2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 36
36
ኢዮአክስ መንገሡ
1የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን ወስደው በአባቱ ፋንታ በኢየሩሳሌም አነገሡት። 2ኢዮአክስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ ሦስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ። 3የግብጽም ንጉሥ ከኢየሩሳሌም ከመንግሥቱ አወረደው፥ በምድሪቱም በሚኖሩት ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለባቸው። 4#ኤር. 22፥11፤12።የግብጽም ንጉሥ ወንድሙን ኤልያቄምን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ፥ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው፤ ኒካዑም ወንድሙን ኢዮአክስን ይዞ ወደ ግብጽ ወሰደው።
ኢዮአቄም መንገሡና መማረኩ
5 #
ኤር. 22፥18፤19፤ 33፥1-6፤ 42፥1-19። ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ። 6#ኤር. 25፥1-38፤ 51፥31-35፤ ዳን. 1፥1፤2።የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደናፆር በኢዮአቄም ላይ መጣበት፤ እርሱንም ወደ ባቢሎን ለመውሰድ በሰንሰለት አሰረው። 7ናቡከደናፆርም ከጌታ ቤት ዕቃ አያሌውን ወደ ባቢሎን አጋዘ፥ በባቢሎንም በመቅደሱ ውስጥ አኖረው። 8የቀረውም የኢዮአቄም ነገር፥ ያደረገውም ርኩሰት፥ በእርሱም የተገኘው ሁሉ፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል፤ ልጁም ዮአኪን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
ዮአኪን መንገሡና መማረኩ
9ዮአኪንም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወርና ዐሥር ቀን ነገሠ፤ በጌታም ፊት ክፉ አደረገ። 10#ኤር. 22፥24-30፤ 24፥1-10፤ 36፥1፤2፤ ሕዝ. 17፥12፤ ኤር. 44፥1፤ ሕዝ. 17፥13።ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደናፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፥ የከበረውንም የጌታን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።
ሴዴቅያስ መንገሡ
11 #
ኤር. 34፥1-22፤ 35፥1-17። ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አንድ ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ። 12በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ፤ ከጌታም አንደበት የመጣውን ቃል በተናገረው በነቢዩ በኤርምያስ ፊት ራሱን አላወረደም። 13#ሕዝ. 17፥15።ደግሞም በጌታ አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደናፆር ላይ ዓመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ ጌታ እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ ልቡንም አጠነከረ። 14ደግሞም የካህናቱ አለቆች ሁሉ ሕዝቡም እንደ አሕዛብ ያለ ርኩሰት ሁሉ በመከተል መተላለፍን አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም ጌታ ራሱ የቀደሰውን የጌታን ቤት አረከሱ።
ኢየሩሳሌም መውደቅዋ
15የአባቶቻቸውም አምላክ ጌታ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስላዘነ ማለዳ ተነሥቶ መልክተኞቹን ወደ እነርሱ ይልክ ነበር። 16እነርሱ ግን የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በጌታ መልክተኞች ይሳለቁ፥ ቃላቱንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
17 #
ኤር. 21፥1-10፤ 41፥1-5። ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጉልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጎልማሳውንና ድንግሊቱን ሽማግሌውንና አዛውንቱን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው። 18የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላቁንና ታናሹን፥ የጌታንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የሹማምንቱን መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ። 19#1ነገ. 9፥8።የእግዚአብሔርንም ቤት አቃጠሉ፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ፥ የንጉሥ ቅጥሮችዋንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፥ ዕንቊውንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፉ። 20ከሰይፍም ያመለጡትን ወደ ባቢሎን ማረካቸው፤ የፋርስ ንጉሥም እስኪነግሥ ድረስ ለንጉሡና ለልጆቹ ባርያዎች ሆኑ፤ 21#ኤር. 25፥11፤ 29፥10።በኤርምያስ አንደበት የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፤ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አደረገች።
ንጉሥ ቂሮስ ለምርኮኞች አርነት ማወጁ
22በኤርምያስም አንደበት የተነገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ጌታ የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፤ እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ ነገረ፥ ደግሞም በጽሑፍ እንዲህ ብሎ አወጀ፦ 23#ኢሳ. 44፥28።“የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰማይ አምላክ ጌታ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል ከሕዝቡ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ ጌታ ከእርሱ ጋር ይሁን፥ እርሱም ይውጣ።’ ”
Currently Selected:
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 36: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ