የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሐዋርያት ሥራ 12:5-9

ሐዋርያት ሥራ 12:5-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ጴጥ​ሮ​ስ​ንም በወ​ኅኒ ቤት ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ዘወ​ትር ስለ እርሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልዩ ነበር። ሄሮ​ድ​ስም ማለዳ ያቀ​ር​በው ዘንድ በወ​ደ​ደ​ባት በዚ​ያች ሌሊት ጴጥ​ሮስ ሁለ​ቱን እጆ​ቹን በሰ​ን​ሰ​ለት ታስሮ በሁ​ለት ወታ​ደ​ሮች መካ​ከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ችም የወ​ኅኒ ቤቱን በር ይጠ​ብቁ ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ወርዶ በአ​ጠ​ገቡ ቆመ፤ በቤ​ትም ውስጥ ብር​ሃን ሆነ፤ ጴጥ​ሮ​ስ​ንም ጎኑን ነክቶ ቀሰ​ቀ​ሰ​ውና፥ “ፈጥ​ነህ ተነሥ” አለው፥ ሰን​ሰ​ለ​ቶ​ቹም ከእ​ጆቹ ወል​ቀው ወደቁ። መል​አ​ኩም፥ “ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፥ ጫማ​ህ​ንም ተጫማ” አለው፤ እንደ አዘ​ዘ​ውም አደ​ረገ፤ “ልብ​ስ​ህ​ንም ልበ​ስና ተከ​ተ​ለኝ” አለው። ተከ​ት​ሎ​ትም ወጣ፤ ጴጥ​ሮስ ግን ራእይ የሚ​ያይ ይመ​ስ​ለው ነበረ እንጂ በመ​ል​አኩ የሚ​ደ​ረ​ገው ነገር እው​ነት እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀም ነበር።