ዘፀአት 5:1-22

ዘፀአት 5:1-22 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከዚ​ህም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘በም​ድረ በዳ በዓል ያደ​ር​ግ​ልኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።’ ” ፈር​ዖ​ንም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እለ​ቅቅ ዘንድ ቃሉን የም​ሰ​ማው እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ው​ቅም፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ አል​ለ​ቅ​ቅም” አለ። እነ​ር​ሱም፥ “ቸነ​ፈር ወይም ሰይፍ እን​ዳ​ይ​ጥ​ል​ብን የሦ​ስት ቀን መን​ገድ በም​ድረ በዳ እን​ድ​ን​ሄድ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ድ​ን​ሠዋ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ ጠራን” አሉት። የግ​ብፅ ንጉ​ሥም፥ “እና​ንተ ሙሴና አሮን፥ ሕዝ​ቡን ለምን ሥራ​ቸ​ዉን ታስ​ተ​ዋ​ላ​ችሁ? ወደ ተግ​ባ​ራ​ችሁ ሂዱ” አላ​ቸው። ፈር​ዖ​ንም ለሕ​ዝቡ አለ፥ “እነሆ፥ ሕዝቡ በም​ድር በጣም በዝ​ተ​ዋል፤ እና​ን​ተም ከሥ​ራ​ቸው አሳ​ር​ፋ​ች​ኋ​ቸ​ዋል። ፈር​ዖ​ንም በዚያ ቀን የሕ​ዝ​ቡን አሠ​ሪ​ዎ​ችና ጸሓ​ፊ​ዎች እን​ዲህ ሲል አዘዘ፦ “እንደ ወት​ሮው ለጡብ ሥራ ደግሞ ገለባ ለሕ​ዝቡ አት​ስጡ፤ ነገር ግን እነ​ርሱ ሄደው ለራ​ሳ​ቸው ገለባ ይሰ​ብ​ስቡ። ቀድሞ ያደ​ር​ጉት የነ​በ​ረ​ውን የጡብ ቍጥር እን​ዲሁ በየ​ቀኑ በእ​ነ​ርሱ ላይ አድ​ር​ጉት፤ ምንም ከእ​ርሱ አታ​ጕ​ድሉ፤ ሥራ ሰል​ች​ተ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ፦ ‘ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እን​ድ​ን​ሠዋ እን​ሂድ’ እያሉ ይጮ​ሃሉ። በእ​ነ​ዚህ ሰዎች ላይ ሥራው ይክ​በ​ድ​ባ​ቸው፤ ይህን ብቻ ያስ​ባሉ፤ ከንቱ ቃልም አያ​ስ​ቡም።” የሕ​ዝ​ቡም አሠ​ሪ​ዎ​ችና ጸሓ​ፊ​ዎች ወጡ፤ ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ፈር​ዖን እን​ዲህ ይላል፦ እን​ግ​ዲህ ገለባ አይ​ሰ​ጣ​ች​ሁም፤ እና​ንተ ሂዱ፤ ከም​ታ​ገ​ኙ​በ​ትም ስፍራ ገለባ ሰብ​ስቡ፤ ከም​ት​ሠ​ሩት ጡብ ግን ምንም አይ​ጐ​ድ​ልም” አሉ​አ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ ገለባ እብቅ ሊሰ​በ​ስቡ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ተበ​ተኑ። አሠ​ሪ​ዎ​ቹም፥ “ገለባ ትቀ​በ​ሉ​በት እን​ደ​ነ​በረ ጊዜ የቀን ሥራ​ች​ሁን ጨርሱ” እያሉ ያስ​ቸ​ኩ​ሉ​አ​ቸው ነበር። የፈ​ር​ዖ​ንም ሹሞች፥ “ቀድሞ ታደ​ር​ጉት እንደ ነበ​ራ​ችሁ እንደ ትና​ን​ት​ና​ውና እንደ ትና​ን​ትና በስ​ቲ​ያው የተ​ቈ​ጠ​ረ​ውን ጡብ ዛሬስ ስለ​ምን አት​ጨ​ር​ሱም?” እያሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን አለ​ቆች ይገ​ርፉ ነበር። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆ​ችም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፥ “ለምን በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ? ገለባ አይ​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም፤ ጡቡ​ንም ሥሩ ይሉ​አ​ቸ​ዋል፤ እነ​ሆም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ይገ​ረ​ፋሉ፤ ይገ​ፋ​ሉም፤ ግፉም በአ​ንተ ሕዝብ ላይ ነው” ብለው ጮኹ። እርሱ ግን፥ “እና​ንተ አር​ፋ​ች​ኋል፤ ቦዝ​ና​ች​ኋል፤ ስለ​ዚ​ህም፦ ‘እን​ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ሠዋ’ ትላ​ላ​ችሁ። አሁ​ንም ሂዱ፤ ሥሩ፤ ገለ​ባም አይ​ሰ​ጡ​አ​ች​ሁም፤ የጡ​ቡን ቍጥር ግን ታመ​ጣ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አለ​ቆች ዕለት ዕለት ከም​ት​ሠ​ሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታ​ጕ​ድሉ ባሉ​አ​ቸው ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋ​ባ​ቸው አዩ። ከፈ​ር​ዖ​ንም ዘንድ ሲወጡ ሙሴ​ንና አሮ​ንን በፊ​ታ​ቸው ቆመው ተገ​ና​ኙ​አ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ሽታ​ች​ንን አግ​ም​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና፥ ይገ​ድ​ለ​ንም ዘንድ ሰይ​ፍን በእጁ ሰጥ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ከ​ታ​ችሁ፤ ይፍ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁም” አሉ​አ​ቸው። ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተመ​ለ​ሰና፥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ​ምን ይህን ሕዝብ አስ​ከ​ፋህ? ስለ ምንስ ላክ​ኸኝ?

ዘፀአት 5:1-22 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚህ በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ’ ይላል” አሉት። ፈርዖንም “እንድታዘዘውና እስራኤልን እንድለቅለት ለመሆኑ ይህ እግዚአብሔር ማነው? እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አልለቅም” አለ። እነርሱም፣ “የዕብራውያን አምላክ ለእኛ ተገልጦልናል፤ የሦስት ቀን መንገድ ወደ ምድረ በዳው ተጕዘን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንድንሠዋ ፍቀድልን፤ አለዚያ ግን በመቅሠፍት ወይም በሰይፍ ይመታናል” አሉት። የግብጽ ንጉሥም፣ “እናንተ ሙሴና አሮን፤ ለምንድን ነው ሕዝቡን ሥራ የምታስፈቱት? በሉ እናንተም ወደየሥራችሁ ተመለሱ!” ፈርዖንም፣ “እነሆ፤ አሁን የምድሪቱ ሕዝብ እጅግ ብዙ ነው፤ እናንተም እንዳይሠሩ እያደረጋችኋቸው ነው” አለ። በዚያ ዕለት ፈርዖን ለባሪያ ተቈጣጣሪዎቹና ለሕዝቡ አለቆች እንዲህ ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ “ለጡብ ሥራ የሚያስፈልጋቸውን ጭድ ካለበት ቦታ ሄደው ራሳቸው ያምጡ እንጂ ከእንግዲህ እናንተ እንዳታቀርቡላቸው። ሆኖም ቀድሞ በሚያቀርቡት ሸክላ ልክ ሠርተው እንዲያቀርቡ አድርጓቸው። የሥራ ድርሻቸውን አትቀንሱ። ሰነፎች ናቸው፤ ‘ሄደን ለአምላካችን መሥዋዕት እንሠዋ’ የሚሉትም ለዚህ ነው። ለሐሰት ወሬ ስፍራ ሳይሰጡ ተግተው እንዲሠሩ ሥራውን አክብዱባቸው።” ከዚያም የባሪያ ተቈጣጣሪዎቹና አለቆቹ ወጥተው ለሕዝቡ፣ “ፈርዖን የሚለው ይህ ነው፤ ‘ከእንግዲህ ጭድ አልሰጣችሁም፤ ሂዱና የራሳችሁን ጭድ ከየትም ፈልጋችሁ አምጡ፤ የሥራ ድርሻችሁ ግን ከቶ አይቀነስም’ ” አሉ። ስለዚህም ሕዝቡ በጭድ ፈንታ ገለባ ለመሰብሰብ በግብጽ ምድር ሁሉ ተሰማሩ። የባሪያ ተቈጣጣሪዎቹም “በየዕለቱ መሥራት የሚገባችሁ ሥራ ቀድሞ ጭድ ስናቀርብላችሁ ከምትሠሩት ሥራ ማነስ የለበትም” እያሉ ያጣድፏቸው ነበር። የሥራው የቅርብ ኀላፊዎች ተደርገው በፈርዖን የባሪያ ተቈጣጣሪዎች የተመደቡት እስራኤላውያንም፣ “የትናንቱንም ሆነ የዛሬውን ሸክላ ሥራ ድርሻችሁን እንደ ቀድሞው ለምን አላሟላችሁም?” እየተባሉ ይጠየቁና ይገረፉ ነበር። ከዚያም ሥራውን በቅርብ ሆነው የሚቈጣጠሩት እስራኤላውያን ኀላፊዎች ፈርዖን ፊት ቀርበው እንዲህ ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ፤ “እኛን ባሮችህን እንደዚህ የምታደርገን ለምንድን ነው? ለእኛ ለባሮችህ ጭድ ሳያቀርቡልን ሸክላ ሥሩ ይሉናል፤ ጥፋቱ የገዛ ሰዎችህ ሆኖ ሳለ እኛ ባሮችህ ግን እንገረፋለን።” ፈርዖንም እንዲህ አለ፤ “ልግመኞች! እናንተ ልግመኞች! እየደጋገማችሁ ‘እንሂድ ለእግዚአብሔር እንሠዋ’ የምትሉት ለዚህ ነው። በሉ አሁንም ወደ ሥራችሁ ተመለሱ፤ ምንም ጭድ አይሰጣችሁም፤ ያም ሆኖ ግን የተመደበላችሁን ሸክላ ማምረት አለባችሁ።” እስራኤላውያን ኀላፊዎችም፣ “በየቀኑ የምትሠሩት ሸክላ ቍጥሩ ቀድሞ ከሚሠራው ሸክላ ማነስ የለበትም” ተብሎ ሲነገራቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ተረዱት። ከፈርዖን ዘንድ እንደ ተመለሱ ሲጠብቋቸው የነበሩትን ሙሴንና አሮንን አግኝተው፣ “እግዚአብሔር ይይላችሁ፤ ይፍረድባችሁም፤ ፈርዖንና ሹማምቱ እንዲጠየፉን አደረጋችሁ፤ እንዲገድሉን በእጃቸው ሰይፍ ሰጣችኋቸው” አሏቸው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ፣ “አቤቱ ጌታ ሆይ፤ በዚህ ሕዝብ ላይ መከራ ያመጣኸው ለምንድን ነው? የላክኸኝ ለዚሁ ነው?

ዘፀአት 5:1-22 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል ያደርግልኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።”’ ፈርዖንም፦ “ቃሉን እሰማ ዘንድ እስራኤልንስ እለቅቅ ዘንድ እግዚአብሔር ማን ነው? እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም፤” አለ። እነርሱም፦ “የዕብራውያን አምላክ ተገናኘን፤ ቸነፈር ወይም ሰይፍ እንዳይጥልብን የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንድንሄድ፥ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ እንለምንሃለን፤” አሉት። የግብፅ ንጉሥም፦ “አንተ ሙሴ! አንተም አሮን! ሕዝቡን ለምን ሥራቸውን ታስተዋላችሁ? ወደ ተግባራችሁ ሂዱ!” አላቸው። ፈርዖንም፦ “እነሆ የምድሩ ሕዝብ አሁን በዝቶአል፤ እናንተም ሥራቸውን ታስፈቱአቸዋላችሁ” አለ። ፈርዖንም በዚያን ቀን የሕዝቡን አስገባሪዎች ሹማምቶቹንም እንዲህ ሲል አዘዘ፤ እንደ ወትሮው ለጡብ ሥራ ደግሞ ገለባ ለሕዝቡ አትስጡ፤ ነገር ግን እነርሱ ሄደው ገለባ ይሰብስቡ። ቀድሞ ያደርጉት የነበረውን የጡብ ቁጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ምንም ከእርሱ አታጉድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፥ ‘ለአምላካችን እንድንሰዋ እንሂድ’ እያሉ ይጮኻሉ። እርሱንም ያደርጉ ዘንድ በሰዎች ላይ ሥራው ይክበድባቸው፤ ከንቱ ቃልም አያስቡ።” የሕዝቡም አስገባሪዎች ሹማምቶቹም ወጡ፤ ሕዝቡንም፥ “ፈርዖን እንዲህ ይላል፦ ‘ገለባ አልሰጣችሁም። እናንተ ሂዱ፤ ከምታገኙበትም ስፍራ ገለባ ሰብስቡ፤ ከሥራችሁ ግን ምንም አይጎድልም፤”’ አሉአቸው። ሕዝቡም ስለ ገለባ እብቅ ሊሰበስቡ በግብፅ ምድር ሁሉ ተበተኑ። አስገባሪዎቹም፥ “ገለባ ትቀበሉበት እንደ ነበረ ጊዜ የቀን ሥራችሁን ጨርሱ፤” እያሉ አስቸኮሉአቸው። የፈርዖንም አስገባሪዎች፦ “ቀድሞ ታደርጉ እንደ ነበራችሁ ትናንትናና ዛሬ የተቆጠረውን ጡብ ስለ ምን አትጨርሱም?” እያሉ በእስራኤል ልጆች ላይ የተሾሙትን አለቆቹን ገረፉ። የእስራኤል ልጆች አለቆችም ወደ ፈርዖን መጡ፤ “ለምን በባሪያዎችህ እንዲህ ታደርጋለህ? ገለባ አይሰጡንም፤ የጡቡንም ሥራ እንድንሠራ ያዝዙናል፤ እነሆም ባሪያዎችህን ይገርፉናል፤ ግድፈቱ ግን በአንተ ሕዝብ ላይ ነው” ብለው ጮሁ። እርሱ ግን፦ “ሰልችታችኋል፤ ሰልችታችኋል፤ ስለዚህም፦ ‘እንሂድ ለእግዚአብሔርም እንሠዋ’ ትላላችሁ። አሁንም ሂዱ፤ ሥሩ፤ ገለባ አይሰጡአችሁም፤ የጡቡን ቁጥር ግን ታመጣላችሁ፤” አላቸው። የእስራኤልም ልጆች አለቆች፦ “ዕለት ዕለት ከምትሰሩት ከጡቡ ቁጥር ምንም አታጕድሉ!” ባሉአቸው ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋባቸው አዩ። ከፈርዖንም ዘንድ ሲወጡ ሙሴንና አሮንን በፊታቸው ቆመው ተገናኙአቸው። እነርሱም፦ “በፈርዖንና በባሪያዎቹ ፊት ሽታችንን አግምታችሁታልና፥ ይገድሉንም ዘንድ ሰይፍን በእጃቸው ሰጥታችኋቸዋልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ፤ ይፍረድባችሁም፤” አሉአቸው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተመለሰና፦ “ጌታ ሆይ! ስለ ምን ይህን ሕዝብ አስከፋህ? ስለ ምንስ ላክኸኝ?

ዘፀአት 5:1-22 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከዚያም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ግብጽ ንጉሥ ሄደው “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ‘በበረሓ ለእኔ በዓል ለማድረግ እንዲሄዱ ሕዝቤን ልቀቅ’ ይልሃል” አሉት። ንጉሡም “ለመሆኑ እግዚአብሔር ማን ነው? የእርሱንስ ትእዛዝ ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለምንድን ነው? እኔ እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም” አለ። ሙሴና አሮንም “የዕብራውያን አምላክ ለእኛ ተገልጦልናል፤ የሦስት ቀን መንገድ ወደ በረሓ ተጒዘን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ ፍቀድልን፤ እኛ ይህን ባናደርግ በበሽታ ወይም በጦርነት እንድናልቅ ያደርጋል” ሲሉ መለሱለት። ንጉሡም እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ሙሴና አሮን ለምን ሕዝቡን ሥራ ታስፈታላችሁ? በሉ ወደ ሥራችሁ ተመለሱ!” ከዚያም ንጉሡ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ አሁን እናንተ ከአገሬው ሕዝብ በዝታችኋል፤ እናንተ ሙሴና አሮን ደግሞ ሥራ ታስፈቱአቸዋላችሁ።” በዚያኑ ቀን ንጉሡ ፈርዖን ጨካኞች የሆኑትን ግብጻውያን አሠሪዎችንና የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆችን እንዲህ ብሎ አዘዘ፥ “ለጡብ ሥራ የሚሆን ገለባ ለሕዝቡ እንደ ወትሮው አትስጡ፤ እነርሱ ራሳቸው ገለባውን ፈልገው ያምጡ፤ ነገር ግን ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን ያኽል አንድ ጡብ እንኳ ሳይጐድል እንዲያስረክቡ አድርጉ፤ ‘ለአምላካችን መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ ልቀቀን!’ እያሉ የሚነዘንዙኝ ብዙ የሚሠሩት ነገር ስለሌለ ነው፤ ሐሰተኛ ወሬ የሚሰሙበት ጊዜ እንዳይኖራቸው፥ እነዚህ ሰዎች ከምንጊዜውም ይልቅ በሥራ እንዲጠመዱና በብርቱ እንዲሠሩ አድርጉአቸው።” ጨካኞች የሆኑት ግብጻውያን አሠሪዎችና የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆች ሄደው ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ አሉ፤ “ንጉሡ ከእንግዲህ ወዲህ ገለባ እንዳይሰጣችሁ አዞአል፤ ራሳችሁ ሄዳችሁ ከየትም ስፍራ ፈልጋችሁ ማምጣት ይኖርባችኋል፤ ነገር ግን የምትሠሩት ጡብ ቊጥር ማነስ የለበትም።” ስለዚህ ሕዝቡ ገለባ ፈልገው ለማግኘት በመላይቱ የግብጽ ምድር ተሰማሩ። ጨካኞች የሆኑትም አሠሪዎች ቀድሞ ገለባ እየሰጡአቸው ይሠሩት የነበረውን ያኽል ጡብ ቈጥረው እንዲያስረክቡ ያስገድዱአቸው ጀመር። እነዚህም ጨካኞች የሆኑት ግብጻውያን አሠሪዎች፥ የእስራኤላውያን ሠራተኞችን አለቆች “ቀድሞ ትሠሩት የነበረውን ያኽል ጡብ ሠርታችሁ የማታስረክቡት ስለምንድነው?” እያሉ ይገርፉአቸው ነበር። የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆችም ወደ ንጉሡ ቀርበው “ንጉሥ ሆይ፥ በእኛ በአገልጋዮችህ ላይ እንዴት ይህን ሁሉ ነገር አደረግህብን? ምንም ገለባ ሳይሰጠን ጡብ እንድንሠራ ታዘናል፤ ከዚህም ጋር እነሆ፥ እየተገረፍን ነው፤ ስሕተቱ ግን የገዛ ሕዝብህ ነው እንጂ የእኛ አይደለም” ሲሉ አቤቱታቸውን አቀረቡ። ንጉሡም መልሶ “እናንተ ሥራ የማትወዱ ሰነፎች ናችሁ፤ በፍጹም ሰነፎች ናችሁ፤ ‘ሄደን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንድናቀርብ ልቀቀን’ እያላችሁ የምትጠይቁበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ በሉ አሁንም ወደ ሥራችሁ ተመለሱ! ከቶ ገለባ አይሰጣችሁም፤ ነገር ግን ቀድሞ የምትሠሩትን ያኽል ጡብ እየሠራችሁ ማስረከብ ይኖርባችኋል!” አላቸው። የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆች ቀድሞ የሚሠሩትን ያኽል ጡብ በየቀኑ መሥራት እንዳለባቸው በተረዱ ጊዜ በመከራ ላይ መውደቃቸውን ተገነዘቡ። ከንጉሡም ፊት እንደ ወጡ፥ እነርሱን በመጠባበቅ ላይ የነበሩትን ሙሴንና አሮንን አገኙአቸው፤ ሙሴንና አሮንንም “በንጉሡ በፈርዖንና በመኳንንቱ ዘንድ እጅግ እንድንጠላ በማድረጋችሁና በሰይፍ ይገድሉንም ዘንድ ምክንያት በመሆናችሁ፥ እግዚአብሔር ይይላችሁ፤ እርሱም ይፍረድባችሁ፤” አሉአቸው። ሙሴም እንደገና ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ እንዲህ አለ፤ “አምላክ ሆይ! በዚህ ሕዝብ ላይ ይህን ያኽል መከራ የምታደርስበት ስለምንድነው? እንዲህ ከሆነ እኔንስ ወደዚህ ስለምን ላክኸኝ?

ዘፀአት 5:1-22 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው ፈርዖንን እንዲህ አሉት፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በምድረ በዳ በዓል እንዲያደርግልኝ ሕዝቤን ልቀቅ።’” ፈርዖንም፦ “ቃሉን እንድሰማ እስራኤልንስ እንድለቅ ጌታ ማን ነው? ጌታን አላውቅም፥ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም” አለ። እነርሱም፦ “የዕብራውያን አምላክ ተገናኘን፤ የሦስት ቀን መንገድ በምድረ በዳ እንድንሄድ፥ ለጌታ ለአምላካችን እንድንሠዋ እንለምንሃለን ካልሆነ ተላላፊ በሽታ ወይም ሰይፍ እንዳይጥልብን” አሉት። የግብጽ ንጉሥም፦ “ሙሴና አሮን፥ ለምን ሕዝቡን ሥራቸውን ታስተዋላችሁ? ወደ ተግባራችሁ ሂዱ” አላቸው። ፈርዖንም፦ “እነሆ የምድሩ ሕዝብ አሁን በዝቶአል፥ እናንተም ሥራቸውን ታስፈቱአቸዋላችሁ” አለ። ፈርዖንም በዚያን ቀን የሕዝቡን አስገባሪዎች ሹማምንቶቹንም እንዲህ ሲል አዘዘ፦ “እንደ ቀድሞው ለጡብ ሥራ የሚሆን ገለባ ለሕዝቡ አትስጡ፤ እነርሱ ራሳቸው ሄደው ገለባ ይሰብስቡ። ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን የጡብ ቍጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ከእርሱ አታጉድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፦ ‘ለአምላካችን እንድንሰዋ መሄድ እንፈልጋለን’ እያሉ ይጮኸሉ። ሥራውን እንዲሰሩት፥ የሃሰትን ቃላት እንዳያስቡ፥ በሰዎቹ ላይ ሥራው ይክበድባቸው።” የሕዝቡ አስገባሪዎችና ሹማምንቶቹም ወጡ፥ ሕዝቡንም አሉት፦ “ፈርዖን እንዲህ ይላል፦ ‘ገለባ አልሰጣችሁም። እናንተ ሂዱ፥ ከምታገኙበትም ስፍራ ገለባ ሰብስቡ፤ ከሥራችሁ ግን ምንም አይጉደል።’” ሕዝቡም ለገለባ የሚሆን እብቅ ሊሰበስቡ በግብጽ ምድር ሁሉ ተበተኑ። አስገባሪዎቹም፦ “ገለባ ትቀበሉበት እንደ ነበረ ጊዜ የቀን ሥራችሁን ጨርሱ” እያሉ አስቸኮሉአቸው። የፈርዖንም አስገባሪዎች፦ “የተወሰነላችሁን የጡብ ሥራ ትናንትናና ዛሬ ለምን እንደ ቀድሞው አልጨረሳችሁም?” እያሉ በእስራኤል ልጆች ላይ የተሾሙትን አለቆቹን ገረፉ። የእስራኤል ልጆች አለቆችም ወደ ፈርዖን ሄደው እንዲህ ብለው ጮሁ፦ “ለምን አገልጋዮችህን እንዲህ ታደርጋለህ? ለአገልጋዮችህ ገለባ አልተሰጠም፥ ጡብ ሥሩ ይሉናል፤ እነሆ አገልጋዮችህ ተገረፍን፤ ይህም ሕዝብህን ሐጢአተኛ ያደርጋል።” እርሱም አላቸው፦ “ሰልችታችኋል፥ ሰልችታችኋል፤ ስለዚህም፦ ‘እንሂድ ለጌታም እንሠዋ’ ትላላችሁ። ስለዚህም ሂዱ፥ ሥሩ፤ ገለባ አይሰጣችሁም፥ የጡቡን ቍጥር ግን ታመጣላችሁ።” የእስራኤልም ልጆች አለቆች፦ “ዕለት ዕለት ከምትሰሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታጉድሉ” በተባሉ ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋባቸው አዩ። ከፈርዖንም ዘንድ ሲወጡ ሙሴንና አሮንን ቆመው አገኙአቸው። እነርሱም፦ “ጌታ እናንተ ላይ ይፍረድባችሁ፥ ሽታችንን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት አግምታችሁታልና፥ እንዲገድሉንም ሰይፍን በእጃቸው አስቀምጣችኋዋልና” አሉአቸው። ሙሴም ወደ ጌታ ተመለሰና፦ “ጌታ ሆይ፥ ለምን ይህን ሕዝብ አስከፋህ? ለምንስ ላክኸኝ?