ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት ጠራ፥ “በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት፥ በእናንተም ላይ በደልሁ፤ አሁን እንግዲህ እንደገና በዚህ ጊዜ ብቻ ኀጢአቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ” አላቸው። ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ። እግዚአብሔርም ከባሕር ዐውሎ ነፋሱን አስወገደ፤ አንበጣዎችንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ አንበጣም እንኳን በግብፅ ዳርቻ ሁሉ አልቀረም። እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አጸና የእስራኤልንም ልጆች አልልቀቀም። እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፤ በግብፅም ሀገር ላይ ጨለማ ይሁን፤ ጨለማውም የሚዳሰስ ነው” አለው። ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በግብፅም ሀገር ሁሉ ላይ ጽኑ ጨለማና ጭጋግ ሦስት ቀን ሆነ፤ ማንም ወንድሙን አላየም፤ ሦስት ቀን ሙሉም ከመኝታው ማንም አልተነሣም፤ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ግን በተቀመጡበት ስፍራ ሁሉ ብርሃን ነበራቸው። ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፥ “ሂዱ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔርን አምልኩ፤ ነገር ግን በጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ብቻ ተዉ፤ ልጆቻችሁና ሴቶቻችሁ ግን ከእናንተ ጋር ይሂዱ” አላቸው። ሙሴም አለው፥ “አይሆንም! አንተ ደግሞ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የምንሠዋው መሥዋዕትንና የሚቃጠል መሥዋዕትን ትሰጠናለህ። ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ፤ አንድ ሰኰናም አይቀርም፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማምለክ ከእነርሱ እንወስዳለንና፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንደምናመልከው ከዚያ እስክንደርስ አናውቅም።” እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ ሊለቅቃቸውም አልወደደም። ፈርዖንም ሙሴን፥ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ በፊቴ በምትታይበት ቀን ትሞታለህና ዳግመኛ ፊቴን እንዳታይ ተጠንቀቅ” አለው። ሙሴም፥ “እንደ ተናገርህ ይሁን፤ ፊትህን እንደገና አላይም” አለ።
ኦሪት ዘፀአት 10 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፀአት 10:16-29
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች