ኤፌሶን 5:1-4
ኤፌሶን 5:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን ምሰሉ፤ ክርስቶስ እንደ ወደደን ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዐዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ተመላለሱ። ማንኛውም የዝሙት ወይም የርኩሰት ወይም የሥሥት ነገር ከቶ በመካከላችሁ አይነሣ፤ ይህ ቅዱስ ለሆነው ለእግዚአብሔር ሕዝብ አይገባምና። የሚያሳፍርና ተራ የሆነ ንግግር፣ ዋዛ ፈዛዛም ለእናንተ ስለማይገባ በመካከላችሁ አይኑር፤ ይልቁንስ የምታመሰግኑ ሁኑ።
ኤፌሶን 5:1-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እንግዲህ እንደ ተወዳጅ ልጆች እናንተም የእግዚአብሔርን አርአያ ተከተሉ። ክርስቶስ እንደ ወደደንና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ሕይወቱን ስለ እኛ አሳልፎ እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ኑሩ። እንዲህ ዐይነቱ ነገር ለክርስቲያኖች ስለማይስማማ ዝሙት ወይም ማናቸውንም ዐይነት ርኲሰት ወይም ንፍገት ማድረግ ይቅርና ወሬው እንኳ ሊሰማባችሁ አይገባም። ይልቅስ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ እንጂ የሚያስቀይምና የሞኝነት አነጋገር፥ ወይም የፌዝን ነገር መናገር አይገባችሁም፤ እንዲህ ያለ ነገር ለእናንተ ተስማሚ አይደለም።
ኤፌሶን 5:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን ምሰሉ። ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ። ነገር ግን ለቅዱሳን እንደሚገባቸው፥ ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም ቅሚያ አይሰማባችሁ። የሚያሳፍር ነገርም፥ የስንፍና ነገርም፥ ወይም የማይገባ የዋዛ ነገር በእናንተ ዘንድ አይሁን፤ ማመስገን ይሁን እንጂ።
ኤፌሶን 5:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን ምሰሉ፤ ክርስቶስ እንደ ወደደን ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዐዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ተመላለሱ። ማንኛውም የዝሙት ወይም የርኩሰት ወይም የሥሥት ነገር ከቶ በመካከላችሁ አይነሣ፤ ይህ ቅዱስ ለሆነው ለእግዚአብሔር ሕዝብ አይገባምና። የሚያሳፍርና ተራ የሆነ ንግግር፣ ዋዛ ፈዛዛም ለእናንተ ስለማይገባ በመካከላችሁ አይኑር፤ ይልቁንስ የምታመሰግኑ ሁኑ።
ኤፌሶን 5:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ። ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤ የሚያሳፍር ነገርም የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸውና አይሁኑ፥ ይልቁን ምስጋና እንጂ።
ኤፌሶን 5:1-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እንግዲህ እንደ ተወዳጅ ልጆች እናንተም የእግዚአብሔርን አርአያ ተከተሉ። ክርስቶስ እንደ ወደደንና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ሕይወቱን ስለ እኛ አሳልፎ እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ኑሩ። እንዲህ ዐይነቱ ነገር ለክርስቲያኖች ስለማይስማማ ዝሙት ወይም ማናቸውንም ዐይነት ርኲሰት ወይም ንፍገት ማድረግ ይቅርና ወሬው እንኳ ሊሰማባችሁ አይገባም። ይልቅስ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ እንጂ የሚያስቀይምና የሞኝነት አነጋገር፥ ወይም የፌዝን ነገር መናገር አይገባችሁም፤ እንዲህ ያለ ነገር ለእናንተ ተስማሚ አይደለም።
ኤፌሶን 5:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን ምሰሉ፤ ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ። ለቅዱሳን የማይገባው፥ ማንኛውም የዝሙትና የርኩሰት፥ ወይም የስስት ነገር ሁሉ በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤ የሚያጸይፍ ነገር፥ ተራና የእንዝህላል ንግግርም ፈጽመው በመካከላችሁ አይኑሩ፤ ይልቁን አመስጋኞች ሁኑ።