የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 6

6
ስለ ልጆ​ችና ስለ ወላ​ጆች
1 # ቈላ​. 3፥20። ልጆች ሆይ፥ ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ችሁ በጌ​ታ​ችን ታዘዙ፤ ይህ የሚ​ገባ ነውና። 2በሕ​ግም ተስፋ ያለው የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ትእ​ዛዝ ይህ ነው፥ “አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤ 3#ዘፀ. 20፥12፤ ዘዳ. 5፥16። መል​ካም ይሆ​ን​ልህ ዘንድ፥ በም​ድር ላይም ዕድ​ሜህ ይረ​ዝም ዘንድ።” 4#ቈላ​. 3፥22-25። እና​ን​ተም አባ​ቶች ሆይ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተግ​ሣ​ጽና ምክር አሳ​ድ​ጉ​አ​ቸው እንጂ አታ​ስ​ቈ​ጡ​አ​ቸው።
ስለ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና ስለ አሳ​ዳ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸው
5አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም በሥ​ጋ​ችሁ ለሚ​ገ​ዙ​አ​ችሁ ጌቶ​ቻ​ችሁ በፍ​ር​ሀ​ትና በመ​ደ​ን​ገጥ፥ በሰፊ ልብም ለክ​ር​ስ​ቶስ እን​ደ​ም​ት​ገዙ ታዘዙ። 6የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርጉ እንደ ክር​ስ​ቶስ ባሮች እንጂ ለሰው ደስ እን​ደ​ሚ​ያ​ሰኝ ለታ​ይታ አይ​ደ​ለም። 7ለሰው ሳይ​ሆን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ደ​ም​ት​ገዙ በፍ​ጹም ሰው​ነ​ታ​ችሁ በፍ​ቅ​ርና በበጎ ፈቃድ ተገ​ዙ​ላ​ቸው። 8ጌታም ቢሆን፥ አገ​ል​ጋ​ይም ቢሆን መል​ካም ያደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዋጋ እን​ደ​ሚ​ያ​ገኝ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና። 9#ዘዳ. 10፥17፤ ቈላ​. 3፥25፤ 4፥1። እና​ን​ተም ጌቶች ሆይ፥ ቍጣ​ች​ሁን እያ​በ​ረ​ዳ​ችሁ፥ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ይቅር እያ​ላ​ችሁ፥ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ ፊት አይቶ የማ​ያ​ዳላ ጌታ በእ​ነ​ር​ሱና በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ማይ እንደ አለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።
ሃይ​ማ​ኖ​ትና ፍጹም ተጋ​ድሎ
10እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በኀ​ይሉ ጽናት በርቱ። 11የሰ​ይ​ጣ​ንን ተን​ኰል መቋ​ቋም እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጋሻ ልበሱ። 12ሰል​ፋ​ችሁ፦#ግሪኩ “ከአ​ለ​ቆ​ችና ከሥ​ል​ጣ​ናት ጋር” የሚል ይጨ​ም​ራል። ከጨ​ለማ ገዦች ጋርና ከሰ​ማይ በታች ካሉ ከክ​ፉ​ዎች አጋ​ን​ንት ጋር ነው እንጂ ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ጋር አይ​ደ​ለ​ምና። 13ስለ​ዚ​ህም በክፉ ቀን መቃ​ወም እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጋሻ ያዙ፤ እን​ድ​ት​ጸ​ኑም በሁሉ የተ​ዘ​ጋ​ጃ​ችሁ ሁኑ። 14#ኢሳ. 11፥5፤ 59፥17። እን​ግ​ዲህ ወገ​ባ​ች​ሁን በእ​ው​ነት ታጥ​ቃ​ችሁ ቁሙ፤ የጽ​ድ​ቅ​ንም ጥሩር ልበሱ። 15#ኢሳ. 52፥7። የሰ​ላም ወን​ጌል ኀይ​ል​ንም ተጫ​ም​ታ​ችሁ ቁሙ። 16ከዚ​ህም ሁሉ ጋር የሚ​ን​በ​ለ​በሉ የክ​ፉን ፍላ​ፃ​ዎች ሁሉ ማጥ​ፋት እን​ድ​ት​ችሉ የእ​ም​ነ​ትን ጋሻ አንሡ። 17#ኢሳ. 59፥17። የመ​ዳ​ን​ንም የራስ ቍር በራ​ሳ​ችሁ ላይ ጫኑ፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስ​ንም ሰይፍ ያዙ፤ ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው። 18በጸ​ሎ​ትና በም​ልጃ ሁሉ ዘወ​ትር በመ​ን​ፈስ ጸልዩ፤ ከዚ​ህም ጋር ስለ ቅዱ​ሳን ሁሉ ለመ​ጸ​ለይ ሁል​ጊዜ ትጉ፤ 19ለእ​ኔም፦ ቃልን እን​ዲ​ሰ​ጠኝ፥ አፌ​ንም ከፍቼ የወ​ን​ጌ​ልን ምሥ​ጢር በግ​ልጥ እን​ድ​ና​ገር ጸል​ዩ​ልኝ። 20ስለ ወን​ጌ​ልም በእ​ስ​ራት መል​እ​ክ​ተኛ የሆ​ንሁ፦ መና​ገር እን​ደ​ሚ​ገ​ባኝ ስለ እርሱ በግ​ልጥ እና​ገር ዘንድ ጸልዩ።
21 # የሐዋ. 20፥4፤ 2ጢሞ. 4፥12። እና​ን​ተም ዜና​ዬን እን​ድ​ታ​ውቁ የም​ን​ወ​ደው ወን​ድ​ማ​ችን የታ​መነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ቲኪ​ቆስ የም​ሠ​ራ​ውን ሁሉ ያስ​ረ​ዳ​ች​ኋል። 22#ቈላ​. 4፥7-8። ዜና​ዬን ታውቁ ዘንድ፥ ልባ​ች​ሁም ይጽ​ናና ዘንድ፥ ስለ​ዚህ ወደ እና​ንተ ላክ​ሁት። 23ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ከእ​ም​ነት ጋር ሰላ​ምና ፍቅር ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ይሁን። 24ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ባለ መጥ​ፋት ከሚ​ወ​ዱት ሁሉ ጋር ጸጋ ይሁን። አሜን።
በሮሜ ተጽፋ በቲ​ኪ​ቆስ እጅ ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች የተ​ላ​ከች መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች።
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ