2 ዜና መዋዕል 36:20-21
2 ዜና መዋዕል 36:20-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የተረፉትንም ወደ ባቢሎን ማረካቸው፤ የሜዶንም ንጉሥ እስኪነግሥ ድረስ ለንጉሡና ለልጆቹ ባሪያዎች ሆኑ፤ በኤርምያስ አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፥ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አገኘች።
2 ዜና መዋዕል 36:20-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከሰይፍ የተረፉትን ቅሬታዎች በምርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ እስከ ፋርስ መንግሥት መነሣትም ድረስ የእርሱና የልጆቹ አገልጋዮች ሆኑ። ምድሪቱም የሰንበት ዕረፍት አገኘች፤ በኤርምያስ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ሰባው ዓመት እስኪያበቃ ድረስ፣ ባድማ በነበረችበት ዘመን ሁሉ ዐረፈች።
2 ዜና መዋዕል 36:20-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከሰይፍም ያመለጡትን ወደ ባቢሎን ማረካቸው፤ የፋርስ ንጉሥም እስኪነግሥ ድረስ ለንጉሡና ለልጆቹ ባሪያዎች ሆኑ፤ በኤርምያስ አፍ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፥ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ሰንበትን አገኘች።
2 ዜና መዋዕል 36:20-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በሰይፍ ከመገደል የተረፉትንም ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ እነርሱም የፋርስ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት እስከ ተነሣበት ጊዜ ድረስ፥ በዚያው በባቢሎን ባሪያዎች ሆነው፥ ንጉሥ ናቡከደነፆርንና የእርሱን ዘሮች ያገለግሉ ነበር። በዚህ ዐይነት አስቀድሞ እግዚአብሔር በነቢዩ ኤርምያስ አማካይነት፥ “ሕዝቡ ሰንበቶችን ባላከበሩበት ልክ ምድሪቱ ለሰባ ዓመት ባድማ ሆና ስለምትቀር፥ የሰንበት ዕረፍት ታገኛለች” ሲል የተናገረው የትንቢት ቃል ተፈጸመ።