የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2 ሳሙኤል 3:1-21

2 ሳሙኤል 3:1-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በሳ​ኦል ቤትና በዳ​ዊት ቤት መካ​ከል ለብዙ ጊዜ ጦር​ነት ሆነ፤ የዳ​ዊት ቤት እየ​በ​ረታ፥ የሳ​ኦል ቤት ግን እየ​ደ​ከመ የሚ​ሄድ ሆነ። ለዳ​ዊ​ትም ወን​ዶች ልጆች በኬ​ብ​ሮን ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በኵ​ሩም ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ ከአ​ኪ​ና​ሆም የተ​ወ​ለ​ደው አም​ኖን ነበረ። ሁለ​ተ​ኛ​ውም ከቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊቱ ከአ​ቤ​ግያ የተ​ወ​ለ​ደው ዶሎ​ሕያ ነበረ። ሦስ​ተ​ኛ​ውም ከጌ​ድ​ሶር ንጉሥ ከቶ​ል​ሜ​ልም ልጅ ከመ​ዓክ የተ​ወ​ለ​ደው አቤ​ሴ​ሎም ነበረ። አራ​ተ​ኛ​ውም የአ​ጊት ልጅ አዶ​ን​ያስ፥ አም​ስ​ተ​ኛ​ውም የአ​ቢ​ጣል ልጅ ሰፋ​ጥያ ነበረ። ስድ​ስ​ተ​ኛ​ውም የዳ​ዊት ሚስት የዒ​ገል ልጅ ይት​ረ​ኃም ነበረ። ለዳ​ዊት በኬ​ብ​ሮን የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት እነ​ዚህ ነበሩ። በሳ​ኦል ቤትና በዳ​ዊት ቤት መካ​ከል ጦር​ነት ሆኖ ሳለ አበ​ኔር የሳ​ኦ​ልን ቤት ያበ​ረታ ነበር። ለሳ​ኦ​ልም የኢ​ዮ​ሄል ልጅ ሩጻፋ የተ​ባ​ለች ዕቅ​ብት ነበ​ረ​ችው፤ ኢያ​ቡ​ስ​ቴም አበ​ኔ​ርን፥ “ወደ አባቴ ዕቅ​ብት ለምን ገባህ?” አለው። አበ​ኔ​ርም ኢያ​ቡ​ስቴ እን​ዲህ ስላ​ለው እጅግ ተቈጣ፤ አበ​ኔ​ርም እን​ዲህ አለው፥ “በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝን? እኔ ለአ​ባ​ትህ ለሳ​ኦል ቤት ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ ለዘ​መ​ዶ​ቹም ቸር​ነት አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ አን​ተ​ንም ለዳ​ዊት እጅ አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጠ​ሁ​ህም፤ አን​ተም ዛሬ ከዚ​ህች ሴት ጋር ስለ ሠራ​ሁት ኀጢ​አት ትከ​ስ​ሰ​ኛ​ለህ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዳ​ዊት እንደ ማለ​ለት እን​ዲሁ ከእ​ርሱ ጋር ዛሬ ባላ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​በ​ኔር ይህን ያድ​ር​ግ​በት፤ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​በት። የዳ​ዊ​ት​ንም ዙፋን በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ መን​ግ​ሥ​ትን ከሳ​ኦል ቤት ወሰ​ዳት።” ኢያ​ቡ​ስ​ቴም አበ​ኔ​ርን ይፈ​ራው ነበ​ርና ቃልን ይመ​ል​ስ​ለት ዘንድ አል​ቻ​ለም። አበ​ኔ​ርም ለዳ​ዊት፥ “ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርግ፤ እጄም ከአ​ንተ ጋር ትሆ​ና​ለች፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ ወደ አንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ” ብለው በስሙ ይነ​ግ​ሩት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ወዲ​ያ​ውኑ ላከ​ለት። ዳዊ​ትም፥ “ይሁን፤ በመ​ል​ካም ፈቃ​ደ​ኛ​ነት ከአ​ንተ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር ከአ​ንተ እሻ​ለሁ፤ ፊቴን ለማ​የት በመ​ጣህ ጊዜ፥ የሳ​ኦ​ልን ልጅ ሜል​ኮ​ልን ካላ​መ​ጣ​ህ​ልኝ ፊቴን አታ​ይም” አለው። ዳዊ​ትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያ​ቡ​ስቴ፥ “በመቶ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሸለ​ፈት ያጨ​ኋ​ትን ሚስ​ቴን ሜል​ኮ​ልን መል​ስ​ልኝ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ። ኢያ​ቡ​ስ​ቴም ልኮ ከሴ​ሊስ ልጅ ከባ​ልዋ ከፈ​ላ​ጥ​ያል ወሰ​ዳት። ባል​ዋም እያ​ለ​ቀሰ ከእ​ር​ስዋ ጋር ሄደ፤ እስከ ብራ​ቂም ድረስ ተከ​ተ​ላት። አበ​ኔ​ርም፥ “ሂድ፤ ተመ​ለስ” አለው፤ እር​ሱም ተመ​ለሰ። አበ​ኔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “አስ​ቀ​ድሞ ዳዊት በእ​ና​ንተ ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ፈል​ጋ​ችሁ ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ዳዊት፦ በባ​ሪ​ያዬ በዳ​ዊት እጅ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ክፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅና ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ እጅ አድ​ና​ለሁ ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እን​ግ​ዲህ አሁን አድ​ርጉ´ ብሎ ነገ​ራ​ቸው። አበ​ኔ​ርም ደግሞ በብ​ን​ያም ልጆች ጆሮ ተና​ገረ፤ አበ​ኔ​ርም ደግሞ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በብ​ን​ያም ቤት ሁሉ መል​ካም የነ​በ​ረ​ውን ለዳ​ዊት ሊነ​ግ​ረው ወደ ኬብ​ሮን ሄደ። አበ​ኔ​ርም ከሃያ ሰዎች ጋር ወደ ዳዊት ወደ ኬብ​ሮን መጣ፤ ዳዊ​ትም ለአ​በ​ኔ​ርና ከእ​ርሱ ጋር ለነ​በ​ሩት ሰዎች ግብዣ አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው። አበ​ኔ​ርም ዳዊ​ትን፥ “ተነ​ሥቼ ልሂድ፤ ካንተ ጋርም ቃል ኪዳን እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ፥ ነፍ​ስ​ህም እንደ ወደ​ደች ሁሉን እን​ድ​ት​ገዛ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ ልሰ​ብ​ስብ” አለው። ዳዊ​ትም አበ​ኔ​ርን አሰ​ና​በ​ተው፤ በሰ​ላ​ምም ሄደ።

2 ሳሙኤል 3:1-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል የነበረው ጦርነት ብዙ ጊዜ ቈየ፤ ዳዊት እየበረታ ሲሄድ፣ የሳኦል ቤት ግን እየተዳከመ መጣ። ዳዊት በኬብሮን ሳለ፣ ስድስት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ የበኵር ልጁ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን፣ ሁለተኛው፣ የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢግያ የተወለደው ኪልአብ፣ ሦስተኛው፣ ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣ አራተኛው፣ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፤ ዐምስተኛው፣ ከአቢጣል የተወለደው ሰፋጥያ፣ ስድስተኛው፣ ከዳዊት ሚስት ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም ነበር። እነዚህ ዳዊት በኬብሮን ሳለ የተወለዱለት ናቸው። የሳኦል ቤትና የዳዊት ቤት በጦርነት ላይ በነበሩበት ጊዜ፣ አበኔር በሳኦል ቤት ላይ ኀይሉን ያጠናክር ነበር። ሳኦልም የኢዮሄልን ልጅ ሪጽፋን በቁባትነት አስቀምጧት ነበር፤ ኢያቡስቴም አበኔርን፣ “ለምንድን ነው ከአባቴ ቁባት ጋራ የተኛኸው?” አለው። አበኔርም በኢያቡስቴ ንግግር እጅግ ስለ ተቈጣ እንዲህ አለ፤ “እኔ ለይሁዳ የምወግን የውሻ ጭንቅላት ነኝን? ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹና ለዘመዶቹ ታማኝነቴን እስከ ዛሬ ድረስ አላጓደልሁም፤ አንተንም አሳልፌ ለዳዊት አልሰጠሁም፤ አሁን ግን አንተ ከዚህች ሴት ጋራ በፈጸምሁት ነገር ትከሰኛለህን? እግዚአብሔር ለዳዊት በመሐላ የሰጠውን ተስፋ እዳር እንዲደርስ ሳላደርግ ብቀር እግዚአብሔር በአበኔር ላይ ክፉ ያድርግበት፤ ከዚያ የባሰም ያምጣበት፤ የማለለትም መንግሥትን ከሳኦል ቤት አውጥቶ፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ባለው በእስራኤልና በይሁዳ ምድር ላይ የዳዊትን ዙፋን ለመመሥረት የሰጠው ተስፋ ነው።” ኢያቡስቴም አበኔርን አጥብቆ ፈርቶት ስለ ነበር፣ እንደ ገና አንዲት ቃል እንኳ ሊመልስለት አልደፈረም። ከዚያም አበኔር ለዳዊት፣ “ምድሪቱ የማን ናት? ከእኔ ጋራ ተስማማ፤ እነሆ እስራኤል ሁሉ ወደ አንተ እንዲመለስ እኔ እረዳሃለሁ” ብለው ለዳዊት እንዲነግሩለት መልክተኞች ላከ። ዳዊትም፣ “ይሁን ዕሺ፣ ከአንተ ጋራ ስምምነቱን አደርጋለሁ፤ ነገር ግን ከአንተ አንዲት ነገር እሻለሁ፤ ይኸውም ወደ እኔ ስትመጣ በመጀመሪያ የሳኦልን ሴት ልጅ ሜልኮልን ይዘህልኝ እንድትመጣ ነው፤ አለዚያ ግን ወደ እኔ እንዳትመጣ” አለ። ከዚያም ዳዊት፣ “የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ የከፈልሁባትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብሎ ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ መልክተኞች ላከበት። ስለዚህም ኢያቡስቴ መልክተኛ ልኮ፣ ሜልኮልን ከባሏ ከሌሳ ልጅ ከፈልጢኤል ወሰዳት። ባሏም እስከ ባሑሪም ከተማ ድረስ እያለቀሰ ተከትሏት ሄደ፤ ከዚያም አበኔር፣ “በል ይበቃል! ወደ ቤትህ ተመለስ” አለው። ስለዚህም ተመለሰ። አበኔር ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋራ ተመካከረ፤ እንዲህም አለ፤ “ባለፈው ጊዜ ዳዊት በላያችሁ እንዲነግሥ ፈልጋችሁ ነበር፤ እግዚአብሔር ለዳዊት፣ ‘በባሪያዬ በዳዊት ሕዝቤን እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅና ከጠላቶቻቸው እጅ እታደጋቸዋለሁ’ ብሎ ተስፋ ስለ ሰጠው፣ ይህን አሁኑኑ አድርጉት።” እንዲሁም አበኔር ለብንያማውያን ራሱ ሄዶ ይህንኑ ነገራቸው፤ ከዚያም እስራኤልና መላው የብንያም ቤት ለማድረግ የፈለጉትን ሁሉ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ። አበኔር ከሃያ ሰዎች ጋራ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጣ፤ ዳዊትም ለአበኔርና ዐብረውት ለነበሩት ሰዎች ግብዣ አደረገላቸው። ከዚያም አበኔር ዳዊትን፤ “ከአንተ ጋራ ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፣ ልብህ እንደተመኘውም ሁሉን እንድትገዛ ፈጥኜ ሄጄ፣ ለጌታዬ ለንጉሡ መላውን እስራኤልን ልሰብስብ” አለው። ስለዚህ ዳዊት አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።

2 ሳሙኤል 3:1-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ብዙ ዘመን ጦርነት ሆነ፥ የዳዊት ቤት እየበረታ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ የሚሄድ ሆነ። ለዳዊትም ወንድ ልጆች በኬብሮን ተወለዱለት፥ በኩሩም ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን ነበረ። ሁለተኛውም የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረች ከአቢግያ የተወለደው ዶሎሕያ ነበረ። ሦስተኛውም ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም ነበረ። አራተኛውም የአጊት ልጅ አዶንያስ፥ አምስተኛውም የአቢጣል ልጅ ሰፋጥያስ ነበረ። ስድስተኛውም የዳዊት ልጅ ሚስት የዔግላ ልጅ ይትረኃም ነበረ። እነዚህም ለዳዊት በኬብሮን ተወለዱለት። በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ጦርነት ሆኖ ሳለ አበኔር በሳኦል ቤት ይበረታ ነበር። ለሳኦልም የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ የተባለች ቁባት ነበረችው፥ ኢያቡስቴም አበኔርን፦ ወደ አባቴ ቁባት ለምን ገባህ? አለው። አበኔርም በኢያቡስቴ ቃል እጅግ ተቆጥቶ እንዲህ አለ፦ እኔ ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹም ለዘመዶቹም ቸርነት አድርጌአለሁ፥ አንተንም ለዳዊት እጅ አሳልፌ አልሰጠሁም፥ አንተም ዛሬ ከዚህች ሴት ጋር ስለ ሠራሁት ኃጢአት ትከስሰኛለህ፥ በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝን? መንግሥትን ከሳኦል ቤት ያወጣ ዘንድ የዳዊትንም ዙፋን በእስራኤልና በይሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረው ከፍ ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር ለዳዊት እንደ ማለለት እንዲሁ ከእርሱ ጋር ባላደርግ እግዚአብሔር በአበኔር ይህን ያድርግበት ይህንም ይጨምርበት። ኢያቡስቴም አበኔርን ይፈራው ነበርና አንዳች ይመልስለት ዘንድ አልቻለም። አበኔርም ለዳዊት፦ ምድሪቱ ለማን ናት? ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፥ እጄም ከአንተ ጋር ትሆናለች፥ እስራኤልንም ሁሉ ወደ አንተ እመልሰዋለሁ ብለው ይነግሩት ዘንድ መልእክተኞች ሰደደለት። ዳዊትም፦ ይሁን፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፥ ነገር ግን አንድ ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ፊቴን ለማየት በመጣህ ጊዜ፥ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ካላመጣህልኝ ፊቴን አታይም አለ። ዳዊትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ፦ በመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ያጨኋትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ ብሎ መልእክተኞችን ሰደደ። ኢያቡስቴም ልኮ ከሌሳ ልጅ ከባልዋ ከፈልጢኤል ወሰዳት። ባልዋም እያለቀሰ ከእርስዋ ጋር ሄደ፥ እስከ ብራቂም ድረስ ተከተላት። አበኔርም፦ ሂድ፥ ተመለስ አለው፥ እርሱም ተመለሰ። አበኔርም ለእስራኤል ሽማግሌዎች፦ አስቀድሞ ዳዊት በእናንተ ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ፈልጋችሁ ነበር። እግዚአብሔርም ስለ ዳዊት፦ በባሪያዬ በዳዊት እጅ ሕዝቤን እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅና ከጠላቶቻቸው ሁሉ እጅ አድናለሁ ብሎ ተናግሮአልና እንግዲህ አሁን አድርጉ ብሎ ነገራቸው። አበኔርም ደግሞ በብንያም ወገን ጆሮ ተናገረ፥ አበኔርም ደግሞ በእስራኤልና በብንያም ቤት ሁሉ መልካም የነበረውን ለዳዊት ሊነግረው ወደ ኬብሮን ሄደ። አበኔርም ከሀያ ሰዎች ጋር ወደ ዳዊት ወደ ኬብሮን መጣ። ዳዊትም ለአበኔርና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሰዎች ግብዣ አደረገላቸው። አበኔርም ዳዊትን፦ ተነሥቼ ልሂድ፥ ከአንተ ጋርም ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፥ ነፍስህም እንደ ወደደች ሁሉን እንድትገዛ እስራኤልን ሁሉ ለጌታዬ ለንጉሥ ልሰብስብ አለው። ዳዊትም አበኔርን አሰናበተው፥ በደኅናም ሄደ።

2 ሳሙኤል 3:1-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በዚህ ዐይነት በሳኦል ቤተሰብና በዳዊት ቤተሰብ መካከል የሚካሄደው ጦርነት ለረጅም ጊዜ ቈየ፤ ሆኖም ዳዊት እየበረታ ሲሄድ የሳኦል ቤተሰብ እየተዳከመ ሄደ። ዳዊት በኬብሮን ሳለ ስድስት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም በኲሩ የኢይዝራኤል ተወላጅ ከሆነችው ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥ ሁለተኛው የቀርሜሎስ ተወላጅ የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢጌል የተወለደው ኪልአብ፥ ሦስተኛው ታልማይ ተብሎ የሚጠራው የገሹር ንጉሥ ልጅ ከሆነችው ከማዕካ የተወለደው አቤሴሎም፥ አራተኛው ከሐጊት የተወለደው አዶኒያ፥ አምስተኛው ከአቢጣል የተወለደው ሸፋጥያ፥ ስድስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ዩትረዓም፥ እነዚህ ሁሉ በኬብሮን የተወለዱ ናቸው። በሳኦል ቤተሰብና በዳዊት ቤተሰብ መካከል ጦርነቱ እየቀጠለ በሄደ መጠን አበኔር በሳኦል ቤተሰብ እየበረታ ሄደ። ሳኦል የአያ ልጅ የሆነች ሪጽፋ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ ኢያቡስቴ አበኔርን “ለምን ከአባቴ ቁባት ጋር ተገናኘህ” አለው። የኢያቡስቴ ቃል አበኔርን በጣም አስቈጣው፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ ወደ ይሁዳ ነገድ የዞርኩ የማልጠቅም ውሻ ነኝን? እኔ ለአባትህ ቤት፥ ለወንድሞቹና ለወዳጆቹ ታማኝነትን አሳይቼአለሁ፤ አንተንም ለዳዊት አሳልፌ አልሰጠሁህም፤ ታዲያ፥ አንተ ስለዚህች ሴት ትወቅሰኛለህን? እግዚአብሔር መንግሥትን ከሳኦል ቤት ወሰደ የዳዊትን ዙፋን በእስራኤልና በይሁዳ ላይ ከሰሜን ከዳን ጀምሮ እስከ ደቡብ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ለመዘርጋት በመሐላ ቃል በገባለት መሠረት ባላስፈጽም በእኔ ላይ እግዚአብሔር ይፍረድ!” ኢያቡስቴም እጅግ ፈርቶ ስለ ነበር፥ ለአበኔር አንድ ቃል እንኳ ሊመልስለት አልቻለም። አበኔር በዚያን ጊዜ በኬብሮን ወደነበረው ወደ ዳዊት መልእክተኞች ልኮ “የዚህች ምድር ገዢ የሚሆን ማነው? እንግዲህ ከእኔ ጋር ስምምነት አድርግ፤ እኔም መላው እስራኤል በአንተ ቊጥጥር ሥር እንዲሆን ለማድረግ እረዳሃለሁ” አለው። ዳዊትም “መልካም ነው! ከአንተ ጋር ስምምነት አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንተ በቅድሚያ የምትፈጽምልኝ ነገር አለ፤ ይኸውም ወደ እኔ በምትመጣበት ጊዜ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ይዘህ ካልመጣህ መገናኘት አንችልም” አለው። እንዲሁም ዳዊት ወደ ኢያቡስቴ መልእክተኞች ልኮ እንዲህ አለው፤ “ሚስቴን ሜልኮልን መልስልኝ፤ እኔ እርስዋን ለማግባት የአንድ መቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ ጥያለሁ” አለው። ስለዚህም ኢያቡስቴ መልእክተኛ በመላክ ሜልኮል የላዊሽ ልጅ ከሆነው ከባልዋ ከፓልጢኤል ልጅ አስወሰዳት፤ ባልዋ ፓልጢኤልም እያለቀሰ እስከ ባሑሪም ከተማ ድረስ ተከተላት፤ ነገር ግን አበኔር “ወደ ቤትህ ተመለስ” ባለው ጊዜ ተመለሰ። አበኔር ወደ እስራኤል መሪዎች ሄዶ እንዲህ አላቸው፤ “ዳዊት የእናንተ ንጉሥ እንዲሆን ለብዙ ጊዜ ተመኝታችሁ ነበር፤ እነሆ፥ አሁን አድርጉ፤ ደግሞም እግዚአብሔር ‘በአገልጋዬ በዳዊት አማካይነት ሕዝቤን እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያንና ከሌሎቹም ጠላቶቻቸው እጅ በመታደግ አድናለሁ’ ሲል ተናግሮ እንደ ነበር አስታውሱ።” አበኔር ለብንያም ነገድ ሕዝብም ይህንኑ ተናገረ፤ ከዚያም በኋላ የብንያምና የእስራኤል ሕዝብ ለማድረግ የተስማሙበትን ጉዳይ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ። አበኔር ኻያ ሰዎችን አስከትሎ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን በመጣ ጊዜ ዳዊት ግብዣ አደረገላቸው፤ አበኔርም ዳዊትን “ከአንተ ጋር እንዲነጋገሩና እንዲዋዋሉ አንተም ልብህ በተመኘው ሁሉ ላይ እንድትነግሥ ለማድረግ ወደ እስራኤላውያን ልሂድ” አለው። በዚህም ዐይነት ዳዊት አበኔርን በሰላም አሰናበተው።

2 ሳሙኤል 3:1-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል የነበረው ጦርነት ለረጅም ጊዜ ቆየ፤ ሆኖም ዳዊት እያየለ ሲሄድ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ ነበር። ዳዊት በኬብሮን እያለ፥ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ የበኲር ልጁ፥ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥ ሁለተኛው፥ የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢጌል የተወለደው ኪልአብ፥ ሦስተኛው፥ ተልማይ ከተባለው ከገሹር ንጉሥ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፥ አራተኛው፥ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፤ አምስተኛው፥ ከአቢጣል የተወለደው ሸፋጥያ፥ ስድስተኛው፥ ከዳዊት ሚስት ከዔግላ የተወለደው ይትረዓም ነበር፤ እነዚህ ዳዊት በኬብሮን እያለ የተወለዱለት ናቸው። የሳኦል ቤትና የዳዊት ቤት በጦርነት ላይ በነበሩበት ጊዜ፥ አበኔር በሳኦል ቤት ሆኖ ኀይሉን ያጠናክር ነበር። ሳኦልም ሪጽፋን የምትባለውን የአያን ልጅ በዕቁባትነት አስቀምጦአት ነበር፤ ኢያቡስቴም አበኔርን፥ “ለምንድን ነው ከአባቴ ዕቁባት ጋር የተኛኸው?” አለው። ይህ የአበኔር ንግግር እጅግ ያስቆጣው ኢያቡስቴ እንዲህ አለ፤ “እኔ ለአባትህ ለሳኦል ቤት፥ ለወንድሞቹና ለዘመዶቹ፥ ታማኝነቴን ሳላጎድል ይሄው አለሁ፤ አንተንም ለዳዊት እጅ አሳልፌ አልሰጠሁም፥ ዛሬ ግን አንተ በዚህች ሴት ትከሰኛለህን? በውኑ እኔ የውሻ ራስ ነኝ? ጌታ ለዳዊት በመሐላ የሰጠውን ተስፋ ከፍጻሜ ሳላደርስ ብቀር እግዚአብሔር በአበኔር ላይ ይፍረድ፤ ከዚያ የባሰም ያምጣበት፤ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ባለው በእስራኤልና በይሁዳ ምድር ላይ የዳዊትን ዙፋን ለመመሥረት መንግሥትን ከሳኦል ቤት እንደሚወስድ ተስፋ ተሰጥቶታልና።” ኢያቡስቴም አበኔርን ስለ ፈራ ሌላ ቃል ሊመልስለት አልደፈረም። ከዚያም አበኔር ለዳዊት እንዲህ ሲሉ ለዳዊት እንዲነግሩት መልክተኞች ላከ፥ “ምድሪቱ የማን ናት? ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፥ እጄም ከአንተ ጋር ትሆናለች፥ እስራኤልንም ሁሉ ወደ አንተ እመልሰዋለሁ።” ዳዊትም፥ “ይሁን፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፥ ነገር ግን አንድ ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ፊቴን ለማየት በመጣህ ጊዜ፥ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ካላመጣህልኝ ፊቴን አታይም” አለ። ከዚያም ዳዊት፥ “የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ የከፈልሁባትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብሎ ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ መልክተኞች ላከበት። ኢያቡስቴም መልክተኛ ልኮ፥ ሜልኮልን ከባሏ ከላይሽ ልጅ ከፓልጢኤል ወሰዳት። ባሏም እስከ ባሑሪም ከተማ ድረስ እያለቀሰ ተከትሎአት ሄደ፤ ከዚያም አበኔር፥ “ሂድ፥ ተመለስ” አለው፤ እርሱም ተመለሰ። አበኔር ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር እንዲህ ሲል ተመካከረ፥ “ቀደም ሲል ዳዊት ንጉሣችሁ እንዲሆን ፈልጋችሁ ነበር፤ ስለዚህ ጌታ ለዳዊት፥ ‘በአገልጋዬ በዳዊት ሕዝቤን እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅና ከጠላቶቻቸው ሁሉ እጅ እታደጋቸዋለሁ’ ብሎ ተስፋ ስለ ሰጠው፥ ይህን አሁን አድርጉ።” እንዲሁም አበኔር ሄዶ ይህንኑ ለብንያማውያን ነገራቸው፤ ከዚያም እስራኤልና መላው የብንያም ቤት ለማድረግ የፈለጉትን ሁሉ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ። አበኔር ከሃያ ሰዎች ጋር ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን በመጣ ጊዜ፤ ዳዊት ለአበኔርና አብረውት ለነበሩት ሰዎች ግብዣ አደረገላቸው። ከዚያም አበኔር ዳዊትን፥ “ለጌታዬ ለንጉሡ መላውን እስራኤልን ልሰብስብ፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፥ ልብህ እንደተመኘውም ሁሉን እንድትገዛ ፈጥኜ ልሂድ” አለው። ስለዚህ ዳዊት አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።