የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ሳሙኤል 6:1-19

1 ሳሙኤል 6:1-19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ሰባት ወር ተቀ​መ​ጠች። ምድ​ራ​ቸ​ውም አይ​ጦ​ችን አወ​ጣች። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ካህ​ና​ት​ንና ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችን ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ጠር​ተው፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ላይ ምን እና​ድ​ርግ? ወደ ስፍ​ራ​ዋስ በምን እን​ስ​ደ​ዳት? አስ​ታ​ው​ቁን” አሉ። እነ​ር​ሱም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ብት​ሰ​ድ​ዱ​አት ስለ አሳ​ዘ​ና​ች​ሁ​አት የበ​ደል መባእ ስጡ እንጂ ባዶ​ዋን አት​ስ​ደ​ዱ​አት፤ የዚ​ያን ጊዜም ትፈ​ወ​ሳ​ላ​ችሁ፤ ስር​የ​ትም ይደ​ረ​ግ​ላ​ች​ኋል፤ አለ​ዚያ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ከእ​ና​ንተ አይ​ር​ቅም” አሉ። እነ​ር​ሱም፥ “ስለ መቅ​ሠ​ፍቱ የም​ን​ሰ​ጠው የበ​ደል መባእ ምን​ድን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ን​ተ​ንና አለ​ቆ​ቻ​ች​ሁን፥ ሕዝ​ባ​ች​ሁ​ንም ያገ​ኘች መቅ​ሠ​ፍት አን​ዲት ናትና እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች ቍጥር አም​ስት የወ​ርቅ እባ​ጮች፥ አም​ስ​ትም የወ​ርቅ አይ​ጦች አቅ​ርቡ። እጁ ከእ​ና​ን​ተና ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ ከም​ድ​ራ​ች​ሁም ይቀ​ልል ዘንድ፥ የእ​ባ​ጫ​ች​ሁን ምሳሌ፥ ምድ​ራ​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ጠ​ፉ​ትን የአ​ይ​ጦ​ችን ምሳሌ አድ​ር​ጋ​ችሁ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብ​ርን ስጡ። ግብ​ጻ​ው​ያ​ንና ፈር​ዖ​ንም ልባ​ቸ​ውን እን​ዳ​ጸኑ ልባ​ች​ሁን ለምን ታጸ​ና​ላ​ችሁ? በተ​ዘ​ባ​በ​ቱ​ባ​ቸው ጊዜ ያወ​ጡ​አ​ቸው አይ​ደ​ሉ​ምን? እነ​ር​ሱም አል​ሄ​ዱ​ምን? አሁ​ንም ወስ​ዳ​ችሁ አን​ዲት አዲስ ሰረ​ገላ ሥሩ፤ የሚ​ያ​ጠ​ቡም፥ ቀን​በር ያል​ተ​ጫ​ነ​ባ​ቸ​ውን ሁለት ላሞች በሰ​ረ​ገላ ጥመ​ዱ​አ​ቸው፤ እን​ቦ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለይ​ታ​ችሁ ወደ ቤት መል​ሱ​አ​ቸው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ወስ​ዳ​ችሁ በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ አኑ​ሩ​አት፤ ስለ​በ​ደል መባእ ካሳ አድ​ር​ጋ​ችሁ ያቀ​ረ​ባ​ች​ሁ​ትን የወ​ር​ቁ​ንም ዕቃ በሣ​ጥን ውስጥ አድ​ር​ጋ​ችሁ በታ​ቦቷ አጠ​ገብ አኑ​ሩት፤ ትሄ​ድም ዘንድ ስደ​ዱ​አት። ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም ተመ​ል​ከቱ፤ በድ​ን​በ​ሩም መን​ገድ ላይ ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ብት​ወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደ​ረ​ገ​ብን እርሱ ነው፤ አለ​ዚ​ያም እን​ዲ​ያው መጥ​ቶ​ብ​ናል እንጂ የመ​ታን የእ​ርሱ እጅ እን​ዳ​ል​ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።” ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ የሚ​ያ​ጠ​ቡ​ትን ሁለ​ቱን ላሞች ወሰዱ፤ በሰ​ረ​ገ​ላ​ውም ጠመ​ዱ​አ​ቸው፤ እን​ቦ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በቤት ዘጉ​ባ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት፥ የወ​ርቁ አይ​ጦ​ችና የአ​ካ​ላ​ቸው እባ​ጮች ምሳሌ ያሉ​በ​ት​ንም ሣጥን በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ጫኑ። ላሞ​ችም ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ወደ​ሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ አቅ​ን​ተው “እምቧ” እያሉ በጎ​ዳ​ናው ላይ ሄዱ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላ​ሉም፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆ​ችም እስከ ቤት​ሳ​ሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላ ይሄዱ ነበር። የቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎ​ችም በእ​ርሻ ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ከፍ አድ​ር​ገው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አዩ፤ ደስ ብሎ​አ​ቸ​ውም ተቀ​በ​ሉ​አት። ሰረ​ገ​ላ​ውም ወደ ቤት​ሳ​ሚ​ሳ​ዊው ወደ ኦሴዕ እርሻ መጣ፤ ታላ​ቅም ድን​ጋይ በነ​በ​ረ​በት በዚያ ቆመ፤ የሰ​ረ​ገ​ላ​ው​ንም ዕን​ጨት ፈል​ጠው ላሞ​ቹን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ። ሌዋ​ው​ያ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት፥ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር የነ​በ​ረ​ውን የወ​ርቅ ዕቃ ያለ​በ​ትን ሣጥን አወ​ረዱ፤ በታ​ላ​ቁም ድን​ጋይ ላይ አኖ​ሩት፤ በዚ​ያም ቀን የቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን አቀ​ረቡ። እነ​ዚ​ያም የፍ​ልስጥኤ​ማ​ው​ያን አም​ስቱ አለ​ቆች አይ​ተው በዚ​ያው ቀን ወደ አስ​ቀ​ሎና ተመ​ለሱ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ስለ በደል መባእ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረ​ቡ​አ​ቸው የሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ምሳሌ የወ​ርቅ እባ​ጮች እነ​ዚህ ናቸው፦ አን​ዲቱ ለአ​ዛ​ጦን፥ አን​ዲ​ቱም ለጋዛ፥ አን​ዲ​ቱም ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ አን​ዲ​ቱም ለጌት፥ አን​ዲ​ቱም ለአ​ቃ​ሮን። የወ​ር​ቁም አይ​ጦች ቍጥር ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች እንደ ነበ​ሩት ከተ​ሞች ሁሉ ቍጥር እን​ዲሁ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም እስከ ታላቁ ድን​ጋይ የሚ​ደ​ርሱ ቅጥር ያላ​ቸው ከተ​ሞ​ችና የፌ​ር​ዜ​ዎን መን​ደ​ሮች ናቸው። በዚ​ህም ድን​ጋይ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አስ​ቀ​መጡ፤ ድን​ጋ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ በቤ​ት​ሳ​ሚ​ሳ​ዊው በኦ​ሴዕ እርሻ አለ። የኢ​ያ​ኮ​ንዩ ልጆ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተመ​ል​ክ​ተው ከቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎች ጋር አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሕ​ዝቡ አም​ስት ሺህ ሰባ ሰዎ​ችን መታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን በታ​ላቅ ግዳይ ስለ መታ ሕዝቡ አለ​ቀሱ።

1 ሳሙኤል 6:1-19 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጥኤማውያን ግዛት ሰባት ወር ቈየ። ፍልስጥኤማውያን ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፣ “የእግዚአብሔርን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ ስፍራው እንዴት መመለስ እንደሚገባን ንገሩን” አሏቸው። እነርሱም፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ከበደል መሥዋዕት ጋር ስደዱት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፤ በዚያ ጊዜ ትፈወሳላችሁ፤ እጁም ከእናንተ ላይ ለምን እንዳልተነሣ ታውቃላችሁ” አሏቸው። ፍልስጥኤማውያንም፣ “የምንልከው የበደል መሥዋዕት ምን መሆን አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተንም ሆነ አለቆቻችሁን የመታው መቅሠፍት አንድ ዐይነት በመሆኑ፣ በፍልስጥኤማውያን ገዦች ቍጥር ልክ አምስት የወርቅ ዕባጮችና አምስት የወርቅ ዐይጦች ላኩ። አገሩን በማጥፋት ላይ ባሉት ዕባጮችና ዐይጦች ዐይነት ምስሎችን ሠርታችሁ ለእስራኤል አምላክ ክብር ስጡ። ይህን ካደረጋችሁ እጁን ከእናንተ፣ ከአማልክታችሁና ከምድራችሁ ላይ ያነሣ ይሆናል። እንደ ግብፃውያንና እንደ ፈርዖን ልባችሁን የምታደነድኑት ለምንድን ነው? እነርሱም እስራኤላውያንን የለቀቋቸው እግዚአብሔር በጽኑ ከቀጣቸው በኋላ አይደለምን? “ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውን ግን ወደ ቤት መልሷቸው። የእግዚአብሔርን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩ፤ በታቦቱም አጠገብ ባለው ሣጥን ውስጥ ለበደል መሥዋዕት የምትልኩትን የወርቅ ምስሎች አስቀምጡ፤ በፈለገውም መንገድ እንዲሄድ ልቀቁት፤ ነገር ግን ወዴት እንደሚሄድ ተመልከቱ፤ ወደ ቤትሳሚስ አቅጣጫ ወደ ገዛ አገሩ የሚሄድ ከሆነ፣ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እግዚአብሔር ነው። ወደዚያ ካልሄደ ግን፣ መከራው በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የእርሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን።” እነርሱም እንደዚሁ አደረጉ። ሁለቱን ላሞች ወስደው በሠረገላው ጠመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ውስጥ ዘጉባቸው። የእግዚአብሔርንም ታቦት፣ የወርቁን ዐይጦችና የዕባጮቹን ምስሎች በሠረገላው ላይ ጫኑ። ከዚያም ላሞቹ መንገዳቸውን ይዘው እምቧ እምቧ እያሉ ቀጥ ብለው ወደ ቤትሳሚስ አመሩ። የፍልስጥኤም ገዦችም እስከ ቤትሳሚስ ድንበር ተከተሏቸው። በዚህ ጊዜ የቤትሳሚስ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው ሲመለከቱም ታቦቱን በማየታቸው በጣም ደስ አላቸው። ሠረገላውም ወደ ቤትሳሚስ ወደ ኢያሱ ዕርሻ መጥቶ በአንድ ትልቅ ቋጥኝ አጠገብ ቆመ። ሕዝቡም የሠረገላውን ዕንጨት ፈልጠው፣ ሁለቱን ላሞች የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር አቀረቡ። ሌዋውያኑም የእግዚአብሔርን ታቦት፣ የወርቅ ዕቃዎቹን ከያዘው ሣጥን ጋር አውርደው በትልቁ ድንጋይ ላይ አኖሩ። በዚያችም ዕለት የቤትሳሚስ ሕዝብ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ መሥዋዕቶችንም ሠዉ። አምስቱ የፍልስጥኤም ገዦችም ይህን ሁሉ ካዩ በኋላ በዚያኑ ዕለት ወደ አቃሮን ተመለሱ። ፍልስጥኤማውያን ስለ በደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የላኳቸው የወርቅ ዕባጮች አንዱ ስለ አሽዶድ፣ አንዱ ስለ ጋዛ፣ አንዱ ስለ አስቀሎና፣ አንዱ ስለ ጌትና አንዱ ስለ አቃሮን የቀረቡ ናቸው፤ የወርቅ ዐይጦቹም ቍጥር፣ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች በሚያስተዳድሯቸው የተመሸጉ ከተሞችና ከእነዚህ ውጭ ባሉት መንደሮቻቸው ቍጥር ልክ ነው። በቤትሳሚሳዊው በኢያሱ ዕርሻ ውስጥ የእግዚአብሔርን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ትልቅ ድንጋይ እስከ ዛሬ ምስክር ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ከቤትሳሚስ ሰዎች ጥቂቱን መታ፤ ወደ እግዚአብሔር ታቦት ውስጥ ተመልክተዋልና ከመካከላቸው ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ እግዚአብሔር እጅግ ስለ መታቸውም ሕዝቡ አለቀሰ።

1 ሳሙኤል 6:1-19 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጥኤማውያን አገር ሰባት ወር ተቀመጠ። ፍልስጥኤማውያንም ካህናትንና ምዋርተኞችን ጠርተው፥ በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ምን እናድርግ? ወደ ስፍራውስ በምን እንስደደው? አስታውቁን አሉ። እነርሱም፦ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ብትሰድዱ የበደል መሥዋዕት መልሱለት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፥ የዚያን ጊዜም ትፈወሳላችሁ፥ እጁም ከእናንተ አለመራቁ ስለ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ አሉ። እነርሱም፦ ስለ በደል መሥዋዕት የምንመልስለት ምንድር ነው? አሉ። እነርሱም እንዲህ አሉ፦ እናንተንና አለቆቻችሁን ያገኘች መቅሠፍት አንዲት ናትና እንደ ፍልስጥኤማውያን አለቆች ቁጥር አምስት የወርቅ እባጮች አምስትም የወርቅ አይጦች አቅርቡ። የእባጫችሁንም ምሳሌ ምድራችሁንም የሚያጠፋአትን የአይጦችን ምሳሌ አድርጋችሁ ለእስራኤል አምላክ ክብርን ስጡ፥ እጁን ከእናንተና ከአማልክቶቻችሁ ከምድራችሁም ምናልባት ያቀልል ይሆናል። ግብጻውያንና ፈርዖንም ልባቸውን እንዳጸኑ ልባችሁን ለምን ታጸናላችሁ? እግዚአብሔር ኃይሉን ካደረገባቸው በኋላ ያወጡአቸው አይደሉምን? እነርሱም አልሄዱምን? አሁንም ወስዳችሁ አንዲት ሰረገላ ሥሩ፥ የሚያጠቡም፥ ቀን በር ያልተጫነባቸውን ሁለት ላሞች በሰረገላ ጥመዱአቸው፥ እንቦሶቻቸውንም ለይታችሁ ወደ ቤት መልሱአቸው። የእግዚአብሔርንም ታቦት ወስዳችሁ በሰረገላው ላይ አኑሩት፥ ስለ በደልም መሥዋዕት ያቀረባችሁትን የወርቁን ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቱ አጠገብ አኑሩት፥ ይሄድም ዘንድ ስደዱት። ተመልከቱም፥ በድንበሩም መንገድ ወደ ቤትሳሚስ ቢወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደረገብን እግዚአብሔር ነው፥ አለዚያም እንዲያው መጥቶብናል እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን። ሰዎቹም እንዲሁ አደረጉ፥ የሚያጠቡትን ሁለቱን ላሞች ወሰዱ፥ በሰረገላም ጠመዱአቸው፥ እንቦሳቻቸውንም በቤት ዘጉባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ታቦት፥ የወርቁ አይጦችና የእባጮቻቸው ምሳሌ ያሉበትንም ሣጥን በሰረገላው ላይ ጫኑ። ላሞችም ወደ ቤትሳሚስ ወደሚወስደው መንገድ አቅንተው እምቧ እያሉ በጎዳናው ላይ ሄዱ፥ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላሉም፥ የፍልስጥኤማውያንም አለቆች እስከ ቤትሳሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላቸው ይሄዱ ነበር። የቤትሳሚስ ሰዎችም በሸለቆው ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፥ ዓይናቸውንም ከፍ አድርገው ታቦቱን አዩ፥ በማየታቸውም ደስ አላቸው። ሰረገላውም ወደ ቤትሳሚሳዊው ወደ ኢያሱ እርሻ መጣ፥ ታላቅም ድንጋይ በነበረበት በዚያ ቆመ፥ የሰረገላውንም እንጨት ፈልጠው ላሞቹን ለእግዚአብሔር ለሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ። ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት፥ ከእርሱ ጋር የነበረውንም የወርቅ ዕቃ ያለበትን ሣጥን አወረዱ፥ በታላቁም ድንጋይ ላይ አኖሩት፥ በዚያም ቀን የቤትሳሚስ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ መሥዋዕትንም ሠዉ። ፍልስጥኤማውያንም አምስቱ አለቆች ባዩት ጊዜ በዚያው ቀን ወደ አስቀሎና ተመለሱ። ፍልስጥኤማውያን ስለ በደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረቡአቸው የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፥ አንዲቱ ለአዛጦን፥ አንዲቱም ለጋዛ፥ አንዲቱም ለአስቀሎና፥ አንዲቱ ለጌት፥ አንዲቱ ለአቃሮን የወርቁም አይጦች ቁጥር ለአምስቱ የፍልስጥኤማውያን አለቆች እንደ ነበሩት ከተሞች ሁሉ ቁጥር እንዲሁ ነበረ፥ እነርሱም እስከ ታላቁ ድንጋይ የሚደርሱ ከተሞችና መንደሮች ናቸው። በዚህም ድንጋይ ላይ የእግዚአብሔርን ታቦት አስቀመጡ፥ ድንጋዩም እስከ ዛሬ ድረስ በቤትሳሚሳዊው በኢያሱ እርሻ አለ። ወደ እግዚአብሔርም ታቦት ውስጥ ተመልክተዋልና የቤትሳሚስን ሰዎች መታ፥ በሕዝቡም ከአምስት ሺህ ሰው ሰባ ሰዎችን መታ፥ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ ግዳይ ስለ መታ ሕዝቡ አለቀሰ።

1 ሳሙኤል 6:1-19 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በፍልስጥኤም ሰባት ወር ከቈየ በኋላ፥ ሕዝቡ ካህናታቸውንና አስማተኞቻቸውን ጠርተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁአቸው፤ “ስለ እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ምን ማድረግ የሚሻለን ይመስላችኋል? ወደ ስፍራው እንዲመለስ ብናደርግ በምን ሁኔታ እንላከው? ዘዴውን ንገሩን” አሉአቸው። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “የእስራኤልን አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት መልሳችሁ ለመላክ ብትፈልጉ፥ ስለ በደላችሁ የሚከፈል ስጦታ አብራችሁ መላክ ይገባችኋል፤ የቃል ኪዳኑ ታቦት ያለ ምንም ስጦታ ተመልሶ መሄድ የለበትም፤ በዚህም ዐይነት እናንተ ከሕመማችሁ ትፈወሳላችሁ፤ እርሱ እናንተን በብርቱ የቀጣበትንም ምክንያት ልታውቁ ትችላላችሁ።” ሕዝቡም፥ “ስለ በደል የሚከፈል ይሆን ዘንድ ከምን ዐይነት ስጦታ ጋር እንላከው?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “በእባጩ አምሳል የተሠራ አምስት የወርቅ ጒልቻ፥ እንደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ብዛት በአይጥ አምሳል የተሠራ አምስት የወርቅ ጉልቻ መሆን አለበት፤ በእናንተ ሁሉና በአምስቱ ገዢዎች ላይ የተላከው መቅሠፍት አንድ ዐይነት ነው። አገራችሁን ለማጥፋት በተላኩት አይጦችና እባጮች አምሳል እነዚህን ስጦታዎች ሠርታችሁ ለእስራኤል አምላክ ክብር መስጠት አለባችሁ፤ ይህን ብታደርጉ ምናልባት እናንተን፥ አማልክታችሁንና ምድራችሁን የሚቀጣበትን መቅሠፍት ያነሣ ይሆናል፤ የግብጽ ንጉሥና ግብጻውያን እንዳደረጉት ስለምን ልባችሁን ታደነድናላችሁ? እስራኤላውያን የግብጽን ምድር ለቀው የወጡት፥ እግዚአብሔር ግብጻውያንን በብርቱ ከቀጣቸው በኋላ አልነበረምን? ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት ጥጆችን አዘጋጁ፤ ጥጆቹን ጠምዳችሁ ሠረገላው የሚሳብበትን ጫፍ በቀንበሩ ላይ እሰሩት፤ እንቦሶቻቸውንም ወደ በረት መልሱ፤ የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩ፤ ስለ በደላችሁም እንዲከፈል ከእርሱ ጋር ለመላክ የሠራችሁትን ልዩ ልዩ ወርቅ በሣጥን ውስጥ አስገብታችሁ በታቦቱ ጐን አስቀምጡ፤ ሠረገላውንም መንገድ አስይዛችሁ እንዲንቀሳቀስ ተዉት። ከዚህም በኋላ አካሄዱን ተመልከቱት፤ አቅጣጫው ወደ ቤትሼሜሽ ከተማ ያመራ እንደ ሆነ ይህን አሠቃቂ መቅሠፍት በእኛ ላይ የላከብን እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል፤ ወደዚያ አቅጣጫ ባያመራ ግን መቅሠፍቱ የመጣብን በአጋጣሚ እንጂ እግዚአብሔር የላከብን አለመሆኑን እንገነዘባለን።” እነርሱም እንደ ተነገራቸው አደረጉ፤ ሁለት ላሞች ወስደው ሠረገላ በታሰረበት ቀንበር ጠመዱአቸው፤ እንቦሶቻቸውንም ወደ በረት መልሰው ዘጉባቸው። የእግዚአብሔርንም ታቦት ወስደው በአይጦችና በእባጮች አምሳል የተሠራ ወርቅ ከተሞላበት ሣጥን ጋር በሠረገላው ላይ አስቀመጡ፤ ላሞቹም መንገዱን ሳይለቁና ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳያዘነብሉ በቀጥታ ወደ ቤትሼሜሽ በማምራት ጒዞአቸውን ቀጠሉ፤ በሚሄዱበትም ጊዜ እምቧ ይሉ ነበር፤ አምስቱ የፍልስጤማውያን ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ድረስ በመከተል ሸኙአቸው። የቤትሼሜሽም ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው በተመለከቱም ጊዜ ታቦቱን አዩ፤ ያንንም በማየታቸው እጅግ ደስ አላቸው። ሠረገላውም በቤትሼሜሽ ወደሚኖር ኢያሱ ተብሎ ወደሚጠራው ሰው እርሻ መጥቶ በትልቅ ቋጥኝ አጠገብ ሲደርስ ቆመ። ሕዝቡም የሠረገላውን እንጨት ፈለጡ፤ ላሞቹንም ዐርደው ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡአቸው። ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ታቦትና ከእርሱ ጋር የነበረውን ወርቅ የሞላበት ሣጥን አንሥተው በታላቁ ቋጥኝ ላይ አስቀመጡ፤ የቤትሼሜሽም ሰዎች የሚቃጠልና ሌላውንም መሥዋዕት ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤ አምስቱም የፍልስጥኤም ገዢዎች ይህን ሁሉ ሲመለከቱ ቈይተው በዚያው ቀን ወደ ዔቅሮን ተመለሱ። ስለ በደላቸው የሚከፈሉ ስጦታዎች ይሆኑ ዘንድ ፍልስጥኤማውያን ለእግዚአብሔር የላኩአቸው በእባጮች አምሳል የተሠሩ አምስት የወርቅ እንክብሎች አሽዶድ፥ ጋዛ፥ አስቀሎና፥ ጋትና ዔቅሮን ተብለው በሚጠሩት ከተሞቻቸው ስም የተላኩ ነበሩ፤ እንዲሁም ከተላኩት መካከል በተመሸጉ ከተሞችና ቅጽር ባልተሠራላቸው መንደሮች ሆነው አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች በሚያስተዳድሩት በእያንዳንዱ ከተማ ስም በአይጥ አምሳል የተሠሩ አምስት የወርቅ እንክብሎች ነበሩ። በቤትሼሜሽ በሚኖረው በኢያሱ እርሻ ውስጥ የእግዚአብሔርን ታቦት ያኖሩበትም ታላቅ ቋጥኝ እስከ ዛሬ ድረስ ምስክር ሆኖ ይታያል። የታቦቱን ውስጣዊ ክፍል በመመልከታቸው እግዚአብሔር ተቈጥቶ ከቤት ሼሜሽ ሰዎች መካከል ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ እግዚአብሔርም ይህን ሁሉ እልቂት በመካከላቸው በማድረጉ የቤት ሼሜስ ሰዎች በማዘን አለቀሱ።

1 ሳሙኤል 6:1-19 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የጌታም ታቦት በፍልስጥኤማውያን ሀገር ሰባት ወር ተቀመጠ። ፍልስጥኤማውያን ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፥ “የጌታን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ ስፍራው እንዴት መመለስ እንደሚገባን ንገሩን” አሏቸው። እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ከበደል መሥዋዕት ጋር ስደዱት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፤ በዚያን ጊዜ ትፈወሳላችሁ፤ እጁም ከእናንተ ላይ ለምን እንዳልተነሣ ታውቃላችሁ” አሏቸው። እነርሱም፥ “የምንልከው የበደል መሥዋዕት ምን መሆን አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተንም ሆነ አለቆቻችሁን የመታው መቅሠፍት አንድ ዓይነት በመሆኑ፥ በፍልስጥኤማውያን ገዥዎች ቍጥር አምስት የወርቅ ዕባጮችና አምስት የወርቅ ዐይጦች ላኩ። አገሩን በማጥፋት ላይ ባሉት ዕባጮችና ዐይጦች ዓይነት ምስሎችን ሠርታችሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ክብር ስጡ። ይህን ካደረጋችሁ እጁን ከእናንተ፥ ከአማልክቶቻችሁና ከምድራችሁ ላይ ያነሣ ይሆናል። ግብፃውያንና ፈርዖን እንዳደረጉት ልባችሁን የምታደነድኑት ለምንድን ነው? እነርሱ እስራኤላውያንን የለቀቋቸው እርሱ በጽኑ ከቀጣቸው በኋላ አይደለምን? ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውን ግን ወደ ቤት መልሷቸው። የጌታን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩ፤ ስለ በደልም መሥዋዕት ያቀረባችሁትን ልዩ ልዩ የወርቅ ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቱ አጠገብ አኑሩት፤ መንገዱንም እንዲሄድ ልቀቁት። ከዚያም ወዴት እንደሚሄድ ተመልከቱ፤ ወደ ገዛ አገሩ ወደ ቤትሼሜሽ አቅጣጫ የሚሄድ ከሆነ፥ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እርሱ ነው። ወደዚያ ካልሄደ ግን፥ መከራው በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የእርሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን።” እነርሱም እንደዚሁ አደረጉ። ሁለቱን ላሞች ወስደው በሠረገላው ጠመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ውስጥ ዘጉባቸው። የጌታን ታቦት በአይጦችና በእባጮች ምስል ከተሠራ ወርቅ ከተሞላበት ሣጥን ጋር በሠረገላው ላይ አስቀመጡ፤ ከዚያም ላሞቹ መንገዳቸውን በመያዝ፥ እምቧ እያሉ፥ ቀጥ ብለው ወደ ቤትሼሜሽ አመሩ። የፍልስጥኤም ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ተከተሏቸው። በዚህ ጊዜ የቤትሼሜሽ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው ሲመለከቱም ታቦቱን በማየታቸው በጣም ደስ አላቸው። ሠረገላውም ወደ ቤትሼሜሽ ወደ ኢያሱ እርሻ መጥቶ ቆመ። በዚያ ስፍራ አንድ ትልቅ ቋጥኝ ነበር። ሕዝቡም የሠረገላውን ዕንጨት ፈለጡት፤ ላሞቹንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ለጌታ አቀረቡ። ሌዋውያኑም የጌታን ታቦትና የወርቅ ዕቃዎቹን የያዘውን ሣጥን አውርደው በትልቁ ቋጥኝ ላይ አኖሩ። በዚያችም ዕለት የቤትሼሜሽ ሕዝብ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ መሥዋዕቶችንም ሠዉ። አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎችም ይህን ተመልክተው፥ በዚያው ዕለት ወደ ዔቅሮን ተመለሱ። ፍልስጥኤማውያን ስለ በደል መሥዋዕት ለጌታ የላኳቸው የወርቅ ዕባጮች እነዚህ ናቸው፤ አንዱ ስለ አሽዶድ፥ አንዱ ስለ ጋዛ፥ አንዱ ስለ አስቀሎና፥ አንዱ ስለ ጌት፥ አንዱ ስለ ዔቅሮን የቀረቡ ነበሩ። የወርቅ ዐይጦቹም ቍጥር፥ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች በሚያስተዳድሯቸው የተመሸጉ ከተሞችና ከእነዚህ ውጭ ባሉት መንደሮቻቸው ቍጥር ልክ ነው። በቤትሼሜሻዊው በኢያሱ እርሻ ውስጥ የጌታን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ትልቅ ቋጥኝ እስከ ዛሬ ምስክር ነው። ጌታም ከቤትሼሜሽ ሰዎች ጥቂቱን መታ፤ ምክንያቱም ወደ ጌታ ታቦት ውስጥ በመመልከታቸው ነበር። ከመካከላቸው ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ ጌታ እጅግ ስለ መታቸውም ሕዝቡ አለቀሱ።