የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 1:1-8

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 1:1-8 አማ2000

አክ​ዓ​ብም ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዐመፀ። አካ​ዝ​ያ​ስም በሰ​ማ​ርያ በሰ​ገ​ነቱ ላይ ሳለ በዐ​ይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እር​ሱም፥ “ሂዱ፥ ከዚህ ደዌ እድን እንደ ሆነ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ጠይቁ” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ሊጠ​ይ​ቁ​ለት ሄዱ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ቴስ​ብ​ያ​ዊ​ውን ኤል​ያ​ስን ጠርቶ፥ “ተነሣ፤ የሰ​ማ​ር​ያን ንጉሥ መል​እ​ክ​ተ​ኞች ለመ​ገ​ና​ኘት ሂድና፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቁ ዘንድ የም​ት​ሄ​ዱት በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም በላ​ቸው” አለው። ኤል​ያ​ስም ሄደ፤ እን​ዲ​ሁም ነገ​ራ​ቸው። መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹም ወደ አካ​ዝ​ያስ ተመ​ለሱ፤ እር​ሱም፥ “ለምን ተመ​ለ​ሳ​ችሁ?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “አንድ ሰው ሊገ​ና​ኘን መጣና፦ ሂዱ፤ ወደ ላካ​ችሁ ንጉሥ ተመ​ል​ሳ​ችሁ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የአ​ቃ​ሮ​ንን አም​ላክ ብዔ​ል​ዜ​ቡ​ልን ትጠ​ይቅ ዘንድ የላ​ክህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አም​ላክ ስለ​ሌለ ነውን? ስለ​ዚህ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ ከወ​ጣ​ህ​በት አልጋ አት​ወ​ር​ድም በሉት አለን” አሉት። እር​ሱም፥ “ሊገ​ና​ኛ​ችሁ የወ​ጣው፦ ይህ​ንስ ቃል የነ​ገ​ራ​ችሁ ሰው መልኩ ምን ይመ​ስ​ላል?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ሰው​ዬው ጠጕ​ራም ነው፤ በወ​ገ​ቡም ጠፍር ታጥቆ ነበር” አሉት። እር​ሱም፥ “ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ ነው” አላ​ቸው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}