መክብብ 11:3-6
መክብብ 11:3-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ደመናት ውሃ ካዘሉ፣ በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባሉ፤ ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ፣ በወደቀበት ቦታ በዚያ ይጋደማል። ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ ደመናትንም የሚያይ አያጭድም። የነፋስን መንገድ እንደማታውቅ፣ ሕይወት ወይም መንፈስ በእናት ማሕፀን ውስጥ ወደሚገኘው አካል እንዴት እንደሚገባም እንደማታውቅ ሁሉ፣ ሁሉን ሠሪ የሆነውን፣ የአምላክን ሥራ ማስተዋል አትችልም። ጧት ላይ ዘርህን ዝራ፤ ማታም ላይ እጅህ ሥራ አይፍታ፤ ይህ ወይም ያ፣ ወይም ሁለቱ መልካም ይሁኑ፣ የቱ እንደሚያፈራ አታውቅምና።
መክብብ 11:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ደመናት ዝናብ በሞሉ ጊዜ በምድር ላይ ያፈስሱታል፥ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት ስፍራ በዚያ ይኖራል። ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናትንም የሚመለከት አያጭድም። የነፋስ መንገድ እንዴት እንደ ሆነች አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፥ እንዲሁም ሁሉን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ሥራ አታውቅም። ወይም ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው።
መክብብ 11:3-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ደመናት ዝናም በሞሉ ጊዜ በምድር ላይ ያፈስሱታል፤ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት ስፍራ በዚያ ይኖራል። ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናትንም የሚመለከት አያጭድም። የነፋስ መንገድ እንዴት እንደ ሆነች፥ አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፥ እንዲሁም ሁሉን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ሥራ አታውቅም። ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንደ ሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው።
መክብብ 11:3-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ደመናት ውሃ ካዘሉ፣ በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባሉ፤ ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ፣ በወደቀበት ቦታ በዚያ ይጋደማል። ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ ደመናትንም የሚያይ አያጭድም። የነፋስን መንገድ እንደማታውቅ፣ ሕይወት ወይም መንፈስ በእናት ማሕፀን ውስጥ ወደሚገኘው አካል እንዴት እንደሚገባም እንደማታውቅ ሁሉ፣ ሁሉን ሠሪ የሆነውን፣ የአምላክን ሥራ ማስተዋል አትችልም። ጧት ላይ ዘርህን ዝራ፤ ማታም ላይ እጅህ ሥራ አይፍታ፤ ይህ ወይም ያ፣ ወይም ሁለቱ መልካም ይሁኑ፣ የቱ እንደሚያፈራ አታውቅምና።
መክብብ 11:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ደመናት ዝናብ በሞሉ ጊዜ በምድር ላይ ያፈስሱታል፥ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት ስፍራ በዚያ ይኖራል። ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናትንም የሚመለከት አያጭድም። የነፋስ መንገድ እንዴት እንደ ሆነች አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፥ እንዲሁም ሁሉን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ሥራ አታውቅም። ወይም ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው።
መክብብ 11:3-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ደመና ብዙ ውሃ ባዘለ ጊዜ በምድር ላይ ያዘንበዋል፤ ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ በዚያው በወደቀበት ስፍራ ይኖራል። ነፋስን የሚጠብቅ አይዘራም፤ ደመናን የሚመለከት አያጭድም። የነፋስን አካሄድና የሰውም ሕይወት አፈጣጠር በእናቱ ማሕፀን እንዴት እንደሚጀመር እንደማታውቅ የሁሉ ነገር ፈጣሪ እግዚአብሔር ሥራውን እንዴት እንደሚያከናውን ማወቅ አትችልም። ጧትም ሆነ ማታ ዘር መዝራትህን አታቋርጥ፤ ሁሉም ይበቅል ወይም አይበቅል እንደ ሆነ የትኛው አዘራር እንደሚሻል ለይተህ ማወቅ አይቻልህም።
መክብብ 11:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)