መክብብ 11:3-6

መክብብ 11:3-6 NASV

ደመናት ውሃ ካዘሉ፣ በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባሉ፤ ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ፣ በወደቀበት ቦታ በዚያ ይጋደማል። ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፤ ደመናትንም የሚያይ አያጭድም። የነፋስን መንገድ እንደማታውቅ፣ ሕይወት ወይም መንፈስ በእናት ማሕፀን ውስጥ ወደሚገኘው አካል እንዴት እንደሚገባም እንደማታውቅ ሁሉ፣ ሁሉን ሠሪ የሆነውን፣ የአምላክን ሥራ ማስተዋል አትችልም። ጧት ላይ ዘርህን ዝራ፤ ማታም ላይ እጅህ ሥራ አይፍታ፤ ይህ ወይም ያ፣ ወይም ሁለቱ መልካም ይሁኑ፣ የቱ እንደሚያፈራ አታውቅምና።