የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2 ነገሥት 1:1-8

2 ነገሥት 1:1-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አክዓብ ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእስራኤል ላይ ዐመፀ። በዚህ ጊዜ አካዝያስ በሰማርያ ካለው እልፍኝ ሰገነቱ ላይ ሳለ፣ ከዐይነ ርግቡ ሾልኮ ወድቆ ነበርና ታመመ፤ ስለዚህ፣ “ሄዳችሁ ከዚህ ሕመም እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ” ሲል መልእክተኞች ላከ። የእግዚአብሔር መልአክ ግን ቴስብያዊውን ኤልያስን እንዲህ አለው፤ “ተነሥተህ የሰማርያን ንጉሥ መልእክተኞች ለመገናኘት ውጣና፣ ‘የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ የምትሄዱ በእስራኤል አምላክ ስለሌለ ነውን?’ ብለህ ጠይቃቸው። ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከተኛህበት ዐልጋ አትነሣም፤ በርግጥ ትሞታለህ።’ ” ከዚያም ኤልያስ ሄደ። መልእክተኞቹ ወደ ንጉሡ ሲመለሱ እርሱም፣ “ለምን ተመልሳችሁ መጣችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “አንድ ሰው ሊገናኘን መጥቶ፣ ‘ወደ ላካችሁ ንጉሥ ተመልሳችሁ ሂዱና፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ ሰዎች የምትልከው በእስራኤል አምላክ ስለሌለ ነውን? ስለዚህ ከተኛህበት ዐልጋ አትነሣም፤ በርግጥ ትሞታለህ።” ’ ” ንጉሡም፣ “ለመሆኑ ሊገናኛችሁ መጥቶ እንዲህ ያላችሁ ሰው እንዴት ያለ ነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “ሰውየው ጠጕራም፣ በወገቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር” አሉት። ንጉሡም፣ “ዐወቅሁት፤ ቴስብያዊው ኤልያስ ነው” አላቸው።

2 ነገሥት 1:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አክ​ዓ​ብም ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዐመፀ። አካ​ዝ​ያ​ስም በሰ​ማ​ርያ በሰ​ገ​ነቱ ላይ ሳለ በዐ​ይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እር​ሱም፥ “ሂዱ፥ ከዚህ ደዌ እድን እንደ ሆነ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ጠይቁ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊጠ​ይ​ቁ​ለት ሄዱ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ቴስ​ብ​ያ​ዊ​ውን ኤል​ያ​ስን ጠርቶ፥ “ተነሣ፤ የሰ​ማ​ር​ያን ንጉሥ መል​እ​ክ​ተ​ኞች ለመ​ገ​ና​ኘት ሂድና፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቁ ዘንድ የም​ት​ሄ​ዱት በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም በላ​ቸው” አለው። ኤል​ያ​ስም ሄደ፤ እን​ዲ​ሁም ነገ​ራ​ቸው። መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹም ወደ አካ​ዝ​ያስ ተመ​ለሱ፤ እር​ሱም፥ “ለምን ተመ​ለ​ሳ​ችሁ?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “አንድ ሰው ሊገ​ና​ኘን መጣና፦ ሂዱ፤ ወደ ላካ​ችሁ ንጉሥ ተመ​ል​ሳ​ችሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ የላ​ክህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? ስለ​ዚህ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም በሉት አለን” አሉት። እር​ሱም፥ “ሊገ​ና​ኛ​ችሁ የወ​ጣው፦ ይህ​ንስ ቃል የነ​ገ​ራ​ችሁ ሰው መልኩ ምን ይመ​ስ​ላል?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ሰው​ዬው ጠጕ​ራም ነው፤ በወ​ገ​ቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር” አሉት። እር​ሱም፥ “ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ ነው” አላ​ቸው።

2 ነገሥት 1:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አክዓብ ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእስራኤል ላይ ዐመፀ። አካዝያስም በሰማርያ በሰገነቱ ላይ ሳለ ከዐይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እርሱም “ሂዱ፤ ከዚህም ደዌ እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ፤” ብሎ መልእክተኞችን ላከ። የእግዚአብሔርም መልአክ ቴስብያዊውን ኤልያስን “ተነሣ፤ የሰማርያን ንጉሥ መልእክተኞች ለመገናኘት ውጣና ‘የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቁ ዘንድ የምትሄዱት በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን? ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም፤” በላቸው’” አለው። ኤልያስም ሄደ። መልእክተኞችም ወደ አካዝያስ ተመለሱ፤ እርሱም “ለምን ተመለሳችሁ?” አላቸው። እነርሱም “አንድ ሰው ሊገናኘን መጣና ‘ሂዱ፤ ወደ ላካችሁም ንጉሥ ተመልሳችሁ” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቅ ዘንድ የላከህ በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን? ስለዚህ ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም፤” በሉት፤’ አለን፤” አሉት። እርሱም “ሊገናኛችሁ የወጣው፥ ይህንስ ቃል የነገራችሁ ሰው መልኩ ምን ይመስላል?” አላቸው። እነርሱም “ሰውዮው ጠጕራም ነው፤ በወገቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር፤” አሉት። እርሱም “ቴስብያዊው ኤልያስ ነው፤” አለ።

2 ነገሥት 1:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ከሞተ በኋላ ሞአብ በእስራኤል ላይ ዐመፀ። በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ በብርቱ ስለ ቈሰለ ታሞ ነበር፤ እርሱም “እኔ ከዚህ ሕመም እድን ወይም አልድን እንደ ሆነ በፍልስጥኤም የዔክሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡልን ጠይቃችሁልኝ ኑ” ብሎ መልእክተኞቹን ላከ። ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ቴስቢያዊውን ኤልያስን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ተነሥተህ የሰማርያ ንጉሥ አካዝያስ የላካቸውን መልእክተኞች ለመገናኘት ውጣ፤ እንዲህም ብለህ ንገራቸው፤ ‘የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ የምትሄዱት፥ በእስራኤል ዘንድ አምላክ የለም ብላችሁ በማሰብ ነውን?’ ስለዚህም እግዚአብሔር፥ ‘እነሆ አንተ ትሞታለህ እንጂ አትፈወስም! ከተኛህበት አልጋም አትነሣም! ብሎሃል’ በሉት።” ስለዚህ ኤልያስ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ መልእክተኞቹም ወደ ንጉሡ ተመልሰው ሄዱ፤ ንጉሡም “ስለምን ተመልሳችሁ መጣችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “አንድ ሰው በመንገድ አግኝቶን ወደ አንተ ተመልሰን እንድንመጣና እግዚአብሔር ስለ አንተ የተናገረውን እንድናስረዳህ አዘዘን፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፤ ‘የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ መልእክተኞች የላክህበት ምክንያት ምንድን ነው? በእስራኤል ዘንድ አምላክ የለም ብለህ በማሰብህ ነውን? ስለዚህ ትሞታለህ እንጂ ከዚህ ሕመም አትፈወስም! ከተኛህበትም አልጋ አትነሣም!’ ” ንጉሡም “በመንገድ ያገኛችሁትና ይህን ቃል የነገራችሁ ያ ሰው እንዴት ያለ ነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “ጠጒራም ልብስ ለብሶ በወገቡ ዙሪያ የጠፍር ቀበቶ የታጠቀ ነው” ሲሉ መለሱለት። ንጉሡም “እርሱማ ኤልያስ ነው!” አለ።

2 ነገሥት 1:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእስራኤል ላይ ዐመፀ። በዚህም ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ በብርቱ ስለ ቆሰለ ታሞ ነበር፤ እርሱም “እኔ ከዚህ ሕመም እድን ወይም አልድን እንደሆነ በፍልስጥኤም የዔክሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡልን ጠይቃችሁልኝ ኑ” ብሎ መልእክተኞቹን ላከ። ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ቴስቢያዊውን ኤልያስን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ተነሥተህ የሰማርያ ንጉሥ አካዝያስ የላካቸውን መልእክተኞች ለመገናኘት ውጣ፤ እንዲህም ብለህ ንገራቸው፤ ‘የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ የምትሄዱት፥ በእስራኤል ዘንድ አምላክ የለም ብላችሁ በማሰብ ነውን?’ ስለዚህም እግዚአብሔር፥ ‘እነሆ አንተ ትሞታለህ እንጂ አትፈወስም! ከተኛህበት አልጋም አትነሣም! ብሎሃል’ በሉት።” ስለዚህ ኤልያስ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ መልእክተኞቹም ወደ ንጉሡ ተመልሰው ሄዱ፤ ንጉሡም “ስለምን ተመልሳችሁ መጣችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “አንድ ሰው በመንገድ አግኝቶን ወደ አንተ ተመልሰን እንድንመጣና እግዚአብሔር ስለ አንተ የተናገረውን እንድናስረዳህ አዘዘን፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፤ ‘የዔክሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ መልእክተኞች የላክህበት ምክንያት ምንድነው? በእስራኤል ዘንድ አምላክ የለም ብለህ በማሰብህ ነውን? ስለዚህ ትሞታለህ እንጂ ከዚህ ሕመም አትፈወስም! ከተኛህበትም አልጋ አትነሣም!’” ንጉሡም “በመንገድ ያገኛችሁትና ይህን ቃል የነገራችሁ ያ ሰው እንዴት ያለ ነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “ጠጉራም ልብስ ለብሶ በወገቡ ዙሪያ የጠፍር ቀበቶ የታጠቀ ነው” ሲሉ መለሱለት። ንጉሡም “እርሱማ ኤልያስ ነው!” አለ።