የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሐዋርያት ሥራ 8:26-39

ሐዋርያት ሥራ 8:26-39 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ፊል​ጶ​ስን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በቀ​ትር ጊዜ ተነ​ሣና በደ​ቡብ በኩል ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ጋዛ በሚ​ያ​ወ​ር​ደው በም​ድረ በዳው መን​ገድ ሂድ።” ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ እነ​ሆም፥ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ሥት የሕ​ን​ደኬ ጃን​ደ​ረባ ከሹ​ሞ​ችዋ የበ​ለጠ፥ በሀ​ብ​ቷም ሁሉ ላይ በጅ​ሮ​ንድ የነ​በረ፥ አንድ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ሊሰ​ግድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ። ሲመ​ለ​ስም በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተቀ​ምጦ የነ​ቢዩ የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን መጽ​ሐፍ ያነብ ነበር። መን​ፈስ ቅዱ​ስም ፊል​ጶ​ስን፥ “ሂድ፤ ይህን ሰረ​ገላ ተከ​ተ​ለው” አለው። ፊል​ጶ​ስም ፈጥኖ ደርሶ የነ​ቢ​ዩን የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን መጽ​ሐፍ ሲያ​ነብ ሰማው፤ ፊል​ጶ​ስም፥ “በውኑ የም​ታ​ነ​በ​ውን ታው​ቀ​ዋ​ለ​ህን?” አለው። ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “ያስ​ተ​ማ​ረኝ ሳይ​ኖር በምን አው​ቀ​ዋ​ለሁ?” አለው፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ወጥቶ አብ​ሮት ይቀ​መጥ ዘንድ ፊል​ጶ​ስን ለመ​ነው። ያነ​በው የነ​በረ የመ​ጽ​ሐፉ ቃልም እን​ዲህ የሚል ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታ​ረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦ​ትም በሚ​ሸ​ል​ተው ፊት እን​ደ​ማ​ይ​ና​ገር እን​ዲሁ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም። በው​ር​ደቱ ፍርዱ ተወ​ገደ፤ ሕይ​ወቱ ከም​ድር ተወ​ግ​ዶ​አ​ልና ትው​ል​ዱን ማን ይና​ገ​ራል?” ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም ለፊ​ል​ጶስ መልሶ፥ “ነቢዩ ስለ ማን እን​ዲህ ይላል? ስለ ራሱ ነውን? ወይስ ስለ ሌላ? እባ​ክህ ንገ​ረኝ” አለው። ፊል​ጶ​ስም አፉን ከፈተ፤ ስለ ኢየ​ሱ​ስም ከዚ​ያው መጽ​ሐፍ ጀምሮ አስ​ተ​ማ​ረው። በመ​ን​ገድ ሲሄ​ዱም ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም፥ “እነሆ፥ ውኃ፥ መጠ​መ​ቅን ምን ይከ​ለ​ክ​ለ​ኛል?” አለው። ፊል​ጶ​ስም፥ “በፍ​ጹም ልብህ ብታ​ምን ይገ​ባ​ሃል” አለው፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም መልሶ፥ “ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እኔ አም​ና​ለሁ” አለው። ሰረ​ገ​ላ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ቆሙ አዘዘ፤ አቁ​መ​ውም ፊል​ጶ​ስና ጃን​ደ​ረ​ባው በአ​ን​ድ​ነት ወደ ውኃው ወረዱ፤ አጠ​መ​ቀ​ውም። ከው​ኃ​ዉም ከወጡ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ፊል​ጶ​ስን ነጥቆ ወሰ​ደው፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ዉም ከዚያ ወዲያ አላ​የ​ውም፤ ደስ እያ​ለ​ውም መን​ገ​ዱን ሄደ።

ሐዋርያት ሥራ 8:26-39 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የጌታም መልአክ ፊልጶስን፣ “ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ” አለው፤ እርሱም ተነሥቶ ሄደ። እነሆ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ ባለሟልና የሀብት ንብረቷ ሁሉ አዛዥ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አገኘ። ይህም ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር። ሲመለስም በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብብ ነበር። መንፈስም ፊልጶስን፣ “ሂድ፤ ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው። ፊልጶስም ፈጥኖ ወደ ሠረገላው ሄደ፤ ጃንደረባውም የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብብ ሰምቶ፣ “ለመሆኑ፣ የምታነብበውን ታስተውለዋለህን?” አለው። ጃንደረባውም፣ “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት አድርጌ አስተውላለሁ” አለው፤ እርሱም ወደ ሠረገላው ወጥቶ አብሮት እንዲቀመጥ ፊልጶስን ለመነው። ጃንደረባው ያነብብ የነበረው የመጽሐፍ ክፍል ይህ ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦት በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፣ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። ራሱን በማዋረዱም ፍትሕን ተነፈገ፤ ሕይወቱ ከምድር ተወግዳለችና፣ ስለ ትውልዱ ማን ሊናገር ይችላል?” ጃንደረባውም መልሶ ፊልጶስን፣ “ነቢዩ ይህን የሚናገረው ስለ ማን ነው? ስለ ራሱ ነው ወይስ ስለ ሌላ ሰው? እባክህ ንገረኝ” አለው። ፊልጶስም አፉን ከፈተ፤ ከዚሁም መጽሐፍ ክፍል ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌል ሰበከለት። በመጓዝ ላይ ሳሉም ውሃ ካለበት ስፍራ ደረሱ፤ ጃንደረባውም፣ “እነሆ፤ ውሃ እዚህ አለ፤ ታዲያ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምን ነገር አለ?” አለው። ፊልጶስም፣ “በፍጹም ልብህ ካመንህ መጠመቅ ትችላለህ” አለው። ጃንደረባውም፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ” ሲል መለሰለት፤ ሠረገላውም እንዲቆም አዘዘ። ከዚያም ሁለቱ አብረው ወደ ውሃው ወረዱ፤ ፊልጶስም ጃንደረባውን አጠመቀው። ከውሃውም በወጡ ጊዜ፣ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ነጥቆ ወሰደው፤ ጃንደረባውም ከዚህ በኋላ አላየውም፤ ሆኖም ደስ እያለው ጕዞውን ቀጠለ።

ሐዋርያት ሥራ 8:26-39 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የጌታም መልአክ ፊልጶስን፦ “ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ” አለው። ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ ሲመለስም በሰረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር። መንፈስም ፊልጶስን፦ “ወደዚህ ሰረገላ ቅረብና ተገናኝ” አለው። ፊልጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና፦ “በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” አለው። እርሱም፦ “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?” አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው። ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፤ እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፥ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ፤ ሕይወቱ ከምድር ተወግዳለችና ትውልዱንስ ማን ይናገራል? ጃንደረባውም ለፊልጶስ መልሶ፦ “እባክህ፥ ነቢዩ ይህን ስለ ማን ይናገራል? ስለ ራሱ ነውን ወይስ ስለ ሌላ?” አለው። ፊልጶስም አፉን ከፈተ፥ ከዚህም መጽሐፍ ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌልን ሰበከለት። በመንገድም ሲሄዱ ወደ ውኃ ደረሱ፤ ጃንደረባውም፦ “እነሆ ውኃ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድር ነው?” አለው። ፊልጶስም፦ “በፍጹም ልብህ ብታምን፥ ተፈቅዶአል” አለው። መልሶም፦ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ” አለ። ሰረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ፥ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ፥ አጠመቀውም። ከውኃውም ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ነጠቀው፤ ጃንደረባውም ሁለተኛ አላየውም፥ ደስ ብሎት መንገዱን ይሄድ ነበርና።

ሐዋርያት ሥራ 8:26-39 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የጌታ መልአክ ፊልጶስን፥ “ተነሥና ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ወደ ደቡብ ሂድ” አለው፤ ያ መንገድ የበረሓ መንገድ ነበር። እርሱም ተነሥቶ ሄደ፤ እነሆ፥ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ለእግዚአብሔር ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤ ይህ ሰው ሕንደኬ ለተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሟልና የገንዘብዋ ሁሉ ኀላፊ ነበረ። እርሱ ወደ አገሩ ሲመለስ በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር። በዚህ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን “ሂድ ወደዚያ ሠረገላ ቅረብና ተገናኘው” አለው። ስለዚህ ፊልጶስ ወደዚያ ሮጦ ሄደና ኢትዮጵያዊው የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰምቶ “የምታነበው ትርጒሙ ይገባሃልን?” አለው። ኢትዮጵያዊውም “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት ሊገባኝ ይችላል?” አለና ፊልጶስን “ወደ ሠረገላው ውጣና ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለው። እርሱም ያነበው የነበረው የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል የሚከተለው ነበረ፦ “እርሱ ለመታረድ እንደሚነዳ በግ ነበረ፤ ሲሸልቱትም ዝም እንደሚል ጠቦት፤ እርሱም ለመናገር አፉን አልከፈተም። እርሱ ተዋረደ፤ ቅን ፍርድም አልተሰጠውም፤ ሕይወቱም ከምድር ተወግዶአልና ስለ ትውልዱ ማን ሊናገር ይችላል?” ጃንደረባውም ፊልጶስን፥ “ነቢዩ ይህን የተናገረው ስለ ማን ነው? ስለ ራሱ ነውን ወይስ ስለሌላ? እባክህን ንገረኝ” አለው። ፊልጶስም ከዚህ የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል ጀምሮ ስለ ኢየሱስ መልካሙን ዜና አበሠረው። ሲሄዱም ውሃ ወዳለበት ቦታ ደረሱ፤ ጃንደረባውም “እነሆ፥ እዚህ ውሃ አለ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ነገር ምንድን ነው?” አለ። [ ፊልጶስም “በሙሉ ልብህ ካመንክ መጠመቅ ትችላለህ” አለው። ጃንደረባውም “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምናለሁ” አለ።] ጃንደረባው ሠረገላው እንዲቆም አዘዘ፤ ሁለቱም ወደ ውሃው ወረዱና ፊልጶስ ጃንደረባውን አጠመቀው። ከውሃው ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ወሰደው፤ ጃንደረባውም ዳግመኛ አላየውም፤ ይሁን እንጂ ደስ እያለው ጒዞውን ቀጠለ።

ሐዋርያት ሥራ 8:26-39 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የጌታም መልአክ ፊልጶስን “ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ፤” አለው። ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ሕንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሥልጣን የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ ኀላፊ አንድ ኢትዮጵያ ጃንደረባ ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ ሲመለስም በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር። መንፈስም ፊልጶስን “ወደዚህ ሠረገላ ቅረብና ተገናኝ፤” አለው። ፊልጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና “በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” አለው። እርሱም “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?” አለው። ወጥቶም ከእርሱ ጋር ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው። ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ፤ ሕይወቱ ከምድር ተወግዳለችና ትውልዱንስ ማን ይናገራል?” ጃንደረባውም ለፊልጶስ መልሶ “እባክህ፥ ነቢዩ ይህን ስለ ማን ይናገራል? ስለ ራሱ ነውን ወይስ ስለ ሌላ?” አለው። ፊልጶስም አፉን ከፈተ፤ ከዚህም መጽሐፍ ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌልን ሰበከለት። በመንገድም ሲሄዱ ወደ ውሃ ደረሱ፤ ጃንደረባውም “እነሆ ውሃ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድነው?” አለው። ፊልጶስም “በፍጹም ልብህ ብታምን፥ ተፈቅዶአል፤” አለው። መልሶም “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ፤” አለ። ሠረገላውም ይቆም ዘንድ አዘዘ፤ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውሃ ወረዱ፤ አጠመቀውም። ከውሃውም ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ነጠቀው፤ ጃንደረባውም ሁለተኛ አላየውም፤ ደስ ብሎት መንገዱን ይሄድ ነበርና።