ኤፌሶን 6:1-3
ኤፌሶን 6:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታችን ታዘዙ፤ ይህ የሚገባ ነውና። በሕግም ተስፋ ያለው የመጀመሪያው ትእዛዝ ይህ ነው፥ “አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም ይሆንልህ ዘንድ፥ በምድር ላይም ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ።”
Share
ኤፌሶን 6 ያንብቡኤፌሶን 6:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ልጆች ሆይ፤ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፤ ይህ ተገቢ ነውና። “አባትህንና እናትህን አክብር” በሚለው ቀዳሚ ትእዛዝ ውስጥ ያለው ተስፋ፣ “መልካም እንዲሆንልህ፣ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም” የሚል ነው።
Share
ኤፌሶን 6 ያንብቡኤፌሶን 6:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና። መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት።
Share
ኤፌሶን 6 ያንብቡኤፌሶን 6:1-3 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ልጆች ሆይ! ተገቢ ነገር ስለ ሆነ በጌታ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ። “አባትህንና እናትህን አክብር” የሚለው ትእዛዝ የተስፋ ቃል ያለበት የመጀመሪያ ትእዛዝ ነው፤ ይህንንም ብታደርግ “ሁሉ ነገር ይሰምርልሃል፤ በዚህም ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝማል።”
Share
ኤፌሶን 6 ያንብቡ