መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 11:3-6

መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 11:3-6 አማ2000

ደመ​ናት ዝናም በሞሉ ጊዜ በም​ድር ላይ ያፈ​ስ​ሱ​ታል፤ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወ​ድቅ፥ ዛፉ በወ​ደ​ቀ​በት ስፍራ በዚያ ይኖ​ራል። ነፋ​ስን የሚ​ጠ​ባ​በቅ አይ​ዘ​ራም፥ ደመ​ና​ት​ንም የሚ​መ​ለ​ከት አያ​ጭ​ድም። የነ​ፋስ መን​ገድ እን​ዴት እንደ ሆነች፥ አጥ​ን​ትም በእ​ር​ጉዝ ሆድ እን​ዴት እን​ድትዋ​ደድ እን​ደ​ማ​ታ​ውቅ፥ እን​ዲ​ሁም ሁሉን የሚ​ሠ​ራ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ አታ​ው​ቅም። ይህ ወይም ያ ማና​ቸው እን​ዲ​በ​ቅል ወይም ሁለቱ መል​ካም እንደ ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምና በማ​ለዳ ዘር​ህን ዝራ፥ በማ​ታም እጅ​ህን አት​ተው።