የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፀአት 4:1-9

ዘፀአት 4:1-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሙሴም መለሰ፥ “እነሆ፥ ባያ​ም​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ባይ​ሰሙ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ህም’ ቢሉኝ ምን እላ​ቸ​ዋ​ለሁ?” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይህ በእ​ጅህ ያለው ምን​ድን ነው?” አለው። እር​ሱም፥ “በትር ነው” አለ። “ወደ መሬት ጣለው” አለው፤ እር​ሱም በመ​ሬት ጣለው፤ እባ​ብም ሆነ፤ ሙሴም ከእ​ርሱ ሸሸ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እጅ​ህን ዘር​ግ​ተህ ጅራ​ቱን ያዝ” አለው፤ ሙሴም እጁን ዘር​ግቶ፥ ጅራ​ቱን ይዞ፥ አነ​ሣው በእ​ጁም በትር ሆነ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እንደ ታየህ ያም​ኑ​ሃል” አለው። ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እጅ​ህን ወደ ብብ​ትህ አግባ አለው።” እጁ​ንም ወደ ብብቱ አገ​ባት፤ “እጅ​ህ​ንም ከብ​ብ​ትህ አውጣ” አለው፤ እጁ​ንም ከብ​ብቱ አወጣ፤ እጁም ለምጽ ሆነች። ዳግ​መ​ኛም፥ “እጅ​ህን ወደ ብብ​ትህ መልስ” አለው። እጁ​ንም ወደ ብብቱ መለ​ሳት፤ “እጅ​ህን ከብ​ብ​ትህ አውጣ” አለው፤ እጁ​ንም ከብ​ብቱ አወጣ፤ ተመ​ል​ሳም ገላ​ውን መሰ​ለች። ደግ​ሞም አለው፥ “እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ባያ​ም​ኑህ፥ በፊ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ምል​ክት ቃል​ህን ባይ​ሰሙ፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪቱ ምል​ክት ቃል​ህን ያም​ናሉ። እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እነ​ዚ​ህን ሁለት ምል​ክ​ቶች ባያ​ምኑ፥ ቃል​ህ​ንም ባይ​ሰሙ፥ ከወ​ንዙ ውኃን ውሰድ፤ በደ​ረ​ቁም መሬት ላይ አፍ​ስ​ሰው፤ ከወ​ን​ዙም የወ​ሰ​ድ​ኸው ውኃ በደ​ረቁ መሬት ላይ ደም ይሆ​ናል።”

ዘፀአት 4:1-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ሙሴም “ባያምኑኝስ፤ ቃሌን ባይቀበሉስ፤ ‘እግዚአብሔር (ያህዌ) አልተገለጠልህም’ ቢሉኝስ?” ብሎ መለሰ። እግዚአብሔርም (ያህዌ)፣ “በእጅህ የያዝሃት እርሷ ምንድን ናት?” ሲል ጠየቀው፤ እርሱም መልሶ፣ “በትር ናት” አለው። እግዚአብሔርም (ያህዌ)፣ “መሬት ላይ ጣላት” አለው። ሙሴ በትሩን መሬት ላይ ጣላት፤ እባብም ሆነች፤ ከአጠገቧም ሸሸ። እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “በል እጅህን ዘርጋና ጅራቷን ያዛት” አለው። ሙሴም እጁን ዘርግቶ ሲይዛት እባቧ ተለውጣ በእጁ ላይ እንደ ገና በትር ሆነች። እግዚአብሔርም (ያህዌ) “ይህ የሆነው የአባቶቻቸው አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር (ያህዌ) የተገለጠልህ መሆኑን እንዲያምኑ ነው” አለው። እግዚአብሔርም (ያህዌ) ደግሞ፣ “እጅህን ብብትህ ውስጥ አስገባ” አለው። ሙሴም እጁን ብብቱ ውስጥ አስገባ፤ ከብብቱ ውስጥ ባወጣት ጊዜ እጁ እንደ በረዶ ለምጽ ሆነች። “አሁንም ደግሞ እጅህን ወደ ብብትህ መልሰህ አስገባ” አለው። ሙሴም እጁን መልሶ ብብቱ ውስጥ አስገባ፤ እንደ ገና እጁን ከብብቱ ውስጥ ባወጣት ጊዜ፣ ተመልሳ እንደ ሌላው የሰውነቱ ክፍል ሆነች። እግዚአብሔርም (ያህዌ)፣ “እንግዲህ ባያምኑህ ወይም የመጀመሪያውን ታምራዊ ምልክት ባይቀበሉ እንኳ ሁለተኛውን ያምናሉ። እነዚህን ሁለት ምልክቶች ባያምኑ ወይም ቃልህን ባይቀበሉ ግን፣ ከአባይ ወንዝ ጥቂት ውሃ ቀድተህ በደረቅ ምድር ላይ አፍስሰው። ከወንዙም ቀድተህ ያፈሰስኸው ውሃ በምድር ላይ ደም ይሆናል።”

ዘፀአት 4:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሙሴም መለሰ፦ “እነሆ አያምኑኝም፤ ቃሌንም አይሰሙም፤ ‘እግዚአብሔር ከቶ አልተገለጠልህም’ ይሉኛል” አለ። እግዚአብሔርም፦ “ይህች በእጅህ ያለችው ምንድር ናት?” አለው። እርሱም፦ “በትር ናት፤” አለ። “ወደ መሬት ጣላት፤” አለው፤ እርሱም በመሬት ጣላት፤ እባብም ሆነች፤ ሙሴም ከእርሷ ሸሸ። እግዚአብሔርም ሙሴ፥ “የአባቶቻቸው አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ፥ እግዚአብሔር እንደ ተገለጠልህ እንዲያምኑ እጅህን ዘርግተህ ጅራትዋን ያዝ፤” አለው። እጁንም ዘርግቶ ያዛት በእጁም ውስጥ በትር ሆነች። እግዚአብሔርም ደግሞ፦ “እጅህን ወደ ብብትህ አግባ፤” አለው። እጁንም ወደ ብብቱ አገባት፤ ባወጣትም ጊዜ እነሆ፥ እጁ እንደ በረዶ ለምጽ ሆነች። እርሱም፦ እጅህን ወደ ብብትህ መልስ አለው። እጁንም ወደ ብብቱ መለሳት፥ ከብብቱም ባወጣት ጊዜ እነሆ ተመልሳ ገላውን መሰለች። ደግሞም አለው፦ “እንዲህም ይሆናል፤ ባያምኑህ የፊተኛይቱንም ምልክት ነገር ባይሰሙ፥ የሁለተኛይቱን ምልክት ነገር ያምናሉ። እንዲህም ይሆናል፤ እነዚህን ሁለት ምልክቶች ባያምኑ ቃልህንም ባይሰሙ፥ ከወንዙ ውኃን ውሰድ፤ በደረቁም መሬት ላይ አፍስሰው፤ ከወንዙም የወሰድኸው ውኃ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል።”

ዘፀአት 4:1-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ሙሴም እግዚአብሔርን “እስራኤላውያን ‘እግዚአብሔር አልተገለጠልህም’ ብለው ባያምኑኝና ቃሌን ባይሰሙ ምን እላቸዋለሁ?” አለው። እግዚአብሔርም “በእጅህ የያዝከው ምንድን ነው?” አለው። እርሱም “በትር ነው” አለ። እግዚአብሔርም “ወደ መሬት ጣለው” አለው፤ ሙሴም ወደ መሬት በጣለው ጊዜ በትሩ ተለውጦ እባብ ሆነ፤ ሙሴም ከእርሱ ሸሸ። እግዚአብሔር ግን ሙሴን “እጅህን ዘርጋና ጅራቱን ይዘህ አንሣው” አለው። ሙሴም እጁን ዘርግቶ ጅራቱን በመያዝ ባነሣው ጊዜ እንደገና በትር ሆነ። እግዚአብሔርም “የቀድሞ አባቶቻቸው የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተገለጥኩልህ ለእስራኤላውያን ማስረጃ ይሆን ዘንድ በዚህ ተጠቀም” አለው። እንደገናም እግዚአብሔር ሙሴን “እጅህን ወደ ብብትህ አስገባው” አለው፤ እርሱም እጁን ወደ ብብቱ አስገባ፤ እጁንም ከብብቱ ባወጣው ጊዜ እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። እግዚአብሔርም “እጅህን እንደገና ወደ ብብትህ አስገባ” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ብብቱ አስገባ፤ መልሶም ባወጣው ጊዜ ተመልሶ እነሆ፥ እንደ ሌላው ሰውነቱ ጤናማ ሆነ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ በመጀመሪያው ተአምር ባያምኑና እውነት ነው ብለው ባይቀበሉህ፥ ሁለተኛውን ተአምር ያምናሉ። እነዚህን ሁለት ተአምራት አይተው ባያምኑና ቃልህንም ባይሰሙ፥ ከዐባይ ወንዝ ጥቂት ውሃ ወስደህ በመሬት ላይ አፍስሰው፤ ከአባይ ወንዝ የወሰድከውም ውሃ በደረቀ ምድር ላይ ወደ ደም ይለወጣል።”

ዘፀአት 4:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሙሴም መለሰ፦ “እነሆ አያምኑኝም ቃሌንም አይሰሙም፦ ‘ጌታ ከቶ አልተገለጠልህም’ ይሉኛል” አለ። ጌታም፦ “ይህ በእጅህ ያለው ምንድነው?” አለው። እርሱም፦ “በትር ነው” አለ። እርሱም “ወደ መሬት ጣለው” አለው፤ እርሱም ወደ መሬት ጣለው፥ እባብም ሆነ፤ ሙሴም ከእርሱ ሸሸ። ጌታም ሙሴን፦ “እጅህን ዘርግተህ ጅራቱን ያዘው” አለው። እጁንም ዘርግቶ ያዘው በእጁም ውስጥ በትር ሆነ። “ይህም የአባቶቻቸው አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ አምላክ የያዕቆብም አምላክ፥ ጌታ እንደ ተገለጠልህ እንዲያምኑ ነው” አለው ጌታም ደግሞ፦ “እጅህን ወደ ብብትህ አስገባ” አለው። እጁንም ወደ ብብቱ አስገባ፤ ባወጣውም ጊዜ፥ እጁ እንደ በረዶ ነጭ እንደሆነ አየ። እርሱም፦ “እጅህን ወደ ብብትህ መልስ” አለው። እጁንም ወደ ብብቱ መለሰው፥ ከብብቱም ባወጣው ጊዜ ተመልሶ ገላውን እንደሚመስል አየ። “እንዲህ ይሆናል፤ ባያምኑህ የፊተኛይቱንም ምልክት ቃል ባይሰሙ፥ የኋላኛይቱን ምልክት ቃል ያምናሉ። እንዲህም ይሆናል፤ እነዚህን ሁለት ምልክቶች ባያምኑ ቃልህንም ባይሰሙ፥ ከዓባይ ወንዝ ጥቂት ውኃን ውሰድ፥ በደረቅ መሬት ላይ አፍስሰው፤ ከዓባይ ወንዝ የወሰድከውም ውኃ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል።”