ዘፀአት 10:16-29
ዘፀአት 10:16-29 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት ጠራ፤ “አምላካችሁን እግዚአብሔርን እናንተንም በደልሁ። አሁን እንግዲህ በዚህ ጊዜ ብቻ ኃጢአቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑ አላቸው፤” ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ ወደ እግዚአብሔርም ለመነ። እግዚአብሔርም ከምዕራብ ዐውሎ ነፋሱን አስወገደ፤ አንበጣዎቹንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ አንበጣም በግብፅ ዳርቻ ሁሉ አልቀረም። እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ የእስራኤልንም ልጆች አልለቀቀም። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግብፅም አገር ላይ ሰው የሚዳስሰው ፅኑ ጨለማ ይሁን አለው። ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፥ በግብፅም አገር ሁሉ ላይ ፅኑ ጨለማ ሦስት ቀን ሆነ። ማንም ወንድሙን አላየም፤ ሦስት ቀንም ሙሉ ከስፍራው ማንም አልተነሣም፤ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ግን በተቀመጡበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው። ፈርዖንም ሙሴን ጠርቶ፦ “ሂዱ፤ እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ነገር ግን በጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ተዉ፤ ልጆቻችሁ ደግሞ ከእናንተ ጋር ይሂዱ፤” አለው። ሙሴም፦ “አንተ ደግሞ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የምንሠዋው መሥዋዕትንና የሚቃጠል መሥዋዕትን ትሰጠናለህ። አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማገልገል ከእነርሱ እንወስዳለንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ፤ አንድ ሰኮናም አይቀርም፤ አምላካችን የምናገለግለው ምን እንደሆነ ከዚያ እስክንደርስ አናውቅም፤” አለ። እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አጸና፤ ሊለቅቃቸውም አልወደደም። ፈርዖንም፦ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና ፊቴን እንዳታይ ተጠንቀቅ፤” አለው። ሙሴም፦ “እንደ ተናገረህ ይሁን፤ ፊትህን እንደ ገና አላይም፤” አለ።
ዘፀአት 10:16-29 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአምላካችሁ በእግዚአብሔር በእናንተም ላይ ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ እንግዲህ አሁን አንድ ጊዜ ደግሞ ኀጢአቴን ይቅር በሉኝና ይህን ቀሣፊ መዓት እንዲያስወግድልኝ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑልኝ።” ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ከዚያም እግዚአብሔር ነፋሱን ወደ ብርቱ የምዕራብ ነፋስ ለወጠው፤ ያም ነፋስ አንበጣዎቹን እየነዳ ወደ ቀይ ባሕር ከተታቸው፤ በግብጽ ምድር በየትኛውም ቦታ አንድም አንበጣ አልቀረም። እግዚአብሔር ግን የፈርዖንን ልብ አደነደነ፤ ፈርዖንም እስራኤላውያን እንዲሄዱ አልፈቀደም። ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “በግብጽ ላይ ድቅድቅ ጨለማ እንዲወርድ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በመላው ግብጽ ላይ ለሦስት ቀናት ድቅድቅ ያለ ጨለማ ሆነ። በእነዚያ ሦስት ቀናት ውስጥ አንዱ ሌላውን ማየት ወይም ከነበረበት ቦታ መንቀሳቀስ አይችልም ነበር። ይሁን እንጂ እስራኤላውያን በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ ብርሃን ነበር። ከዚያም ፈርዖን ሙሴን አስጠርቶ፣ “ሄዳችሁ እግዚአብሔርን አምልኩ፤ ሴቶቻችሁና ልጆቻችሁ ሳይቀሩ ዐብረዋችሁ ይሂዱ፤ በጎቻችሁ፣ ፍየሎቻችሁና የጋማ ከብቶቻችሁ ብቻ እዚሁ ይቅሩ” አለው። ሙሴም እንዲህ አለው፤ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሥዋዕትና የሚቃጠል መሥዋዕት እንድንሠዋ ፍቀድልን፤ እንስሶቻችን ሁሉ ዐብረው መሄድ አለባቸው። አንድ ሰኰና እንኳ አይቀርም። ከእንስሶቻችን መካከል ለአምላካችን ለእግዚአብሔር አምልኮ የምናቀርባቸው ይኖራሉ፤ ሆኖም እዚያ ከመድረሳችን በፊት እግዚአብሔርን ለማምለክ የምናቀርባቸው እንስሳት የትኞቹ እንደ ሆኑ አስቀድመን ለይተን ማወቅ አንችልም።” ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አደነደነ፤ ፈርዖንም ሕዝቡን መልቀቅ አልፈቀደም። ፈርዖን ሙሴን፣ “ከፊቴ ጥፋ! ሁለተኛ እኔ ዘንድ እንዳትደርስ! ፊቴን ባየህበት በዚያ ቀን ፈጽመህ እንደምትሞት ዕወቅ” አለው። ሙሴም፣ “እንዳልከው ይሁን፤ እኔም ዳግመኛ ከፊትህ አልደርስም” አለው።
ዘፀአት 10:16-29 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ንጉሡም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “አምላካችሁን እግዚአብሔርንና እናንተን በድያለሁ፤ እንግዲህስ እነሆ፥ አንድ ጊዜ ብቻ በደሌን ይቅር እንድትሉኝ እለምናችኋለሁ፤ ይህን ከባድ ቅጣት ከእኔ እንዲያስወግድም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑልኝ።” ሙሴም ከንጉሡ ፊት ወጥቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። እግዚአብሔርም የምሥራቁን ነፋስ የሚቋቋምና አንበጦቹንም ጠራርጎ ወደ ቀይ ባሕር የሚነዳ ብርቱ ነፋስ ከምዕራብ በኩል አስነሣ፤ በዚህ ዐይነት በመላው የግብጽ ምድር አንድ አንበጣ እንኳ አልቀረም። ነገር ግን እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ ስላደነደነ አሁንም እስራኤላውያንን አለቀቀም። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋው፤ በእጅ እስከሚዳሰስ ድረስ ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ የግብጽን ምድር ይሸፍናል” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በመላውም የግብጽ ምድር ለሦስት ቀን ጨለማ ሆነ። ግብጻውያን እርስ በርሳቸው ስለማይተያዩ ማንም ሰው እስከ ሦስት ቀን ከቤቱ መውጣት አልቻለም ነበር፤ እስራኤላውያን በሚኖሩበት ስፍራ ግን ብርሃን ነበር። ንጉሡም ሙሴን ጠርቶ “ሄዳችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ሴቶቻችሁና ልጆቻችሁም ከእናንተ ጋር መሄድ ይችላሉ፤ ነገር ግን በጎቻችሁና ፍየሎቻችሁ የቀንድ ከብቶቻችሁም እዚህ መቅረት ይኖርባቸዋል።” ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እንዲህ ከሆነማ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላም መሥዋዕት የምናቀርባቸው እንስሶች አንተ ትሰጠናለህ ማለት ነዋ? ከቶ ይህ ሊሆን አይችልም፤ እንስሶቻችንን ሁሉ እንወስዳለን፤ አንዲት ሰኮና እንኳ ወደ ኋላ አትቀርም፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን የምናገለግልባቸውን እንስሶች መርጠን ማቅረብ ያለብን እኛው ራሳችን ነን፤ እዚያም ከመድረሳችን በፊት ለእርሱ የምንሠዋቸው እንስሶች ምን ዐይነት እንደ ሆኑ ማወቅ አንችልም።” እግዚአብሔርም የንጉሡን ልብ ስላደነደነ ሕዝቡን መልቀቅ አልፈለገም፤ ስለዚህ ሙሴን “ዳግመኛ እንዳላይህ ከፊቴ ወዲያ ሂድ! እኔን በምታይበት ጊዜ እንደምትሞት ዕወቅ!” አለው። ሙሴም “እውነት ነው፤ አንተ እንዳልከው ዳግመኛ አላይህም” አለው።
ዘፀአት 10:16-29 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት ጠራ፥ “በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት፥ በእናንተም ላይ በደልሁ፤ አሁን እንግዲህ እንደገና በዚህ ጊዜ ብቻ ኀጢአቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ” አላቸው። ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ። እግዚአብሔርም ከባሕር ዐውሎ ነፋሱን አስወገደ፤ አንበጣዎችንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ አንበጣም እንኳን በግብፅ ዳርቻ ሁሉ አልቀረም። እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አጸና የእስራኤልንም ልጆች አልልቀቀም። እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግብፅም ሀገር ላይ ጨለማ ይሁን፤ ጨለማውም የሚዳሰስ ነው” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በግብፅም ሀገር ሁሉ ላይ ጽኑ ጨለማና ጭጋግ ሦስት ቀን ሆነ፤ ማንም ወንድሙን አላየም፤ ሦስት ቀን ሙሉም ከመኝታው ማንም አልተነሣም፤ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ግን በተቀመጡበት ስፍራ ሁሉ ብርሃን ነበራቸው። ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔርን አምልኩ፤ ነገር ግን በጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ብቻ ተዉ፤ ልጆቻችሁና ሴቶቻችሁ ግን ከእናንተ ጋር ይሂዱ” አላቸው። ሙሴም አለው፥ “አይሆንም! አንተ ደግሞ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የምንሠዋው መሥዋዕትንና የሚቃጠል መሥዋዕትን ትሰጠናለህ። ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ፤ አንድ ሰኰናም አይቀርም፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማምለክ ከእነርሱ እንወስዳለንና፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንደምናመልከው ከዚያ እስክንደርስ አናውቅም።” እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ ሊለቅቃቸውም አልወደደም። ፈርዖንም ሙሴን፥ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ በፊቴ በምትታይበት ቀን ትሞታለህና ዳግመኛ ፊቴን እንዳታይ ተጠንቀቅ” አለው። ሙሴም፥ “እንደ ተናገርህ ይሁን፤ ፊትህን እንደገና አላይም” አለ።
ዘፀአት 10:16-29 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአምላካችሁ በእግዚአብሔር በእናንተም ላይ ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ እንግዲህ አሁን አንድ ጊዜ ደግሞ ኀጢአቴን ይቅር በሉኝና ይህን ቀሣፊ መዓት እንዲያስወግድልኝ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑልኝ።” ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ከዚያም እግዚአብሔር ነፋሱን ወደ ብርቱ የምዕራብ ነፋስ ለወጠው፤ ያም ነፋስ አንበጣዎቹን እየነዳ ወደ ቀይ ባሕር ከተታቸው፤ በግብጽ ምድር በየትኛውም ቦታ አንድም አንበጣ አልቀረም። እግዚአብሔር ግን የፈርዖንን ልብ አደነደነ፤ ፈርዖንም እስራኤላውያን እንዲሄዱ አልፈቀደም። ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “በግብጽ ላይ ድቅድቅ ጨለማ እንዲወርድ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በመላው ግብጽ ላይ ለሦስት ቀናት ድቅድቅ ያለ ጨለማ ሆነ። በእነዚያ ሦስት ቀናት ውስጥ አንዱ ሌላውን ማየት ወይም ከነበረበት ቦታ መንቀሳቀስ አይችልም ነበር። ይሁን እንጂ እስራኤላውያን በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ ብርሃን ነበር። ከዚያም ፈርዖን ሙሴን አስጠርቶ፣ “ሄዳችሁ እግዚአብሔርን አምልኩ፤ ሴቶቻችሁና ልጆቻችሁ ሳይቀሩ ዐብረዋችሁ ይሂዱ፤ በጎቻችሁ፣ ፍየሎቻችሁና የጋማ ከብቶቻችሁ ብቻ እዚሁ ይቅሩ” አለው። ሙሴም እንዲህ አለው፤ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሥዋዕትና የሚቃጠል መሥዋዕት እንድንሠዋ ፍቀድልን፤ እንስሶቻችን ሁሉ ዐብረው መሄድ አለባቸው። አንድ ሰኰና እንኳ አይቀርም። ከእንስሶቻችን መካከል ለአምላካችን ለእግዚአብሔር አምልኮ የምናቀርባቸው ይኖራሉ፤ ሆኖም እዚያ ከመድረሳችን በፊት እግዚአብሔርን ለማምለክ የምናቀርባቸው እንስሳት የትኞቹ እንደ ሆኑ አስቀድመን ለይተን ማወቅ አንችልም።” ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አደነደነ፤ ፈርዖንም ሕዝቡን መልቀቅ አልፈቀደም። ፈርዖን ሙሴን፣ “ከፊቴ ጥፋ! ሁለተኛ እኔ ዘንድ እንዳትደርስ! ፊቴን ባየህበት በዚያ ቀን ፈጽመህ እንደምትሞት ዕወቅ” አለው። ሙሴም፣ “እንዳልከው ይሁን፤ እኔም ዳግመኛ ከፊትህ አልደርስም” አለው።
ዘፀአት 10:16-29 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት ጠራ፤ “አምላካችሁን እግዚአብሔርን እናንተንም በደልሁ። አሁን እንግዲህ በዚህ ጊዜ ብቻ ኃጢአቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑ አላቸው፤” ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ ወደ እግዚአብሔርም ለመነ። እግዚአብሔርም ከምዕራብ ዐውሎ ነፋሱን አስወገደ፤ አንበጣዎቹንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ አንበጣም በግብፅ ዳርቻ ሁሉ አልቀረም። እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ የእስራኤልንም ልጆች አልለቀቀም። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግብፅም አገር ላይ ሰው የሚዳስሰው ፅኑ ጨለማ ይሁን አለው። ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፥ በግብፅም አገር ሁሉ ላይ ፅኑ ጨለማ ሦስት ቀን ሆነ። ማንም ወንድሙን አላየም፤ ሦስት ቀንም ሙሉ ከስፍራው ማንም አልተነሣም፤ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ግን በተቀመጡበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው። ፈርዖንም ሙሴን ጠርቶ፦ “ሂዱ፤ እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ነገር ግን በጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ተዉ፤ ልጆቻችሁ ደግሞ ከእናንተ ጋር ይሂዱ፤” አለው። ሙሴም፦ “አንተ ደግሞ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የምንሠዋው መሥዋዕትንና የሚቃጠል መሥዋዕትን ትሰጠናለህ። አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማገልገል ከእነርሱ እንወስዳለንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ፤ አንድ ሰኮናም አይቀርም፤ አምላካችን የምናገለግለው ምን እንደሆነ ከዚያ እስክንደርስ አናውቅም፤” አለ። እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አጸና፤ ሊለቅቃቸውም አልወደደም። ፈርዖንም፦ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና ፊቴን እንዳታይ ተጠንቀቅ፤” አለው። ሙሴም፦ “እንደ ተናገረህ ይሁን፤ ፊትህን እንደ ገና አላይም፤” አለ።
ዘፀአት 10:16-29 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ንጉሡም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “አምላካችሁን እግዚአብሔርንና እናንተን በድያለሁ፤ እንግዲህስ እነሆ፥ አንድ ጊዜ ብቻ በደሌን ይቅር እንድትሉኝ እለምናችኋለሁ፤ ይህን ከባድ ቅጣት ከእኔ እንዲያስወግድም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑልኝ።” ሙሴም ከንጉሡ ፊት ወጥቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። እግዚአብሔርም የምሥራቁን ነፋስ የሚቋቋምና አንበጦቹንም ጠራርጎ ወደ ቀይ ባሕር የሚነዳ ብርቱ ነፋስ ከምዕራብ በኩል አስነሣ፤ በዚህ ዐይነት በመላው የግብጽ ምድር አንድ አንበጣ እንኳ አልቀረም። ነገር ግን እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ ስላደነደነ አሁንም እስራኤላውያንን አለቀቀም። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋው፤ በእጅ እስከሚዳሰስ ድረስ ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ የግብጽን ምድር ይሸፍናል” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በመላውም የግብጽ ምድር ለሦስት ቀን ጨለማ ሆነ። ግብጻውያን እርስ በርሳቸው ስለማይተያዩ ማንም ሰው እስከ ሦስት ቀን ከቤቱ መውጣት አልቻለም ነበር፤ እስራኤላውያን በሚኖሩበት ስፍራ ግን ብርሃን ነበር። ንጉሡም ሙሴን ጠርቶ “ሄዳችሁ እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ሴቶቻችሁና ልጆቻችሁም ከእናንተ ጋር መሄድ ይችላሉ፤ ነገር ግን በጎቻችሁና ፍየሎቻችሁ የቀንድ ከብቶቻችሁም እዚህ መቅረት ይኖርባቸዋል።” ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እንዲህ ከሆነማ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላም መሥዋዕት የምናቀርባቸው እንስሶች አንተ ትሰጠናለህ ማለት ነዋ? ከቶ ይህ ሊሆን አይችልም፤ እንስሶቻችንን ሁሉ እንወስዳለን፤ አንዲት ሰኮና እንኳ ወደ ኋላ አትቀርም፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን የምናገለግልባቸውን እንስሶች መርጠን ማቅረብ ያለብን እኛው ራሳችን ነን፤ እዚያም ከመድረሳችን በፊት ለእርሱ የምንሠዋቸው እንስሶች ምን ዐይነት እንደ ሆኑ ማወቅ አንችልም።” እግዚአብሔርም የንጉሡን ልብ ስላደነደነ ሕዝቡን መልቀቅ አልፈለገም፤ ስለዚህ ሙሴን “ዳግመኛ እንዳላይህ ከፊቴ ወዲያ ሂድ! እኔን በምታይበት ጊዜ እንደምትሞት ዕወቅ!” አለው። ሙሴም “እውነት ነው፤ አንተ እንዳልከው ዳግመኛ አላይህም” አለው።
ዘፀአት 10:16-29 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠራና እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ አምላካችሁንና እናንተን በደልሁ፤ አሁን እንግዲህ አንድ ጊዜ ብቻ ኃጢአቴን ይቅር በሉኝ፥ ይህንን ሞት ከእኔ እንዲያነሣልኝ ብቻ ጌታ አምላካችሁን ለምኑልኝ።” እርሱም ከፈርዖን ፊት ወጣ፥ ወደ ጌታም ፀለየ። ጌታም ከምዕራብ ዐውሎ ነፋሱን መለሰ፥ አንበጣዎቹንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ ስንኳ አንበጣ በግብጽ አገር አልቀረም። ጌታም የፈርዖንን ልብ አጸና የእስራኤልንም ልጆች አልለቀቀም። ጌታም ሙሴን፦ “በግብጽ ምድር ላይ ጨለማ እንዲሆን፥ ማንም ሰው የሚያውቀው ጨለማ እንዲሆን እጅህን ወደ ሰማያት ዘርጋ” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ሰማያት ዘረጋ፥ በግብጽም ምድር ሁሉ ላይ ሦስት ቀን ፅኑ ጨለማ ሆነ፤ ማንም ወንድሙን አላየም፥ ሦስት ቀንም ሙሉ ማንም ከስፍራው አልተነሣም፤ የእስራኤል ልጆች ሁሉ ግን በተቀመጡበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው። ፈርዖንም ሙሴን ጠርቶ፦ “ሂዱ፥ ጌታን አገልግሉ፤ ነገር ግን በጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ተዉ፤ ልጆቻችሁም ከእናንተ ጋር ይሂዱ” አለው። ሙሴም እንዲህ አለው፦ “አንተ ደግሞ ለጌታ አምላካችን የምንሠዋው መሥዋዕትንና የሚቃጠል መሥዋዕትን በእጃችን ትሰጠናለህ። ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ አንድ ሰኮናም አይቀርም፥ ጌታ አምላካችንን ለማገልገል ከእነርሱ እንወስዳለንና፤ ጌታን የምናገለግለው በምን እንደሆነ እዚያ እስክንደርስ አናውቅም።” ጌታ ግን የፈርዖንን ልብ አጸና፥ ሊለቅቃቸውም አልወደደም። ፈርዖንም፦ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ ተጠንቀቅ፤ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና ፊቴን እንዳታይ” አለው። ሙሴም፦ “እንደ ተናገረህ ይሁን፤ ፊትህን እንደገና አላይም” አለ።