቸው። አመንዝረዋል፤ እጃቸውም በደም ተበክሏልና። ከጣዖቶቻቸው ጋራ አመነዘሩ፤ የወለዱልኝን ልጆቻቸውን እንኳ ለእነርሱ መብል ይሆኑ ዘንድ በእሳት ሠውተውላቸዋል። ደግሞም ይህን አደረጉብኝ፤ በዚያ ቀን ቤተ መቅደሴን አረከሱ፤ ሰንበታቴንም አቃለሉ። ልጆቻቸውን ለጣዖቶቻቸው በሠዉባት ዕለት ወደ መቅደሴ ገብተው አረከሷት፤ እንግዲህ በቤቴ ውስጥ ያደረጉት እንዲህ ያለውን ነው።

ሕዝቅኤል 23:1-39 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ የአንዲት እናት ልጆች የሆኑ ሁለት ሴቶች ነበሩ። በግብጽም አመነዘሩ፥ በኰረዳነታቸው አመነዘሩ፥ በዚያ ጡቶቻቸው ምዋሸሹ በዚያም የድንግልናቸውን ጡቶች ዳበሱ። ስማቸውም የታላቂቱ ኦሖላ የእኅትዋም ኦሖሊባ ነበረ፥ ለእኔም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ስማቸውም ኦሖላ ሰማርያ ናት፥ ኦሖሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት። ኦሖላም ገለሞተችብኝ፥ ውሽሞችዋም ጎረቤቶችዋን አሦራውያንን በፍቅር ተከተለቻቸው። እነርሱም ሰማያዊ ሐር የለበሱ አለቆችና ሹማምቶች፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ በፈረስ ላይ የሚቀመጡ ፈረሰኞች ነበሩ። ግልሙትናዋንም ከተመረጡ ከአሦር ሰዎች ሁሉ ጋር አደረገች፥ በፍቅር በተከተለቻቸውም ጣዖቶቻቸው ሁሉ ረከሰች። በግብጽም የነበረውን ግልሙትናዋን አልተወችም፥ በዚያ በኰረዳነትዋ ጊዜ ከእርስዋ ጋር ተኝተው ነበር፥ የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር፥ ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር። ስለዚህ በፍቅር በተከተለቻቸው በውሽሞችዋ በአሦራውያን እጅ አሳልፌ ሰጠኋት። እነርሱም ኅፍረተ ሥጋዋን ገለጡ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ማርከው ወሰዱ፥ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉ፥ ፍርድንም ስላደረጉባት በሴቶች መካከል መተረቻ ሆነች። እኅትዋም ኦሖሊባ ይህን አየች፥ ሆኖም ከእርስዋ ይልቅ በፍቅር በመከተልዋ ረከሰች፥ ግልሙትናዋም ከእኅትዋ ግልሙትና ይልቅ በዛ። አለቆችንና ሹማምቶችን ጎረቤቶችዋን ጌጠኛ ልብስ የለበሱትን በፈረሶች ላይ የሚቀመጡትን ፈረሰኞች፥ ሁሉም መልከ መልካሞችን ጐበዛዝት አሦራውያንን በፍቅር ተከተለቻቸው። የረከሰችም እንደ ሆነች አየሁ፥ ሁለቱም አንድ መንገድ ሄደዋል። ግልሙትናዋንም አበዛች፥ በቀይ ቀለምም የተሳለችውን የከለዳውያንን ስዕል፥ በናስ ላይ የተሳሉትን ሰዎች አየች። በወገባቸው ዝናር የታጠቁ ራሳቸውንም በቀለማዊ መጠምጠሚያ የጠመጠሙ ነበሩ፥ ሁሉም ከተወለዱባት አገር የሆኑትን የከለዳውያንን ልጆች መስለው መሳፍንትን ይመስሉ ነበር። ባየቻቸውም ጊዜ በፍቅር ተከተለቻቸው፥ ወደ ከላውዴዎን ምድር ወደ እነርሱ መልእክተኞችን ላከች። የባቢሎንም ሰዎች ወደ እርስዋ ፍቅር ወዳለበት መኝታ መጡ በግልሙትናቸውም አረከሱአት፥ እርስዋም ከእነርሱ ጋር ረከሰች ነፍስዋም ከእነርሱ ተለየች። ግልሙትናዋንም ገለጠች ኅፍረተ ሥጋዋንም አሳየች፥ ነፍሴም ከእኅትዋ እንደ ተለየች እንዲሁ ነፍሴ ከእርስዋ ተለየች። ነገር ግን በግብጽ ምድር የገለሞተችበትን የኰረዳነትዋን ዘመን አስባ ግልሙትናዋን አበዛች። ሥጋቸውም እንደ አህዮች ሥጋ ዘራቸውም እንደ ፈረሶች ዘር የሆነውን እነዚያን ምልምሎች በፍቅር ተከተለቻቸው። ስለ ኰረዳነትሽ ምክንያት ግብጻውያን ጡቶችሽን በዳበሱ ጊዜ የኰረዳነትሽን ሴሰኝነት አሰብሽ። ስለዚህ፥ ኦሖሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስሽ ከእነርሱ የተለየች ውሽሞችሽን አስነሣብሻለሁ፥ በዙሪያሽም በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ። እነርሱም የባቢሎን ሰዎች ከለዳውያንም ሁሉ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእነርሱም ጋር አሦራውያን ሁሉ፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ አለቆችና ሹማምቶች ሁሉ፥ መሳፍንቶችና አማካሪዎች ሁሉ፥ በፈረስ ላይ የተቀመጡ ናቸው። በመሣሪያና በሰረገላ በመንኰራኵርም በአሕዛብም ጉባኤ ይመጡብሻል፥ ጋሻና አላባሽ ጋሻ ራስ ቍርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል፥ ፍርድንም እሰጣቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም ይፈርዱብሻል። ቅንዓቴንም በአንቺ ላይ አደርጋለሁ በመዓትም ያደርጉብሻል፥ አፍንጫሽንና ጆሮሽንም ከአንቺ ይቈርጣሉ፥ ከአንቺም የቀረ በሰይፍ ይወድቃል፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽንም ማርከው ይወስዳሉ፥ ከአንቺም የቀረውን እሳት ትበላቸዋለች። ልብስሽንም ይገፍፉሻል የክብርሽንም ጌጥ ይወስዳሉ። ሴሰኝነትሽንም፥ ከግብጽ ምድር ያወጣሽውን ግልሙትናሽንም ከአንቺ አስቀራለሁ፥ ዓይንሽንም ወደ እነርሱ አታነሺም ግብጽንም ከዚያ ወዲያ አታስቢም። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ በጠላሻቸው እጅ፥ ነፍስሽ በተለየቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጥሻለሁ፥ እነርሱም በጥል ያደርጉብሻል፥ የደከምሽበትንም ሁሉ ይወስዳሉ፥ ዕራቁትሽንና ዕርቃንሽን አድርገውም ይተዉሻል፥ የግልሙትናሽም ነውር፥ ሴሰኝነትሽና ግልሙትናሽም ሁሉ ይገለጣል። ከአሕዛብ ጋር ስላመነዘርሽ በጣዖቶቻቸውም ስለ ረከስሽ ይህን ያደረጉብሻል። በእኅትሽ መንገድ ሄደሻል፥ ስለዚህ ጽዋዋን በእጅሽ እሰጥሻለሁ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የጠለቀውንና የሰፋውን ብዙም የሚይዘውን የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፥ መሳቂያና መሳለቂያም ትሆኛለሽ። በእኅትሽ በሰማሪያ ጽዋ፥ በድንጋጤና በጥፋት ጽዋ፥ በስካርና በውርደት ትሞልያለሽ። ትጠጪዋለሽ ትጨልጪውማለሽ ገሉንም ታኝኪዋለሽ ጡትሽንም ትሸነትሪዋለሽ፥ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር። ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዘንግተሽኛልና፥ ወደ ኋላሽም ጥለሽኛልና አንቺ ደግሞ ሴሰኝነትሽንና ግልሙትናሽን ተሸከሚ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? ኃጢአታቸውንም ታስታውቃቸዋለህን? አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና፥ ከጣዖቶቻቸውም ጋር አመንዝረዋልና፥ ለእኔም የወለዱአቸውን ልጆቻቸውን መብል እንዲሆኑላቸው በእሳት አሳልፈዋቸዋልና። ይህን ደግሞ አድርገውብኛል፥ በዚያ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል ሰንበታቴንም ሽረዋል። ልጆቻቸውንም ለጣዖቶቻቸው በሠዉ ጊዜ፥ በዚያው ቀን ያረክሱት ዘንድ ወደ መቅደሴ ገቡ፥ እነሆም፥ በቤቴ ውስጥ እንደዚህ አደረጉ።

ሕዝቅኤል 23:1-39 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ከአንድ እናት የሚወለዱ ሁለት እኅትማማች ነበሩ፤ እነርሱም በወጣትነታቸው ወራት በግብጽ ሲኖሩ ክብርናቸውን አጥተው በመዋረድ አመንዝሮች ሆኑ። ከእነርሱም ታላቂቱ ኦሆላ ትባል ነበር፤ እርስዋም ሰማርያ ነች፤ ታናሽቱ ደግሞ ኦሆሊባ ትባል ነበር እርስዋም ኢየሩሳሌም ነች፤ እኔ ሁለቱንም አግብቼ ልጆች ወለዱልኝ። ኦሆላ እኔ ካገባኋት በኋላ እንኳ አመንዝራነትዋን ቀጠለች፤ በአሦራውያን ወዳጆችዋም ፍቅር ተቃጠለች። እነርሱም ሐምራዊ የለበሱ ታላላቅ መሳፍንት፥ ከፍተኛ ማዕርግ ያላቸው መኰንኖች ነበሩ፤ ሁሉም ወጣትነት ያላቸውና መልከ ቀና የሆኑ ፈረሰኞች ነበሩ። እርስዋም ለአሦራውያን ባለ ሥልጣኖች ሁሉ መጠቀሚያ አመንዝራ ነበረች፤ ፍትወትዋም የአሦራውያንን ጣዖቶች በማምለክ ራስዋን እንድታረክስ አደረጋት። ክብርናዋን ባጣችበት በግብጽ የጀመረችውን አመንዝራነት ቀጥላለች፤ ከልጃገረድነትዋ ጊዜ ጀምሮ ወንዶች ሁሉ እርስዋን እንደ አመንዝራ በመቊጠር ከእርስዋ ጋር ያመነዝራሉ። ስለዚህ እጅግ ለምትፈልጋቸው ለአሦራውያን ወዳጆችዋ አሳልፌ ሰጠኋት፤ እነርሱም ልብስዋን ገፈው እርቃንዋን አስቀሩአት፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋን በምርኮ ያዙ፤ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉአት፤ ፍርድም በእርስዋ ላይ ተግባራዊ ሆነ፤ ሴቶች ሁሉ ስለ ገጠማት መጥፎ ዕድል አሉባልታ ማሰማት ጀመሩ። “እኅትዋ ኦሆሊባ ይህንንም ካየች በኋላ ባሰባት እንጂ አልታረመችም፤ እንዲያውም ከኦሆላ የበለጠ አመንዝራ ሆነች። እርስዋም በበኩልዋ ታላላቅ የአሦራውያን መሳፍንትንና የጦር መኰንኖችን፥ ደማቅ ልብስ የሚለብሱ ወታደሮችንና መልከቀና የሆኑ ወጣትነት ያላቸውን ፈረሰኞች በማፍቀር በፍትወት የተቃጠለች ሆነች። ይህችም ሁለተኛይቱ ረከሰች፤ ሁለቱም በአንድ ዐይነት መንገድ ተጓዙ። “አመንዝራነትዋም እየባሰ ሄደ፤ በወገቦቻቸው ዙሪያ የሚያማምሩ ቀለበቶችን ታጥቀው፥ በራሶቻቸውም ላይ ጌጠኛ ጥምጥም ጠምጥመው፥ በደማቅ ሐምራዊ ቀለም በግድግዳ ላይ የተቀረጹትን ከፍተኞች የሆኑት ባለሥልጣኖችን ምስሎች አይታ ተማረከች። ልክ እነርሱን ስታይ በፍትወት ተቃጥላ እነርሱ ወደሚኖሩባት ወደ ባቢሎን መልእክተኞችን ላከች፤ ባቢሎናውያንም ከእርስዋ ጋር ለማመንዘር መጡ፤ ብዙ ጊዜ ስላረከሱአት በመጨረሻ ሁሉንም በመጸየፍ ጠላቻቸው። እርቃንዋን ወደ አደባባይ በመውጣት አመንዝራነትዋ በሰው ሁሉ ዘንድ እንዲጋለጥ አደረገች፤ እኔም እኅትዋን የተጸየፍኩትን ያኽል እርስዋንም ተጸየፍኳት። እርስዋም በልጃገረድነትዋ ወራት በግብጽ አመንዝራ ሆና ሳለ ስታደርግ የነበረውን ሁሉ በመፈጸም አመንዝራነትዋን አበዛች። ብልቶቻቸው እንደ አህያ፥ ዘራቸውም እንደ አለሌ ፈረስ ሆኖ በፍትወት በሚቃጠሉ ወንዶች ተማረከች። ኦሆሊባ ሆይ! በልጃገረድነትሽ ወራት ወንዶች በጡቶችሽ እየተጫወቱ ክብረ ንጽሕናሽን ባጣሽ ጊዜ ትፈጽሚው የነበረውን ርኲሰት ደግመሽ መፈጸም ትፈልጊያለሽ። “አሁንም ኦሆሊባ ሆይ! እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምልሽ ይህ ነው፤ እነዚያን ወዳጆችሽን ተጸይፈሻቸዋል፤ ነገር ግን እነርሱ በአንቺ እንዲነሡ አደርጋለሁ፤ እንዲከቡሽም ወደዚህ አመጣቸዋለሁ። ባቢሎናውያንንና ከለዳውያንን ሁሉ አመጣለሁ፤ የፈቆድን፥ የሾዐንና የቆዐንን ወንዶች እንዲሁም አሦራውያንን ሁሉ አመጣለሁ፤ ወጣትነት ያላቸው፥ መልከ ቀና የሆኑ መሳፍንትና የጦር መኰንኖች፥ ታላላቅ ባለሥልጣኖችና ከፍተኛ ማዕርግ ያላቸው እነዚህ ሁሉ በፈረስ ተቀምጠው ይመጣሉ። እነርሱም በብዙ ሠረገላና ስንቅ በተጫኑ ጋሪዎች የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት መርተው በማምጣት በሁሉም አቅጣጫ አደጋ ይጥሉብሻል፤ በጋሻና በራስ ቊር እየተከላከሉ ይከቡሻል፤ እኔም ለእነርሱ ፍርድ አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነርሱም በራሳቸው ሕግ መሠረት ይቀጡሻል። እኔ በአንቺ ስለ ተቈጣሁ፤ እነርሱም በቊጣቸው በአንቺ ላይ የፈለጉትን እንዲያደርጉ እፈቅድላቸዋለሁ፤ አፍንጫሽንና ጆሮዎችሽን ይቈርጣሉ፤ ከአንችም የቀሩትን በሰይፍ ይገደላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ከአንቺ ነጥቀው ይወስዳሉ፤ ከአንቺም የቀሩትን በእሳት ያቃጥሉአቸዋል። ልብሶችሽን ሁሉ ይገፉሻል፤ ጌጣጌጦችሽንም ሁሉ ይወስዳሉ። የዝሙት ሥራሽንና ገና በግብጽ ሳለሽ ጀምሮ የምትፈጽሚያቸውን አሳፋሪ ድርጊቶች ሁሉ እንድትተይ አደርጋለሁ፤ ዳግመኛም ወደ ጣዖቶች አትመለከቺም፤ ስለ ግብጽም አታስቢም።” ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “በጥላቻ ለምትጸየፊያቸው ሕዝቦች አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ አንቺን ከመጥላታቸው የተነሣ የደከምሽበትን ሁሉ ይወስዱብሻል፤ እርቃንሽንም አስቀርተው እንደ አመንዝራ ሴት ኀፍረተ ሥጋሽ እንዲጋለጥ ያደርጋሉ፤ የተቃጠለ ፍትወትሽና ዘማዊነትሽ፥ ይህ ሁሉ እንዲደርስብሽ አድርጎአል፤ ለሕዝቦች ሁሉ የፍትወት መጠቀሚያ ዘማዊት ሆነሽ በጣዖቶቻቸው ራስሽን አረከስሽ። የእኅትሽን አካሄድ ስለ ተከተልሽ እርስዋ የጠጣችውን የቅጣት ጽዋ እንድትጠጪ አደርግሻለሁ።” ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ ከእኅትሽ ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ እርሱም ትልቅና ጥልቀት ያለው ነው፤ ሰው ሁሉ መቀለጃና ማፌዣ ያደርግሻል፤ ጽዋውም ብዙ የሚይዝ ነው። አንቺ በስካርና በሐዘን የተሞላሽ ትሆኚአለሽ፤ የእኅትሽ የሰማርያንም የጥፋትና የውድመት ጽዋ ትጠጪአለሽ። ምንም ሳታስቀሪ ጨልጠሽ ትጠጪዋለሽ፤ ጽዋውንም ሰባብረሽ በስባሪው በሐዘን ጡቶችሽን ትቈራርጪአለሽ። እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” አሁንም ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ስለ ረሳሽኝና ጀርባሽን ስላዞርሽብኝ፥ ስለ ሴሰኛነትሽና ስለ አመንዝራነትሽም መከራ ትቀበዪአለሽ።” እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! በኦሆላና በኦሆሊባ ላይ ፍርድ ለመስጠት ተዘጋጅተሃልን? ያደረጉትን አጸያፊ ነገር ግለጥላቸው፤ ሁለቱም አመንዝሮችና ነፍሰ ገዳዮች ናቸው፤ ያመነዘሩት ከጣዖቶች ጋር ሲሆን፥ የገደሉአቸውም ለእኔ የወለዱአቸውን ልጆች ነው፤ ወንዶች ልጆቼን ለጣዖቶቻቸው ሠውተዋል። እነርሱ የፈጸሙት በደል ይህ ብቻ አይደለም፤ ቤተ መቅደሴንም በዚያን ጊዜ አርክሰዋል፤ ሰንበቴንም ሽረዋል። ለጣዖቶች መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ ልጆቼን በገደሉበት ዕለት ወደ ቤተ መቅደሴ መጥተው አረከሱት፤ እነሆ በቤቴ ያደረጉት ይህ ነው።

ሕዝቅኤል 23:1-39 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ የአንድ እናት ልጆች የሆኑ ሁለት ሴቶች ነበሩ። በግብጽ አመነዘሩ፤ በወጣትነታቸው አመነዘሩ፤ በዚያ ጡቶቻቸው ተዳሰሱ፥ በዚያም የድንግልናቸው የጡቶች ጫፍ ተዳበሱ። ስማቸውም፦ የታላቂቱ ኦሆላ የእኅትዋም ኦሆሊባ ነበረ። የእኔም ሆኑ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ስማቸውም፦ ኦሆላ ሰማርያ ናት፥ ኦሆሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት። ኦሖላም የእኔ ሆና ሳለ አመነዘረች፥ ጦረኞች ከሆኑት አሦራውያን ውሽሞችዋ ጋር በፍትወት ተከተለቻቸው። እነርሱም ሰማያዊ የለበሱ ገዢዎችና ባለ ሥልጣኖች፥ ሁሉም መልከ መልካም ወጣቶች፥ ፈረስ የሚጋልቡ ፈረሰኞች ነበሩ። ዝሙቷንም ከተመረጡ የአሦር ሰዎች ሁሉ ጋር አደረገች፥ በፍትወት ከተከተለቻቸው ከጣዖቶቻቸው ሁሉ ጋር እራስዋን አረከሰች። ከግብጽ ጀምሮ የነበረውን አመንዝራነቷን አልተወችም፤ በወጣትነትዋ ጊዜ ወንዶች ከእርሷ ጋር ተኝተው ነበርና፥ የድንግልናዋንም የጡቶቿ ጫፎች ዳብሰው ነበርና፥ ፍትወታቸውንም አፍስሰውባት ነበርና። ስለዚህ በፍትወት በተከተለቻቸው በውሽሞችዋ እጅ፥ በአሦር ልጆች እጅ አሳልፌ ሰጠኋት። እነርሱም ዕራቁትነትዋን ገለጡ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ወሰዱ፤ እርሷንም በሰይፍ ገደሉ፤ በሴቶች መካከል መተረቻ ሆነች፥ ፍርድም ተፈጸመባት። እኅትዋ ኦሆሊባ ይህን አየች፥ ሆኖም በፍትወቷና በአመንዝራነቷ ከእርሷ ይልቅ ብልሹ ነበረች፥ ይህም ከእኅትዋ ይልቅ የበዛ ነበር። አሦራውያንን፥ ገዢዎችና ባለ ሥልጣኖች፥ ጌጠኛ ልብስ የለበሱ ጦረኞች፥ በፈረሶችን የሚጋልቡ ፈረሰኞች፥ ሁሉም መልከ መልካም ወጣቶችን በፍትወት ተከተለቻቸው። እራስዋን እንዳረከሰች አየሁ፤ ሁለቱም በአንድ መንገድ ሄዱ። አመንዝራነቷን ቀጠለችበት፤ በቀይ ቀለም የተሳለ የከለዳውያን ስዕል፥ በግድግዳ ላይ የተቀረጸ የወንዶች ምስል አየች። በወገባቸው ዝናር የታጠቁ፥ በራሳቸውም ላይ መጠምጠሚያ ያንጠለጠሉ፥ ሁሉም የተወለዱባት አገር የከለዳ የሆነች የባቢሎን ልጆች የሆኑትን ባለሥልጣኖችን ይመስሉ ነበር። በዓይኗም ባየቻቸው ጊዜ በፍትወት ተከተለቻቸው፥ ወደ ከላውዴዎን ምድር ወደ እነርሱ መልእክተኞችን ላከች። የባቢሎንም ልጆች ወደ እርሷ፥ ወደ ፍቅር አልጋ ገቡ፥ በዝሙታቸውም አረከሱአት፤ እርሷም በእነርሱ ረከሰች ነፍስዋም ከእነርሱ ተለየች። ዝሙቷን ገለጠች፥ ዕርቃንዋንም ገለጠች፥ ነፍሴ ከእኅትዋ እንደ ተለየች እንዲሁ ነፍሴ ከእርሷም ተለየች። ሆኖም በግብጽ ምድር ያመነዘረችበትን የወጣትነትዋን ዘመን አስባ ዝሙቷን አበዛች። ሥጋቸው እንደ አህዮች ሥጋ፥ ዘራቸውም እንደ ፈረሶች ዘር የሆነውን እነዚያን ምልምሎች በፍትወት ተከተለቻቸው። ስለ ወጣትነት ጡቶችሽን ግብጻውያን ጡቶችሽን የዳበሱበትን ጊዜ የወጣትነትሽን ሴሰኝነት አሰብሽ። ስለዚህ ኦሆሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስሽ ከእነርሱ የተለየቻቸው ወዳጆችሽን አስነሣብሻለሁ፥ እነርሱንም ከየአቅጣጫው በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ። እነርሱም የባቢሎን ልጆች፥ ከለዳውያን ሁሉ ፋቁድ፥ ሾዓ፥ ቆዓ፥ ከእነርሱም ጋር የአሦር ልጆች ሁሉ፥ ሁሉም መልከ መልካም ወጣቶች፥ ገዢዎች፥ ባለ ሥልጣናት፥ መኰንኖችና የተጠሩ፥ ሁሉም ፈረስ የሚጋልቡ ናቸው። መሣሪያ፥ ሠረገላና መንኰራኵር ይዘው፥ ብዙ ሕዝብ ሆነው በአንቺ ላይ ይመጣሉ፤ ጋሻና አላባሽ ጋሻ ራስ ቁርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል፥ ፍርድንም እሰጣቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም ይፈርዱብሻል። በቁጣ እንዲቀርቡሽ ቅናቴን በአንቺ ላይ አደርጋለሁ፥ አፍንጫሽንና ጆሮሽን ይቆርጣሉ፤ ቀሪሽም በሰይፍ ይወድቃል፤ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችሽን ይወስዳሉ፥ ከአንቺም የቀረው በእሳት ይበላል። ልብስሽን ይገፍፉሻል የሚያማምሩ ጌጣጌጦችሽን ይወስዳሉ። ሴሰኝነትሽንና ከግብጽ ምድር ያመጣሽውን ዝሙትሽንም ከአንቺ አስቀራለሁ፥ ዓይንሽን ወደ እነርሱ አታነሺም፥ ግብጽንም ዳግም አታስቢም። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ በጠላሻቸው እጅ፥ ነፍስሽም በተለየቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነርሱም በጥል ይቀርቡሻል፥ የድካምሽን ፍሬ ሁሉ ይወስዳሉ፥ ዕራቁትሽንና ዕርቃንሽን አድርገውም ይተዉሻል፥ የዝሙትሽ ዕራቁትነት፥ ሴሰኝነትሽና ግልሙትናሽ ይገለጣል። ከአገሮች ጋር ስላመነዘርሽ በጣዖቶቻቸውም ስለ ረከስሽ ይህን አደረጉብሽ። በእኅትሽ መንገድ ሄደሻል፤ ስለዚህ የእርሷን ጽዋ በእጅሽ እሰጥሻለሁ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጥልቅና ሰፊ የሆነውን የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ ብዙም ስለሚይዝ መሳቂያና መሳለቂያም ትሆኛለሽ። የድንጋጤና የጥፋት ጽዋ በሆነው በእኅትሽ በሰማሪያ ጽዋ፥ በስካርና በኀዘን ትሞዪአለሽ። ትጠጪዋለሽ፥ ትጨልጪዋለሽም፥ ገሉን ታኝኪዋለሽ፥ ጡትሽንም ትቆራርጪአለሽ፤ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለረሳሽኝ፥ ወደ ኋላሽም ስለጣልሽኝ፥ አንቺ ደግሞ ሴሰኝነትሽንና ግልሙትናሽን ተሸከሚ። ጌታ እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በኦሆላና በኦሆሊባ ትፈርዳለህን? ርኩሰታቸውን ንገራቸው። አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና፤ ከጣዖቶቻቸው ጋር አመንዝረዋል፤ ለእኔ የወለዷቸውን ልጆቻቸውን እንኳ መብል እንዲሆኑ አሳልፈው ሰጥተዋቸዋል። ደግሞም ይህን አደረጉብኝ፦ በዚያኑ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል፥ ሰንበቶቼንም ሽረዋል። ልጆቻቸውን ለጣዖቶቻቸው በሠዉ ጊዜ፥ በዚያው ቀን ሊያረክሱት ወደ መቅደሴ ገብተዋልና፤ እነሆም በቤቴ ውስጥ ይህን አደረጉ።