ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 5:1-4

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 5:1-4 አማ2000

እን​ግ​ዲህ እንደ ተወ​ደዱ ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሰሉ። ክር​ስ​ቶስ እንደ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ራሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ የሚ​ሆን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ቍር​ባን አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላ​ችሁ በፍ​ቅር ተመ​ላ​ለሱ። ነገር ግን ለቅ​ዱ​ሳን እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ቸው፥ ዝሙ​ትና ርኵ​ሰት ሁሉ ወይም ቅሚያ አይ​ሰ​ማ​ባ​ችሁ። የሚ​ያ​ሳ​ፍር ነገ​ርም፥ የስ​ን​ፍና ነገ​ርም፥ ወይም የማ​ይ​ገባ የዋዛ ነገር በእ​ና​ንተ ዘንድ አይ​ሁን፤ ማመ​ስ​ገን ይሁን እንጂ።