ዘዳግም 10:17-19
ዘዳግም 10:17-19 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የአማልክት አምላክ (ኤሎሂም)፣ የጌቶች ጌታ (አዶናይ) ታላቅ አምላክ (ኤሎሂም)፣ ኀያልና የሚያስፈራ፣ አድልዎ የማያደርግ፣ መማለጃም የማይቀበል ነውና። እርሱ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች ይፈርዳል፤ መጻተኛውንም ምግብና ልብስ በመስጠት ይወድዳል። ስለዚህ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና መጻተኛን ውደዱ።
ዘዳግም 10:17-19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶች ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኀያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድም የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና። ለመጻተኛ፥ ለድሃ አደጉና ለመበለቲቱ ይፈርዳል፤ መብልና ልብስም ይሰጠው ዘንድ ስደተኛውን ይወድዳል። እናንተ በግብፅ ሀገር ስደተኞች ነበራችሁና ስለዚህ ስደተኛውን ውደዱ።
ዘዳግም 10:16-19 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ከእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ። ለድሃ አደጉና ለመበለቲቱ ይፈርዳል፥ መብልና ልብስም ይሰጠው ዘንድ ስደተኛውን ይወድዳል። እናንተ በግብፅ አገር ስደተኞች ነበራችሁና ስለዚህ ስደተኛውን ውደዱ።
ዘዳግም 10:17-19 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር አምላካችሁ ከባዕዳን አማልክት ሁሉና ከኀይላትም ሁሉ በላይ ታላቅና ብርቱ ስለ ሆነ በፍርሃት መከበር ይገባዋል። እርሱ በፍርድ አያዳላም፤ ጉቦም አይቀበልም። እርሱ እናትና አባት ለሌላቸው ድኻ አደጎችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች በትክክል ይፈርዳል፤ እርሱ በእኛ ሕዝብ መካከል የሚኖሩትንም መጻተኞች ሁሉ ስለሚወድ ምግብና ልብስ ይሰጣቸዋል። ስለዚህም እናንተም ለእነዚህ ስደተኞች ፍቅራችሁን ልታሳዩአቸው ይገባል፤ እናንተም ራሳችሁ በግብጽ ምድር መጻተኞች የሆናችሁበት ጊዜ ነበር።