የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 4

4
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ የሰ​ጠው ተአ​ም​ራዊ ኀይል
1ሙሴም መለሰ፥ “እነሆ፥ ባያ​ም​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ባይ​ሰሙ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ህም’ ቢሉኝ ምን እላ​ቸ​ዋ​ለሁ?” አለ። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይህ በእ​ጅህ ያለው ምን​ድን ነው?” አለው። እር​ሱም፥ “በትር ነው” አለ። 3“ወደ መሬት ጣለው” አለው፤ እር​ሱም በመ​ሬት ጣለው፤ እባ​ብም ሆነ፤ ሙሴም ከእ​ርሱ ሸሸ። 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እጅ​ህን ዘር​ግ​ተህ ጅራ​ቱን ያዝ” አለው፤ ሙሴም እጁን ዘር​ግቶ፥ ጅራ​ቱን ይዞ፥ አነ​ሣው በእ​ጁም በትር ሆነ። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እንደ ታየህ ያም​ኑ​ሃል” አለው። 6ዳግ​መ​ኛም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እጅ​ህን ወደ ብብ​ትህ አግባ አለው።” እጁ​ንም ወደ ብብቱ አገ​ባት፤ “እጅ​ህ​ንም ከብ​ብ​ትህ አውጣ” አለው፤ እጁ​ንም ከብ​ብቱ አወጣ፤ እጁም ለምጽ ሆነች። 7ዳግ​መ​ኛም፥ “እጅ​ህን ወደ ብብ​ትህ መልስ” አለው። እጁ​ንም ወደ ብብቱ መለ​ሳት፤ “እጅ​ህን ከብ​ብ​ትህ አውጣ” አለው፤ እጁ​ንም ከብ​ብቱ አወጣ፤ ተመ​ል​ሳም ገላ​ውን መሰ​ለች። 8ደግ​ሞም አለው፥ “እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ባያ​ም​ኑህ፥ በፊ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ምል​ክት ቃል​ህን ባይ​ሰሙ፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪቱ ምል​ክት ቃል​ህን ያም​ናሉ። 9እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እነ​ዚ​ህን ሁለት ምል​ክ​ቶች ባያ​ምኑ፥ ቃል​ህ​ንም ባይ​ሰሙ፥ ከወ​ንዙ ውኃን ውሰድ፤ በደ​ረ​ቁም መሬት ላይ አፍ​ስ​ሰው፤ ከወ​ን​ዙም የወ​ሰ​ድ​ኸው ውኃ በደ​ረቁ መሬት ላይ ደም ይሆ​ናል።”
10ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ጌታ ሆይ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ፤ ትና​ንት፥ ከት​ና​ንት ወዲያ ባሪ​ያ​ህን ከተ​ና​ገ​ር​ኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁም። እኔ አፌ ኰል​ታፋ፥ ምላ​ሴም ተብ​ታባ የሆነ ሰው ነኝ።” 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ለሰው አፍን የሰጠ ማን ነው? ዲዳስ፥ ደን​ቆ​ሮስ፥ የሚ​ያ​ይስ፥ ዕው​ርስ የሚ​ያ​ደ​ርግ ማን ነው? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? 12እን​ግ​ዲህ አሁን ሂድ፤ እኔም አን​ደ​በ​ት​ህን አረ​ታ​ለሁ፤ ትና​ገ​ረ​ውም ዘንድ ያለ​ህን አለ​ብ​ም​ሃ​ለሁ” አለው። 13ሙሴም፥ “ጌታ ሆይ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ፤ መና​ገር የሚ​ችል የም​ት​ል​ከው ሌላ ሰው ፈልግ” አለው። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ሌዋ​ዊው ወን​ድ​ምህ አሮን አለ አይ​ደ​ለ​ምን? እርሱ እን​ደ​ሚ​ና​ገ​ር​ልህ#ዕብ. “ደኅና እን​ዲ​ና​ገር” ይላል። አው​ቃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ እርሱ ሊገ​ና​ኝህ ይመ​ጣል፤ በአ​የ​ህም ጊዜ በልቡ ደስ ይለ​ዋል። 15አን​ተም ትና​ገ​ረ​ዋ​ለህ፤ ቃሌ​ንም በአፉ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ እኔ አን​ደ​በ​ት​ህ​ንና አን​ደ​በ​ቱን አረ​ታ​ለሁ፤ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ት​ንም አለ​ብ​ማ​ች​ኋ​ለሁ። 16እርሱ ስለ አንተ ከሕ​ዝቡ ጋር ይነ​ጋ​ገ​ራል፤ እርሱ አፍ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ አን​ተም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ትሆ​ን​ለ​ታ​ለህ። 17ይህ​ች​ንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ወደ እባ​ብ​ነት የተ​ለ​ወ​ጠ​ች​ውን” የሚል ይጨ​ም​ራል። ተአ​ም​ራት የም​ታ​ደ​ር​ግ​ባ​ትን በትር በእ​ጅህ ያዝ።”
የሙሴ ወደ ግብፅ መመ​ለስ
18ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶ​ርም ተመ​ለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕ​ይ​ወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመ​ልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወን​ድ​ሞች እሄ​ዳ​ለሁ” አለው። ዮቶ​ርም ሙሴን፥ “በደ​ኅና ሂድ” አለው። 19ከብዙ ዘመ​ንም በኋላ የግ​ብፅ ንጉሥ ሞተ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በም​ድ​ያም፥ “ነፍ​ስ​ህን የሚ​ሹ​አት ሰዎች ሁሉ ሞተ​ዋ​ልና ተመ​ል​ሰህ ወደ ግብፅ ሂድ” አለው። 20ሙሴም ሚስ​ቱ​ንና ልጆ​ቹን ወሰደ፤ በአ​ህ​ዮች ላይም አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው፤ ወደ ግብ​ፅም ሀገር ተመ​ለሰ፤ ሙሴም ያችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በትር በእጁ ይዞ ሄደ። 21እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመ​ል​ሰህ ስት​ሄድ በእ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴን ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት ታደ​ር​ገው ዘንድ ተመ​ል​ከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸ​ና​ዋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አይ​ለ​ቅ​ቅም። 22አንተ ግን ፈር​ዖ​ንን እን​ዲህ ትለ​ዋ​ለህ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እስ​ራ​ኤል የበ​ኵር ልጄ ነው፤ 23ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ አል​ሁህ፤ አን​ተም ልት​ለ​ቅ​ቃ​ቸው ባት​ፈ​ቅድ፤ እኔ የበ​ኵር ልጅ​ህን እን​ደ​ም​ገ​ድል ዕወቅ።”
24እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በመ​ን​ገድ ላይ በአ​ደ​ረ​በት ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ተገ​ና​ኘው፤ ሊገ​ድ​ለ​ውም ፈለገ። 25ሚስቱ ሲፓ​ራም ባል​ጩት ወሰ​ደች፤ የል​ጅ​ዋ​ንም ሸለ​ፈት ገረ​ዘች፤ “ይህ የልጄ የግ​ር​ዛቱ ደም ስለ እርሱ ፈንታ ይሁን” ብላ ከእ​ግሩ በታች ወደ​ቀች። 26ከእ​ር​ሱም ሄደ፤ የዚያ ጊዜ፥ “ይህ የልጄ የግ​ር​ዛቱ ደም ስለ እርሱ ፈንታ ይሁን” ብላ​ለ​ችና።
27እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን አለው፥ “ሄደህ በም​ድረ በዳ ሙሴን ተገ​ና​ኘው፤” ሄዶም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ተገ​ና​ኘው፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተሳ​ሳሙ። 28ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከ​ውን ቃል ሁሉ፥ የአ​ዘ​ዘ​ው​ንም ተአ​ም​ራት ሁሉ ለአ​ሮን ነገ​ረው። 29ሙሴና አሮ​ንም ሄዱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ሰበ​ሰቡ። 30አሮ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ የነ​ገ​ረ​ውን ቃል ሁሉ ተና​ገረ፤ ተአ​ም​ራ​ቱ​ንም በሕ​ዝቡ ፊት አደ​ረገ። 31ሕዝ​ቡም አመኑ፤ ደስም አላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ጐብ​ኝ​ቶ​አ​ልና፤ ጭን​ቀ​ታ​ቸ​ው​ንም አይ​ቶ​አ​ልና፤ ሕዝ​ቡም ራሳ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው ሰገዱ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ